Get Mystery Box with random crypto!

#ድርድር ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምን | Ethio channel

#ድርድር

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምንጫቸው በግልፅ ያልተገለፁ/ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር።

ዛሬ ከህ/ተ/ም/ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድርድርን በተመለከተ መረጃ ሰጥተዋል።

" ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች። ሕዝብ ሳያውቀው የሚደረግ ድርድር የለም። " ብለዋል።

አክለውም ፥ " በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ ሲሆን፣ እስካሁን ውጤቱን አላሳወቀም። የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ ነው። " ብለዋል።

" ውጊያ ሲመጣ ለሕዝብ አሳውቀን የጀመርን ሰዎች፣ ድርድር ከተጀመረ የሚያስደብቀን ነገር የለም። ነገር ግን፣ የብቻ ጠላት የለም የሀገር ጠላት እንጂ፣ ለብቻም የሚሰራ ሥራ የለም በጋራ እንጂ። " ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

የእኛም የሕዝባችንም ፍላጎት ለጥይት የሚወጣ ውጪ ለልማት እንዲወጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የተደበቀ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፦
- በፀጥታ ተቋማት ዝግጅት፣
- በህግ ማስከበር፣
- በ ' ተረኝነት ' ጉዳይ ፣
- በማህበራዊ ሚዲያዎች ጉዳይ ፣
- ሌብነትን በተመለከተ፣
- የብሄራዊ ምክክሩን በተመለከተ የሰጧቸው ምላሽ እና ማብራሪያዎች በዚህ ታገኛላችሁ https://telegra.ph/PM-Abiy-Ahmed-06-14-2 (#PMOEthiopia)

@adis_mereja