Get Mystery Box with random crypto!

በዲማ ወረዳ ' ማንነታቸው አልታወቀም ' በተባሉ ግለሰቦች በተፈፀመ ጥቃት የ6 ዜጎች ህይወት አልፏ | Ethio channel

በዲማ ወረዳ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች በተፈፀመ ጥቃት የ6 ዜጎች ህይወት አልፏል።

ከትላትን በስቲያ ፤ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ በሚገኘው ስደተኛ መጠለያ ጣቢያና በመርከስ ቀበሌ ለጊዜው ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ ግለሰቦች የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ፤ " ቅዳሜ ምሽት 3:30 አካባቢ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት የ4 ሰው ህይወት አልፏል " ብሏል።

ግለሰቦቹ ከዲማ ከተማ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኡኩጎ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ከቀኑ 10:30 አካባቢ በመርከስ ቀበሌ " ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ " ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@adis_mereja