Get Mystery Box with random crypto!

#ከስሜ_በፊት ክፍል ስምንት 'አማን እያበድክ ነው!?' 'አላበድኩም ቡራ' አማኑኤል በተረጋጋ ድም | ሜርሲ እና ብዕሯ✍

#ከስሜ_በፊት
ክፍል ስምንት

"አማን እያበድክ ነው!?"
"አላበድኩም ቡራ" አማኑኤል በተረጋጋ ድምፅ መለሰለት።
"እያበድክ ነው እንጂ.."ብሩክ ከተቀመጠበት ወንበር እምር ብሎ ተነስቶ መንጎራደድ ጀመረ።
"እሺ ቢሮ ነው ያለነው ተረጋግተን እናውራ"
ብሩክ ወገቡን ይዞ አፍጦበት ከቆየ በኋላ ወደ ወንበሩ ተመለሰ ቁጭ አለ።
"በቃ ሁሉንም ነገር ጨረስክ አይደል...ከዛ ስፍራ ውጣ።አንተ ስትኖር እኮ ነው ሌሎችን ማኖር የምትጀምረው።ሉክ አት ዩር ቦዲይ የለህም እኮ መንምነሃል።"
"ቡራ የምልህ ግን ገብቶሃል!?እኔም እነርሱን ከመቀላቀሌ ከማወቄ በፊት እንዳንተ ነበርኩ።እንዳንተ አስብ ነበር....ካገኛኋቸው በኋላ ግን ፍፁም ሌላ ናቸው ሌላ።እነርሱ ያጡት ምግብ አይደለም ከጋንዳ ውስጥ ያገኙትን ትርፍራፊ በልተው መኖር የሚችሉ ናቸው።እነርሱ ያጡት ቤት አይደለም በየ ጎዳናው በየሸራው ውስጥ እራሳቸውን ማኖር ያስለመዱ ሰዎች ናቸው...."
"ታዲያ ምንድነው ያጡት?" ብሩክ በመገረም ጠየቀው።
* * * *
ብሩክ መኪናውን አማኑኤል ወደሚያዝበት እየነዳ ከአንድ ስፍራ ሲደርሱ እንዲያቆም ነገረው።ብሩክ ግራ ቀኙን ሲመለከት ከቆየ በኋላ
"አማን እዚህ መኪናዬን ማቆም አልችልም"
"ለምን!?"
"ይሄን ሰፈር በፊልምም ቢሆን አይቻለሁ።ገና እግርህ ከመኪናው ከመውረዱ ነው መኪናውን ፈታተው እንዳልነበር የሚያደርጉት።"
አማኑኤል ፈገግ እያለ "ለዚህ ነው አታውቃቸውም የምልህ።ፀባይ ከሌለህ አንተንም እንዳልነበረህ ወደ መጣህበት መነመንህን ይሰዱሃል።"
"ምን አልክ!?" ብሩክ በመደናገጥ ጠየቀው።አማኑኤል እየሳቀ ከመኪናው ወረደ።ብሩክ ግን ላለመውረደ አሻፈረኝ አለ።
ከጎዳናው ጥግ ድንጋይ ላይ ሰብሰብ ብለው ከተቀመጡት ውስጥ አንዱ ቀና ብሎ እንዳየ
"እንዴ አማኑ" ብሎ ሲነሳ ሁሉም ቀና ብለው አዩት።እየተንጋጉ መጥተው በየሙዳቸው ሰላም አሉት።ብሩክ ከመኪናው ውስጥ ሆኖ ሲያወሩት በመደነቅ ተመለከት።ወደ እርሱ አንዱን ይዞ ሲመጣ ብሩክ መሪውን አጥብቆ ያዘው።ልጁ የመኪናውን መስታወት ሲያንኳኳ ቀስ አድርጎ ከፈተለት።
"እእ አባቴ ፒስ ነው...ስለ መኪናህ ምንም ሃሳብ አይግባህ እኛ አለንላት።ቀና ብሎ በክፉ ዓይን የሚሾቃት እንኳ አይኖርም።...እስካሁንም አፍጥጠሻል አረ ውረጂ...." አማኑኤል እንዲወርድ በአንገቱ ምልክት ሰጠው።
* * * *
እቤቱን ዘልቃ ስትገባ ማንም አልነበረም ነበር።በእጇ የያዘችውን ፔስታል ከመሬቱ በማስቀመጥ ወደ ፍራሹ ተመለከተች።ተዝረክርኮ ነበር።ብልድልብሱን እያስተካከለች እያለ ወደ መደርደሪያው ተመለከተች።ዓይኗ ቀድሞ ያረፈው ማስታወሻው ላይ ነበር።ብልድልብሱን ወደ ቦታው መልሳ ፈራ ተባ እያለችም ቢሆን ከመደርደሪያው ማስታወሻውን አነሳች።ብዙ ካንገራገረች በኋላ ከፍራሹ ቁጭ በማለት የመጀመርያውን ገፅ ገለጠች።
* * * *
ብሩክ የሚያየውን ባለማመን ግራ ቀኝ ያማትራል።ሽታው አፍንጫውን ሲሰነፍጠው ከኪሱ ማስክ በማውጣት አደረገ።
"አማን እንሂድ በቃ"
"ገና መች አየህና..."
"ያየሁት ከበቂ በላይ ነው"
አማኑኤል ከቆሻሾቹ ክምር ጠጋ በማለት ከአንዱ ጉብታ ላይ ቆመ ብሩክም ተጠጋው።
በጣም ብዙ ወጣቶች እናቶች ህፃናት ልጅ ያዘሉ ከመኪና የሚራገፈውን ምግብ በፔስታል እያደረጉ እየተቀራመቱ ይበላሉ።ግማሹ የያዘውን ይዞ ይሄዳል።"
"ማለት አይሞቱም!?" ብሩክ የሚያየው ነገር ከአቅሙ በላይ ሆኖበት ነበር።
"እየኖሩ ነው እንግዲህ።" ከዛ ስፍራ ወጣ ብሎ በጠባብ መንገድ እየሄዱ ይመለከቱ ነበር።
ህፃናት ብርድ ያቆፈደደ ሰውነታቸውን እያከኩ በዛው ሰውነታቸው መሬት ለመሬት ከጓደኞቻቸው ጋር ሲንከባለሉ።በዛው እጃቸው እናታቸው ከጋንዳው ለቅማ ያመጣችውን ምግብ ሲቀራመቱ።እየዘገነነው ይመለከታል።ወጣቶች በሃይላንድ ለብርዱ ብለው የመኪና ቤንዚን ሲጠጡ ከወረቀት እራሳቸው እያበጁ ሲጋራ ሲሰሩና እየተቀባበሉ ሲያጨሱ ለእርሱ ከዓዕምሮው በላይ ነበር።ለሰዓታት አማኑኤል እያዞረ ከሳያው በኋላ ዝናብ መጣል ሲጀምር ወደ መኪናው አመሩ።ልጆቹ እየበሰበሱ በቦታቸው እየጠበቁለት ነበር።ብሩክ ባየው ነገር ተገረመ።አማኑኤል አመስግኗቸው ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ሊሰጥ ሲል
"አረ አማኑ ባለፈው የሰጠሀን ይሀው እስካሁን አልነካነውም።ደግሞ ሁላችንም ወደየ ቤታችን ስለተመለስን ቤት ያፈራውን መብለት ጀምረናል።እማዬ ግን ያንን ልጅ ልባርከው አምጡት ስትል ነበር።"
አማኑኤል ፈገግ ብሎ
"በቃ ነገ እመጣለሁ ብሏል በልልኝ ይሄን ደግሞ ለእናትህ ቡና መግዣ ይሆናል ተቀበለኝ እኔ ስመጣ በአሪፉ ታፈላልኛለች"
"አብሽር" ብሎት ተቀብሎት ሄደ።መኪና ውስጥ እንደገቡ ብሩክ በረጅሙ ተንፍሶ
"በፊልም ላይ ሳያቸው እንደማንኛውም ሰው አሳዝነውኝ ተውኳቸው።በአካል ግን ከዓዕምሮ በላይ ነው"
አማን ፈገግ አለ የፈለገው ይሄንኑ ነበር።
* * * *
አማኑኤል ወደ ውስጥ ሲዘልቅ አራቱም ተቀምጠው አገኛቸው።እንደገባ ሲያዩ ከተቀመጡበት ብድግ አሉ።ፊታቸው ተቀያይሮ ነበር።መዓዛን ሲመለከት አልቅሳ እንደነበር ዓይኖቿን አይቶ ተረዳ።መዓዛ እጅ ላይ ማስታወሻውን ሲያየው ባለበት ደንግጦ ቆመ።ነገሮች ሁሉ እንደተበላሹ ለመረዳት ጊዜም አልፈጀበት።

ይቀጥላል.....

@Mercy_ena_berua
@Mercy_ena_berua