Get Mystery Box with random crypto!

' . . . . ከአላዛር ጋር ስንተኛው የፍቅር ምዕራፍ ላይ ነበርን? እንዴት ነው የሚሰላው? ሂሳብ | .

" . . . . ከአላዛር ጋር ስንተኛው የፍቅር ምዕራፍ ላይ ነበርን? እንዴት ነው የሚሰላው? ሂሳብ አለው? ደንብ አለው ከጥንት ዘመን ተረቆ የተላለፈልን ከዕውን ሕይወት ይሁን ከልብ ወለድ ተጠረቃቅሞ የተበጀ ማብራሪያ ስልት ?አብረን አድረን በጠዋት ሳልቀሰቅሰው. . . ቀስቅሼው በሞቀ ውሃ ፊቱን እንደልጅ አጥቤ በፎጣ ሳላደርቀው. . .(መጀመሪያ በመዳፌ እልግለታለሁ) ወንበር ላይ ሳላስቀምጠው. . . አስቀምጬ እስኪጠግብ ሳላጎርሰው. . . አብልቼ ልብሱን አልብሼ ስራው ሳልሸኘው. . . አራት አምስቴ ከቢሮዬ ቢሮው እየደወልኩ በስሜቴና በጆሮው ትንፋሹን ሳልሰማው. . .ቁልምጫውንም እንደ ምሳዬ ሳልበላው. . .ምሽት እምሰራበት ቦታ መጥቶ ቆሞ ወዲያ ወዲህ እያለ ፀጉሩንእየዳበሰ ሳይጠብቀኝ. . .በሰፊው ከተማ እዛ እዛ እዛና እዛ በእግር ሳያዞረኝ. . .ገላዬን እጠበኝ ብዬው ውሃ ውስጥ ሳንጋለል. . .በዋናዬ መሃል ጣቱን እንደ ከረሜላ ሳልጠባ. . .ጭር ባለ ሌሊት ቀስቅሼው ‹‹አዝዬ ናፈቅኸኝ›› ሳልለው. . .ማለት እችላለሁ
ፍቅር አለቀ ?
ፍቅር ተጠናቀቀ ?
ፍቅር ላመ ደቀቀ?"

#መረቅ
#አዳም_ረታ