Get Mystery Box with random crypto!

.

የቴሌግራም ቻናል አርማ merbebtt — . M
የቴሌግራም ቻናል አርማ merbebtt — .
የሰርጥ አድራሻ: @merbebtt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 343
የሰርጥ መግለጫ

እ ን ደ ው የላይ ላዩን . . .
@hmf27

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-11 20:20:46
ROPHNAN SIDIST-VI

1.ቃል
2.ሰናዬ
3.ወጋሕት
4.ሀሜት
5.እሰይ
6.ቢሆን
7.ደሴ
8.ፎሌ
9.ህይወት
10.መርከብ
11.የእሳት እራት
12.ታውቂያለሽ ይሆን
13.አማኙ ቅኔ

May all the glory and grace in the world be yours!

H.M.F 27
@MERBEBTT
51 viewshannamariam_27, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 06:50:36
Finally free from the confusion of what am i going to class listening to ! ሀምሌ 4ዬ

Welcome
SIDIST-VI
62 viewshannamariam_27, edited  03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 17:23:00
" . . . . ከአላዛር ጋር ስንተኛው የፍቅር ምዕራፍ ላይ ነበርን? እንዴት ነው የሚሰላው? ሂሳብ አለው? ደንብ አለው ከጥንት ዘመን ተረቆ የተላለፈልን ከዕውን ሕይወት ይሁን ከልብ ወለድ ተጠረቃቅሞ የተበጀ ማብራሪያ ስልት ?አብረን አድረን በጠዋት ሳልቀሰቅሰው. . . ቀስቅሼው በሞቀ ውሃ ፊቱን እንደልጅ አጥቤ በፎጣ ሳላደርቀው. . .(መጀመሪያ በመዳፌ እልግለታለሁ) ወንበር ላይ ሳላስቀምጠው. . . አስቀምጬ እስኪጠግብ ሳላጎርሰው. . . አብልቼ ልብሱን አልብሼ ስራው ሳልሸኘው. . . አራት አምስቴ ከቢሮዬ ቢሮው እየደወልኩ በስሜቴና በጆሮው ትንፋሹን ሳልሰማው. . .ቁልምጫውንም እንደ ምሳዬ ሳልበላው. . .ምሽት እምሰራበት ቦታ መጥቶ ቆሞ ወዲያ ወዲህ እያለ ፀጉሩንእየዳበሰ ሳይጠብቀኝ. . .በሰፊው ከተማ እዛ እዛ እዛና እዛ በእግር ሳያዞረኝ. . .ገላዬን እጠበኝ ብዬው ውሃ ውስጥ ሳንጋለል. . .በዋናዬ መሃል ጣቱን እንደ ከረሜላ ሳልጠባ. . .ጭር ባለ ሌሊት ቀስቅሼው ‹‹አዝዬ ናፈቅኸኝ›› ሳልለው. . .ማለት እችላለሁ
ፍቅር አለቀ ?
ፍቅር ተጠናቀቀ ?
ፍቅር ላመ ደቀቀ?"

#መረቅ
#አዳም_ረታ
75 viewsAb, 14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:41:43 አሁን ደግሞ ሌሎች ወንድሞቻቸውን በማጣጣል በመናቅ እነሱ ብቻ እሚወደዱ ስለሚመስላቸው ወንዶቻችን የ 2 ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናደርጋለን።

H.M.F 27
@Merbebtt
24 viewsAb, 13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:07:29
"ይህቺ ሳንቲም ከእኔ እጅ ስትወጣ ያገኛት ሰው ወዜን ነክቷል። ፊት ለፊት ቢያየኝ ይንቀኛል። ግን በመኖር ኪነ-ጥበብ ተነካክተናል። አያመልጥም።

ከለማኝ ወደ ቻሪው ይሄዳል ...

ሐብታም ደሃ መሆኑ አይደለም ጉዳዬ። ወገኔ መሆኑ ይበቃኛል"

***
#ግራጫ_ቃጭሎች
58 viewsAb, 11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 14:00:38 ነጠብጣብ ሐሳቦች

ሰማይ ከሚመክን ፤ይጸንስ መከራ
ያርግፍ ! ያርግፍ! ያርግፍ ! መኣት እያፈራ
የ’ሣት ዛፍ ባለበት ፤ ሰደድ አያስፈራ
.............
ከሐምሌት ጋር ሞቷል፤ የማመንታት ዓለም
ከሆኑ በኋላ፤ አለመሆን የለም
ሸክም ጸጋ ሆኗል፤ ጸጋህን አትግፋ
በጠባብ ዓለም ውስጥ፤ ትከሻህን አስፋ!
............
አንድ ሕልም እንደ ጠጅ፤ እየደጋገሙ
ንግር ፤ትንቢት ሳይሆን፤ ታሪክ እያልለሙ
ተኝቶ መነሣት
አቤት ሲያቅለሸልሽ
ጌታ ሆይ አትንሣት
ነፍሴን እንቆቅልሽ

በዕውቀቱ ስዩም
52 viewsAb, 11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 19:31:44
We can't do anything even if we look crazy
72 viewsH.M.F, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 19:27:42 አሁን ደግሞ ሌሎች ወንድሞቻቸውን በማጣጣል በመናቅ እነሱ ብቻ እሚወደዱ ስለሚመስላቸው ወንዶቻችን የ 2 ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናደርጋለን።

H.M.F 27
@Merbebtt
80 viewsH.M.F, 16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:44:31 ረዥም ዝምታ
የነፍስ ፀጥታ
ሰፈነ በቤቱ
ሰከነ ከልቡ
ባለ ዕጁ አሰበ
ሀጥያኑ ታጠበ
ፈራሽ ገላ አፈርን ከመናፈቅ ለየ።
86 viewsH.M.F, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:21:53 ሃናማርያም

ትላንት ሌላ ዛሬ ሌላ !

ከጥንተ ጥንተ ዘመን እየተሳቡ መጥተው "አደገች እኮ ቁርጥ ቅላቷ ያባቷ " ምናምን እያሉ መዳፋቸው ጉያ ጉንጬን ሰክተው ከሚመጠምጡ የአዋቂ ውሪዎች መሀል ከእያንዳንዷ ሴት ጀርባ ቢቻላቸው የራሳቸው ሊያደርጉት የሚፈልጉትን አይነት ታታሪ፣ ጎበዝ፣ ልጆቿን ሲበዛ የሚወድላት ጥሩ አባት እና ጥሩ ባል ያላትን እናቴን በሆዳቸው መንፈሳዊ ቅናታቸውን አዝለው በጥርሳቸው ግን የወዳጅነታቸውን የሚፈግጉላት ነበሩ። መቀማጠልን የሚፈቅድ ባል። ወለድሽ አገባሁሽ ሳይል ጎንበስ ብሎ የሚታዘዛት ባል። ለሷ ሲሉት ካለው ላይም ከሌለው ላይም የማይሰስት ባል። ለማንምና ለምንም ቀርቶ "አላውቃችሁም"ብላ አንጀታቸውን ለቆረጠችላቸው ቤተሰቦቿ እንኳን አሳልፎ የማያስነካ ባል። እንዴት አያስቀናቸው?!
እኔ በማውቀው አባቴ ሲያኖረን እራሱን ሰውቶ ነው። ፍላጎቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ። ጭንቀቱን አምቆ። ተሳስቶ ቢያስከፋን የሚጨብጠው ኤሌትሪክ ሙሊት ገመድ ይጠፋዋል። ድሎትን ከሞላ ጎደል ገርምማ ያደገች ሚስት ናትና ያለችው ችግር ብሎ ነገር አታውቅለትም። ጠባብ ቤት ምን ሊመስል እንደሚችል ከአባቴ ጋር ከመኖሯ አስቀድሞ ከግምቷም አልነበር።

H.M.F 27
@Merbebtt
79 viewsH.M.F, edited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ