Get Mystery Box with random crypto!

ካቦድ ☁️

የቴሌግራም ቻናል አርማ intoglory — ካቦድ ☁️
የቴሌግራም ቻናል አርማ intoglory — ካቦድ ☁️
የሰርጥ አድራሻ: @intoglory
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 613
የሰርጥ መግለጫ

በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ መኖር
Living in the presence of God

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-04 21:51:09 በዝምታ ውስጥ እግዚአብሔርን እያገኘሁት ነው
ከሁከት ወጥቼ ዝም ብዬ ሳደምጥ እግዚአብሔር ይናገራል

እርሱን ስሙት የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ በዝምታ እንዲናገር ዕድል ከተሰጠው ለልብ ይናገራል

ታላቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮችን ሲሰነጥቅ፣ አለቶችን ሲሰባብር እግዚአብሔር ይሆን ብዬ ልሰማው ቀረብኩ

የምድር መናወጥ ሲሆን አሳትም በመካከል ሲነድ እግዚአብሔር እንዳለ አስቤ ድምፁን ናፈቅሁ

ነገር ግን እግዚአብሔር በነውጡ መሃል አልተገኘም፣ በጫጫታውና በብልጭታው መሀል የለም

በሁሉ ደክሜ ሁከቱንና እሩጫውን እንዳላይ በሬን ዘግቼ በዝምታ ውስጥ ስቀመጥ ግን...

አንድ ነገር አስተዋልኩ እግዚአብሔር በዝምታው መካከል ያልፋል፣ በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ጣፋጭ ድምፁን ያሰማል በቃሉ እንዲህ እንደተፃፈ

"እርሱም፦ ውጣ፥ በተራራውም ላይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም አለ። እነሆም፥ እግዚአብሔር አለፈ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጠቀ፤ ዓለቶቹንም ሰባበረ፥ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም። ከነፋሱም በኋላ የምድር መናወጥ ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በምድር መናወጥ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መናወጥ በኋላ እሳት ሆነ፥ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም። ከእሳቱም በኋላ ትንሽ የዝምታ ድምፅ ሆነ። ኤልያስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመጐናጸፊያው ሸፈነ፥ ወጥቶም በዋሻው ደጃፍ ቆመ። እነሆ፦ ኤልያስ ሆይ፥ በዚህ ምን ታደርጋለህ? የሚል ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።" 1ኛ ነገሥት 19፥11-13

@intoglory
86 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 09:53:49 አዲስ ነገር

እግዚአብሔር በሕይወታችን አዲስን ነገር ለማድረግ ሁልጊዜ ፈቃደኛና ደስተኛ ነው

“እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል..." ኢሳ 43፥19

ይህ አዲስ ነገር ታዲያ በሕይወታችን ይበቅልና ይታይ ዘንድ አስቀድሞ በሕይወታችን ሊሆን ስለሚያስፈልገው አንዳች ነገር ጌታ ኢየሱስ በቃሉ እንዲህ ያስተምራል

"በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።" ማቴ 9፥16-17

አዲሱን ነገር በአዲስ ማንነት መቀበል

አሮጌ ማንነት አዲስን የሕይወት ስርዓት የመቀበል ችሎታ የለውም

ይህ በአረጀ ልብስ ላይ አዲስን እራፊ እንደሚያኖር ፣ ማጣፊያውም ልብሱን እንደሚቦጭቀው ሕይወታችንን የሚቦጭቅ ነው

ብዙዎቻችን አዲስ የሕይወት ስርዓት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ሕይወታችን የምንጠብቅ ነገር ግን አሮጌውን ለመጣል የሳሳን ሆነን በእግዚአብሔር ቤት እንመላለሳለን

ይህም በአረጀ አቁማዳ አዲስን የወይን ጠጅ እንደማኖር ሁኖ የሚያጠፋን እንጂ የሚጠቅመን አይደለም

አሁን የሚበቅል አዲስ የሕይወት ስርዓት በተለወጠና በአዲስ የሕይወት ስርዓት ለመመላለስ ፈቃደኛ ለሆኑ የተሰጠ የእግዚአብሔር ቃል ቃልኪዳን ነው

አዲሱ የወይን ጠጅና አዲሱ አቁማዳ እርስ በእርሳቸው እንደሚጠባበቁ ሁሉ በዚህ የአዲስ ሕይወት ኪዳን የተጠበቀ ነው

ከእግዚአብሔር የምንቀበለውን ሁሉ የምንቀበለው በመታደስ ውስጥ ነው

“የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።” ሮሜ 12፥2

በኢየሱስ ስም ይህ ክረምት በተሃድሶ አልፈን ለሕይወታችን አዲስን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ የምንቀበልበት ክረምት ይሁንልን

@intoglory
426 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 18:22:29 “እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።” ዮሐ 8፥32

አርነት በነፃነት መመላለስን የሚያመለክት ቃል ነው

አርነት የወጡ ነገሮች በነፃነት የመመላለስ ኃይል አላቸው

በሕይወታችን ብዙ ነገሮቻችን በነፃነት ይመላለሱ ዘንድ እንጂ በባርነት ቀንበር ስር እንዳይወድቁ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው

መንፈሳዊ ህይወታችን፣አገልግሎታችን፣ የለት ተለት ኑሯችን፣ ሰላማችን፣ ጤናችን፣ ኢኮኖሚያችን፣ አእምሯችን...ወዘተ. አርነት ያስፈልጋቸዋል

ይህ አርነት ታዲያ እንዲሁ የሚመጣ ሳይሆን እንደጌታ ቃል እውነትን በማወቅ የሚሆን ነው

እውነትን ማወቅ የተያዝንበትን የባርነት ቀንበር በግልጽ ለይቶ ከማወቅ ይጀምራል

እውነት የተሰወረውን ቀንበራችንን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፣ በእግራችን ያለን ሰንሰለትና የተያዝንበትን ስውር ወጥመድ ይገልጥልናል

እውነት ብርሃን ነው በላያችን ሲበራ በጭለማው የተጣቡብንን ቆንጥጠው ከእኛ አልላቀቅ ያሉንን ክፋቶች ያመለክተናል

ያኔ ሁሉ ለአይኖቻችን ግልጥ ሲሁን ሸክማችንን የከበደንን ነገር ሁሉ አንድ በአንድ ማራገፍ እንጀምራለን

ዛሬ እንዲ እንጸልይ አባት ሆይ አርነት እንድወጣ አቤቱ እውነትን አውቅ ዘንድ ስጠኝ አሜን

@intoglory
301 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 17:46:22
452 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 20:43:57 “ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።” ማቴ 17፥21

ይህ ክፍል አስቀድሞ አንድ አባት ነፃ ይወጣለት ዘንድ ወደ ደቀመዛሙርቱ ይዞት ስለመጣው በአጋንንት እስራት ውስጥ ስለነበረ ልጅ በመተረክ የሚጀምር ክፍል ነው

ድዊዎችን እንዲፈውሱና አጋንንትን እንዲያስወጡ ስልጣን የተሰጣቸው ደቀመዛሙርት ታዲያ ግን ይህን ስልጣናቸውን ተጠቅመው በዚህ ብላቴና ሁኔታ ላይ መፍትሔ ማምጣት ያልቻሉ ሆነው ታይተዋል

“ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው አለው።” ማቴ 17፥16

ጌታ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በገጠማቸው በዚህ ሁኔታ መነሻ ለሁላችን የሚሆን አንድ ታላቅ ነገርን እንዲህ ያስተምራል

“ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።” ማቴ 17፥21

ይህ አይነት

ችግሮች እንደየአይነታቸው እንዲሁ መፍትሔያቸው ደግሞ ልዩ ልዩ ነው

ደቀመዛሙርቱ የችግሩን አይነት ካለማወቅ የተነሳ በከንቱ ደከሙ

የችግሮቻችንን አይነት መለየት በቀላሉ መፍትሄዎቻቸውን እንድናውቅ ያደርገናል

@intoglory
327 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, edited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 10:02:04 አዲሱ ኪዳን

ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ የሆነው ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ህይወት ጀማሪ ነው

እርሱ የመለኮትን ሙላት በሰውነት ገልጦ ያሳየ የአዲስ ኪዳን መሪ ነው

በዚህ ኪዳን በመለኮትና በሰው መካከል የነበረውን ርቀት በማስወገድ ወደ መለኮት አቅርቦናል

“አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።” ኤፌ 2፥13

አሁን አዲሱ ኪዳን የመለኮት ሙላት በሰውነት ሁሉ ተገልጦ እንዲኖር የመጣ ኪዳን ነው

ይህ ታላቅ ሚስጥር መለኮት የሆነውን ኢየሱስን በእያንዳንዳችን በምናምን ውስጥ በማኖር የተገለጠ ነው

“ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው።” ቆላ 1፥27

አዲሱ ኪዳን እግዚአብሔር በሩቅ በመገናኛው ድንኳን ሳይሆን ቀርቦ በሰውነት ማለት በእኔ፣ በአንተ፣ በአንቺ ይገለጥ ዘንድ የመጣ ኪዳን ነው

@intoglory
360 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:25:54 ህይወቴ የተለወጠበት #ሚስጥር
#ካልተለወጣቹ ክሰሱኝ
sʜᴀʀᴇ  sʜᴀʀᴇ   sʜᴀʀᴇ

@SisayAzusaRevivall
@SisayAzusaRevivall
ይ ላ ሉን
212 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:48:25 ዕብራውያን 3፥12

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እግዚአብሔርን በመካድ ወደ አለማዊነትና ህይወት ወደሌለበት ወደ አሮጊቶች ተረት ዘወር ማለት በአማኞች ዘንድ እየተለመደ የመጣ ነገር ሆኗል

ይህ ሁኔታ ታዲያ በቅዱሳን መካከል ግራ መጋባትን የሚፈጥርና ልብን የሚያሳዝን ዜና ሆኖ ብዙ ጊዜ አልፏል

በአካል ውስጥ የአንድ ብልት ህመም ለሌሎች እየተረፈ ፤ ዘላለም አብሮ ላለመቀጠል ከአካሉ ተሰብሮ የሚወድቀው ክፍል ደግሞ እጅጉን እያስመረረ ለቤተክርስቲያን የበረታ ሀዘን ነው

በሮሜ መጽሐፍ እንዳየነው ታዲያ ከግንዱ ተቆርጦ የወደቀው ቅርንጫፍ መልሶ ግንዱ ውስጥ ሊገባና ሊጣበቅ አሁንም በእግዚአብሔር ዘንድ ለወደቀው ለዚያ ብልት ተስፋ አለው(ሮሜ 11፥23-24)

ነገር ግን ለትምህርታች እንዲሆን የወደቁ ብዙዎች ከሚደረድሩት ምክንያት ባሻገር በትክክል ሰዎችን ከእግዚአብሔር ሊለይና እግዚአብሔርን ሊያስክድ ስለሚችል ዋና ነገር ከመጽሐፍ እንመልከት

ሐዋርያው ጳውሎስ በአንድ ስፍራ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።"በማለት እጅግ ብዙ ኃይላትን ሲዘረዝርና እነዚህ ኃይላት ሁሉ ግን በክርስቶስ ካለን ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለዩን የማይችሉ እንደሆኑ ያመለከታል(ሮሜ 8፥35-39)

ሐዋርያው የዘረዘራቸው እነዚህን ኃይላት በባህሪያቸው ከውጭ ተጽዕኖ የሚመነጩ በመሆናቸው ውጫዊ ኃይላት ብለን ልንላቸው እንችላለን

የትኛውም ውጫዊ ኃይል አማኞችን በክርስቶስ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለይ የሚችል አይደለም

ይኸው የእግዚአብሔር ሰው ሐዋርያው ጳውሎስ ታዲያ በዕብራውያን መልዕክቱ ላይ እግዚአብሔርን አስክዶ ከእርሱ ፍቅር ሊለየን ስለሚችል አንዳች ኃይል ግን እንዲህ ይጠቁማል

“ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ” ዕብ 3፥12

ክፉና የማያምን ልብ

ክፉና የማያምን ልብ እግዚአብሔርን ወደ መካድ ውድቀት ሊያመጡ የሚችሉ ውስጣዊ ኃይላት ናቸው

በክፋት የተሞላ ልብ ለእግዚአብሔር ፍቅር መቀመጫ ሊሆን አይችልም

የማያምን ልብም እንዲሁ የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስ ኢየሱስን በውስጡ ለማስቀመጥ አይቻለውም

“በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር...” ኤፌ 3፥16-17

እንግዲህ እኛ አማኞች ሁልጊዜ ልባችንን ከእነኚህ ብንጠነቀቅ ከክህደት እናመልጣለን እንዲህ እንደተጻፈ:-

“አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።” ምሳሌ 4፥23

@intoglory
273 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 16:26:18 2. መገለጥ (revelation)

መገለጥ መናፍስትን በመለየት የፀጋ ስጦታ ውስጥ ትልቁን ስፍራ የሚወስድ ነው

ይህ በህልም ፣ በሌሊት ራዕይና በቀጥታ ራዕይ ምስል ከሳች ሆኖ የሚመጣ የመገለጥ አይነት ሲሆን የመንፈሱን አይነትና ባህሪ በግልጽ መረዳት የሚያስችለን ፀጋ ነው

ርኩሳን መናፍስት ራሳቸውን በተለያየ አይነት ማንነት የሚገልጡ ሲሆን እነዚህን ማንነታቸውን ሊወክሉላቸው በሚችሉ ምልክቶች ራሳቸውን መስለው የሚኖሩ ናቸው

እነዚህ በብዛት ከሚገለጡባቸው ማንነቶች መካከል በጥቂቱ:- እባብ፣ዘንዶ፣ የሌሊት ወፍ፣ አሞራ፣ውሻ የተለያዩ አውሬዎች እንደ ጅብ፣ ተኩላ፣አምበሳ...ወዘተ ሲሆኑ በሞቱ ሰዎች በመመሰል፣ ጭለማንና ጭጋግን በመልበስ የሚደረጉ መገለጦችንም የሚጨምር ነው

ርኩሳን መናፍስትን መለየት በራዕዮች ወይንም በህልም እንደነዚህ ያሉ የክፉው መገለጦችን ከመንፈስ ቅዱስ በመረዳት የሚደረግ ነው

በመገለጥ መናፍስትን ማወቅ የመለየት ፀጋ በሌላቸው ሰዎችም ሊታይ የሚችል ነው ። ይህ አይነት መገለጥ ታዲያ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሊያም ደግሞ ከራሱ ከክፉ ሆኖ ሊመጣ ይችላል

በመጽሐፍ ቅዱሳችን መዝሙረኛው ዳዊት ከእግዚአብሔር ስለሚሰጥ መገለጥ “የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ።” በማለት ይናገራል ። መዝ 13፥4

በሌላ ስፍራም “ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።” ብሎ እግዚአብሔር ለሚፈሩት አስቀድሞ ስለሚሰጠው መገለጥ ይናገራል። መዝ 60፥4

ከክፉው የሆነው መገለጥ በአብዛኛውን ጊዜ ለማስፈራራትና ለማስጨነቅ የሚመመጣ ሲሆን በተጨማሪም በሌሊት ራዕይና በህልም ሰዎችን ለማርከስ ይጠቀምበታል

@intoglory
316 views𝖋𝖙.𝖕𝖆𝖚𝖑, 13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ