Get Mystery Box with random crypto!

#EOTC አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታ | Mereja Tv

#EOTC

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታል ይገኛሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ሆስፒታል በመገኘት ጠይቀዋቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሕመም ምክንያት በሆስፒታል ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትን 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ዛሬ ረፋድ ላይ በሆስፒታል በመገኘት እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዲልክላቸው ጸሎት በማድረስ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በጉብኝቱ ብፁዕ ጠቅላይ ዋና ስራአስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና የልዩ ጽ/ቤት የሥራ ሓላፊዎች ቅዱስነታቸውን በማጀብ መገኘታቸውን የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ዘገባ ያመላክታል።


https://t.me/meraja_tv