Get Mystery Box with random crypto!

የኔ ሴት ስያሜ ከ ፍጥረታት ሁሉ በሃሳብ አልፌ የከፍታን ጣርያ ነካሁት አየሁት ከንፌ ከነገሮች | 💞መንታ ልቦች💞

የኔ ሴት ስያሜ

ከ ፍጥረታት ሁሉ በሃሳብ አልፌ
የከፍታን ጣርያ ነካሁት አየሁት ከንፌ
ከነገሮች ሀሉ ከታላላቅ አዉራ
ትልቅ ነው ክቡር ነው ተብሎ ከምጠራ

በሰማይ በማታ ለሰማዪ ድምቀት
የልቤ ጨረቃ ብላት ምናለበት
ውብናት ድንቅ ፍጥረት በምሽት ጨረቃ
ንጋት ስትተካ ውበቷ ተክቶ ምያበቃ

የጨረቃም ውበቷ አለፈና ለልቱ ስነጋ
ወጣሁና አንጋጠጥኩ ስያሜ ፍለጋ
ልቤም ድንግጥ አለ ፀሃይን አይቼ
ጨረቃንም ሻርኳት በፀሃይ ተክቼ


ፀሃይናት የኔ ሴት ብዬ ሰየምኩና
ጎንበስ ከማለቴ ሸፈናት ደመና
ደመናናት ብዬ ፀሃይን የረታች
ድንቅ ነሽ ውብ ያልኳት ከወዴትስ ገባች


ድንቅ ናቸው ያልኩት ተተካክተው ስያልፉ
ውብ የተባሉት በውቦች ብገፉ
በዝህ ሹምሽረት ቀና ስል ማላጠት
ውቦች ድንቅ ፍጥረት በስሯ ምያልፉባት
የኔ ሴት ሰማይ ናት
Isru H

Join us||➠ @menta_liboch12