Get Mystery Box with random crypto!

የአይኔ እንግዳ በእውነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይ የተመሰረተ ክፍል 11 ሰላም ተ | 💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞

የአይኔ እንግዳ



በእውነተኛ የፍቅር ታሪክ ላይ የተመሰረተ



ክፍል 11



ሰላም ተባባልንና ወደ ክላስ መሄድ ጀመርን።ከዛ ልክ አይን አይኗን ሳያት አልተገናኛችሁም እንዴ አለችኝ አዎ አልኳት በቃ ቦርሳዬን እናስቀምጥና እንፈልገዋለን ብላ ገና ሳትጨርስ ከኮሊደሩጋር ዘሎ ተጠመጠመብኝ ወይኔኔኔኔ እንዴት እንደተደሰትኩ በጣም ነበር እኮ የናፈቀኝ።


ለብዙጊዜያት እንዳልተገናኙ ሰዎች ለብዙ ደቂቃ ተቃቀፍን። ከዛ በጣም ናፍቀሺኛል ከሚባለው በላይ አለኝ ።



እኔም እኮ እሱነው የምልክ አልኩት የቱን ነው የምትይኝ ሲለኝ ሳኩ ። አሁንም አቅፎኛል ምናለ ከዚ እቅፍ ውስጥ እስከዘላለም ባልወጣ አልኩኝ በውስጤ። ከዛም ወደክላስ መሄድ ጀመርን።



የሱክላስ 2ተኛፍሎር ላይ የኔደሞ 3ተኛ ፍሎርላይ ነበር።1ፍሎር ላይ ስንደርስ እኔ እዚጋር የምጠብቀው ሰው አለ አንተሂድ አልኩት። ከዛ አቀፈኝና ሄደ።ነፂ እየጠበቀችኝ ነበር ።



ልክ ስታየኝ እእእእ ምን አወራችሁ አለችኛ ከዛም 1በ1ነገርኳት።ደስ አላት ከተማርን በኀበላ ረፍት አልፎ ምሳ ሰአት ተደወለ።ልክ ከነፂጋር ፎቁን ስንወርድአሁንም ልክ እንደ ጠዋቱ ከየት መጣሳልል እቅፍ አደረገኝ ።


በጣም ሲደጋገመብኝ እየሰለቸኝ መጣ ቦታም አልሰጠሁትም እሺ ኑሀሚንአችን ዛሬ እኮ ጁመአ ነው ከሰአት ልትገቢ ነው እንዴ ሲለኝ አው maths ፈተና አለብኝ ስለው እንደዛ ከሆነግቢ ሲለኝ እሺ አልኩት።


ነገ እኮ ቅዳሜ ነው አንገናኝም ሲለኝ እንድመጣ የሚያደርጉኝን 3ምክንያቶች ንገረኝ ስለው ጊዜ ላገኝሽ ስለፈለኩ አለኝ። አጥጋቢ መልስ መስሎ ስላልታየኝ እንቢ አልኩትና ቻው ብዬው ሄድኩኝ።


ወንድ ልጅ እንገናኝ ና ስልክ ቁጥርሽን ሲለኝ እንደሚያናድደኝ የሚያናድደኝ ነገር የለም የሆነ አለአ የተናኩ የተናኩ ነው የሚመስለኝ በጣም ተናደድኩ ።




ክፍል


አስራ ሁለት


ይቀጥላል







ኑሀሚን
•═••• መንታ ልቦች •••═•
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
@MENTA_LBOCH ||
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━