Get Mystery Box with random crypto!

ከኢድ ሶላት መልስ እቤት ሁለት ረከአ መስገድ ብዙ ሰው የረሳው ሱና | 💎🇸🇦🌹የሰለፊ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው

ከኢድ ሶላት መልስ እቤት ሁለት ረከአ መስገድ


ብዙ ሰው የረሳው ሱና


ከኢድ ሶላት በፊትም ሆነ ከኋላው የሚሰገድ በእድያም ሆነ ቀብልያ የለም። እንዲሁም አዛንም ሆነ ኢቃም አይባልም። የአላህ መልእክተኛ ሜዳ ላይ ወተው ከኢድ ሶላት ዉጪ ምንም አይነት ሶላት አይሰግዱም ነበር። ምናልባት በኡዝር ምክንያት የኢድ ሶላት በሜዳ መስገድ ሳይቻል ቀርቶ መስጅድ ውስጥ ከተሰገደ ተህየተል መስጅድ ሁለት ረከአ ሊሰግድ ይችላል። ከዛ ውጪ ሌላ ምንም አይነት ሶላት የለም።

ነገር ግን የአላህ መልእክተኛ ከኢድ ሶላት መልስ እቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከአ ይሰግዱ እንደነበረ በሶሂህ ሀዲስ ፀድቋል።

አቢ ሰኢድ አላህ መልካም ስራው ይውደድለትና እንዲህ ብሏል። {{የአላህ መልእክተኛ ከኢድ ሶላት በፊት ምንም ነገር አይሰግዱም ነበር። ነገር ግን እቤታቸው ሲመለሱ ሁለት ረከአ ይሰግዱ ነበር።}}

ሶሂህ ኢብኑ ማጃህ (1076)
ሸኽ አልባንይ ሀዲሱ ሀሰን ነው ብለዋል።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru