Get Mystery Box with random crypto!

አላህን 'ዋቃ ጉራቻ' (ጥቁር ጌታ) እያሉ መጥራት በእስልምና የሚፈቀድ አይደለም። የራስን የቆዳ ቀ | ⚘ሱና የኑሕ መርከብ ናት قناة السنة سفينة نوح

አላህን "ዋቃ ጉራቻ" (ጥቁር ጌታ) እያሉ መጥራት በእስልምና የሚፈቀድ አይደለም። የራስን የቆዳ ቀለም ተከትሎ ፈጣሪን ነጭ፣ ቀይ ወይም ጥቁር እያሉ መጥራት መታረም ያለበት ጥፋት ነው። ፈረንጆቹ የጌታ ምስል ነው እያሉ የነጭ ማለትም የፈረንጅ ቅብ ያለው ምስል እንደሚጠቀሙ ይታወቃል። በነጮች ዘረኝነት ከተማረሩ ጥቁሮች ውስጥ ሌላ ፅንፍ በመያዝ ጌታ ጥቁር ነው እስከማለት የደረሱ አሉ። በየትኛውም ዘር ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች በዘር ተጠቅልሎ ከሚመጣ መሰል ብልሹ አስተሳሰብ እራሳቸውንም ወገናቸውንም ሊጠብቁ ይገባል። ኢስላም ከዘራችንም፣ ከቋንቋችንም እንዲያውም ከህይወታችንም በላይ ነውና።
እምነታቸው ለሚገዳቸው ሙስሊሞች ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor