Get Mystery Box with random crypto!

ምናባዊው ደራሲ🤔🧐😳😊

የቴሌግራም ቻናል አርማ menabawiw_felasefa — ምናባዊው ደራሲ🤔🧐😳😊
የቴሌግራም ቻናል አርማ menabawiw_felasefa — ምናባዊው ደራሲ🤔🧐😳😊
የሰርጥ አድራሻ: @menabawiw_felasefa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 314
የሰርጥ መግለጫ

For any idea and comments@Hermon-kira and
@Estif_Habeshawi an

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 20:35:07 ተረት ተረት
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ቀን የጋሽ ጎንጤ አህያ ወደአንበሳ ሄደችና ኮስተር ብላ
(በነገራችን ላይ አህያ ብትኮሳተርም ባትኮሳተርም ያው አህያ ናት)
"እእ... በቃኝ ! መረረኝ! በቤት የሰው ልጆች ጀርባየ እስኪገጠብ
ባሪያ አደረጉኝ ...በውጭ ጅብ እየተከታተለ ነፃነቴን አሳጣኝ
...ቀኘን ይገነጥለኝ ይሆን ሆዴን ይቦተርፈኝ እያልኩ ስጋት!
በመንደሩ ደግሞ ቡሌ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣኝ !
ቡሌ ደሞ ማነው ?
የአያ ይሁኔ አህያ ነዋ!
እሱ ደግሞ ምን ልሁን ነው የሚለው ?
አፈቀርኩሽ እያለ ነው የሚጃጃለው .... ባየኝ ቁጥር እያናፋ እላየ
ላይ መውጣት ነው ... አሳዳሪየ እንኳን ተው አይለውም... የኔ
አንሶት ባሪያ ሁርንጭላ እንድወልድለትኮ ነው...ከነዘር ማንዘሬ
ሊገርደኝ " አንበሳ ከት ብሎ ሳቀና
እንዴት ነው ነገሩ? ...ባሪያ ያደረጉሽንም ጠልተሽ ...የሚበሉሽንም
ጠልተሽ ...የሚበ ...ማለቴ የሚያፈቅሩሽንም ጠልተሽ ምን
ይሻላል?
"ተው እንጅ ጋሽ አንበሶ! በፍቅር ስም ከሚመጣ ጭቆና የለየለት
ባርነት ይሻላል "
አንበሳ ራሱን ነቀነቀና " እንዴት ያለ ፈላስፋ ወጥቶሽ የለም እንዴ"
አለ
"ምንድነው ደሞ እሱ?''
"ወዲህ ነው ተይው...እና ምን ልርዳሽ?" አለ ከአህያ ጆሮ ላይ
ዱቄት እያራገፈ !
እንደማፈር ብላ "ይቅርታ ገና ከወፍጮ ቤት መምጣቴ ነው
ሳልለቃለቅ በቀጥታ መጣሁ ...እና አመጣጤ እንዳንተ ጀግና ሁኘ
በነፃነት መኖር እፈልጋለሁ ...ጉልበት ነው አለኝ ...ጥርስ ነው
ብረት የሚሸርፍ ጥርስ አለኝ ....ጫካ ብገባ እራባለሁ ብየ
አልፈራ የምበላው ሳር ! ምን ይጎድለኛል ብሸፍት? ጀግና እና ነፃ
ለመሆን ምን ይጎድለኛል...? "
አንበሳ አያት ....እንደገና አያት ...በደንብ አያት ....ፍርጥም ያለ
ታፋዋን አየ ...ክትት ያለ ሆዷን አየ ....ውጥር ያለ ደረቷን አየ
...ደልደል ያለ መቀመጫዋን አየ ....እናም አንበሳ የእጅ ሰዓቱን
አየ ....በአንበሳ ሰዓት አቆጣጠር የምሳ ሰዓት ነበር ....በረዢሙ
ተነፈሰና ...
"ሁለት ነገሮች ይጎድሉሻል ...አንድ ልብ ...ሁለተኛው ምክር
የምትጠይቂበትን ሰዓትና ማንን መጠየቅ እንዳለብሽ አለማወቅ
...ቢሆንም ለዘላለም ነፃ ትወጫለሽ!
የዛን ቀን ማታ ጋሽ ጎንጤ መንደር ለመንደር እየዞሩ "ያችን አህያ
አይታችኋል ወይ?" ሲሉ ተሰሙ! በነጋታው "የአያ ጎንጤን አህያ
ጅብ ገነጣጥሏት አደረ" ተባለ !
አንበሳ ጉብታው ላይ ተቀምጦ በወይራ መፋቂያ ጥርሱን እየፋቀ
ርጋፊውን ትፍ ትፍ አለና "የዚህ ሰፈር ጅቦች ምነው
ጠገቡ ? ...
ደሀ አህያ የት ሄዶ ይኑር? ከዚህ በኋላ አንድ አህያ
ቢነካ ውርድ ከራሴ!" አለ! የአንበሳን ሀዘንና መቆርቆር የሰሙ
የመንደሩ አህዮች አንበሳን ወደዱት! በየልባቸውም ሄደው
ሊያመሠግኑት ወሰኑ!

41 viewsĒsŧf ሀበሻዊ, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:13:01 ለልደትህ ይድፋህ!?
(አሌክስ አብርሃም)

ወገኖቸ መልካም ልደት የሚሏችሁን ሁሉ አትመኑ! አንዳንዶች የልደት በግ አልብሰው ቀበሮ ሞት ይልካሉና ከፈቀዳችሁልኝ ልምዴን ላካፍል? አመሠግናለሁ! በጣም እንደምትወደኝ ዘላለም ብኖር ደስ እንደሚላት የነገረችኝ ልጅ ባለፈው አመት ልደቴን ሳከብር በፖስጣ የታሸገ ስጦታ አመጣችልኝ...ፖስታው ባዶ ስለሚመስልና ውስጡ የሆነ ወረቀት ነገር ስለነበር በቃ ዶላር ይሆናል ብየ አሰብኩ... ሰዎች ስጦታ ለመምረጥ ለመግዛት ጊዜ ካጡ ካሹን መስጠት የተለመደ ነገር ነው! (ዶላርን በስሙ ብቻ የምታውቁና ነክታችሁት ለማታውቁ እኔ አሁኑኑ.......አብራራላችኋለሁ! ዶላር /አንዳንዶች ዳላር ይሉታል / እንደምላጭ የሳሳ ግን እንደምላጭ ስለታም የገንዘብ አይነት ነው ! ከአገራችሁ ጋር የተያያዛችሁበትን ጨምሮ የማይቆርጠው እትብት የማይላጨው ፀጋ የለም )
እና ቆንጆ አይኖቿን እያስለመለመች "ክፈተዋ " አለችኝ ፖስታውን ! ስከፍተው ትኬት ነው ... አይኔን ማመን አልቻልኩም ....Go Skydiving on your Birthday...
Jump two miles up with Amazing Views... ይላል! አቻ ትርጉሙ " ለልደት ቀንህ ለምን ሶስት ኪሎሜትር ወደሰማይ ወጥተህ ከአውሮፕላን ዘለህ እንደዱባ አትፈጠፈጥም ለመገፍተሩ እኛ አለንልህ " ማለት ነው ያው በሉት! ትኬቱ ከፍላችሁ ከአውሮፕላን ላይ በዣንጥላ መዝለያ ነው! ለልደቴ ማለት ነው ... እኔ ማለት ነው ....በዣንጥላ ከላይ ከሰማይ ማለት ነው ...




"አታካብዳ ! "
"አካብዳለሁ ! ከፍታ አልወድም አልጋ ራሱ እየራቀብኝ ፍራሽ ላይ ነው የምተኛው" አልኩ! ለነገሩ ክብደት ለመስጠት!
"ብቻህን አይደለህምኮ ...አብሮህ የሚዘል ነጭ አለ ... " ትለኛለች ጭራሽ! እንደው ቢሆን እንኳ "Where Are You From? " እየተባልኩ ከመፈጥፈጥ ...ስር መሰረቴን ከሚያውቅ ከአገሬ ልጅ ጋራ ቁልቁል እያየን "ያ ሜዳ ጎዣምን አይመስልም?" እየተባባልን አብሬ ብፈጠፈጥ አይሻልም ? ሲሆን ሲሆን እንደግብፅ ነገስታት የሆነች ቆንጆ ጋር አስተሳስረው ወደሞቴ ቢልኩኝ ሸጋ ነው!....ነፋስ ከሚያርመሰምሰው ጥቁር ፀጉሯ የሚመነጨውን የሻምፖና ኮንዲሽነር ሽታ ሳምባየን እንደሞላው ቁልቁል እንዲህ ያለም የለ እያልኩ የሆነ ሆኖ በልደት ስጦታ ተጠቅልሎ ከሚመጣ ሞት ይጠብቃችሁ! እኔን አልፎኝ እዚህ ደርሻለሁ


58 viewsĒsŧf ሀበሻዊ, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 02:29:01 #ላባቴ

የማትንበረከክ
የማትርመጠመጥ
ከባለጌ ዙፋን
በርጩማ የማትመርጥ፡፡
ያለ ባህር ሰርጓጅ ያለ ሙሴ በትር
በመታገስ ብቻ ፣ባህር የምትመትር፡፡

ካዘልከኝ ጀምሮ ፣እንኮኮ ጫንቃህ ላይ
ከፍታውን እንጅ፣ ዝቅታውን እንዳላይ
እንደ ንሥር መጠቅሁ፣ እንደ ምስራቅ በራሁ
የገዛ ክንፎቼን ፣እንደ ዳንቴል ሠራሁ፡፡
በርግጥ ደሀ ነበርህ…
ከሰላምታ በቀር የማታበረክት
ነጠላህ መናኛ፣ሰውነትህ የክት
በርግጥ ድሀ ነበርህ
የነጣህ፣ የጠራህ
ከጦርሜዳ ይልቅ ገበያ ሚያስፈራህ፡፡
ቤሳ ባታወርሰኝ አወረስከኝ ትግል
የትም እንዳይጥለኝ ፣ሕይወት እንደ ፈንግል፡፡
አባየ ብርሀን
አባ የምስራቅ በር
ገመና ሸሻጊ፣እንደ ካባ ገበር
አባቴ ባትሆን ይጸጽተኝ ነበር፡፡

በእውቀቱ ስዩም
77 viewsĒsŧf ሀበሻዊ, 23:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 23:25:05
ወጣቱ ዶክተር ቢሮውን እንደከፈተ ዘና ብሎ ወንበሩ ላይ ተቀምጧል፡፡ ፀሀፊው አንድ ሰው መግባት እንደሚፈልግ ስትነገረው እንድታስገባው ነገራት፡፡

ተንደላቆ ተቀምጦ የነበረው ዶክተር ወዳው ስራ የበዛበት ለመምሰል መራወጥ ጀመረ፡፡ ወዳው የቢሮ ስልኩን አንስቶ "አዎ ልክ ነው፤ ያው ክፍያው 2000 ብር ነው፤ 2:10 ላይ እጠብቅሀለው፤ አይ አሁን ቢዚ ነኝ በኀላ" እያለ መቀባጠር ጀመረ፡፡

ልክ ስልኩን እንደዘጋ ሁሉን ሲያዳምጥ ወደ ነበረው እንግዳ ዞሮ "ምን ልርዳክ?" ብሎ ጠየቀ፡፡

በፀሀፊዋ እንዲገባ የተነገረው ሰውም "አይ የተበላሸውን የቢሮክን የስልክ መስመር ልሰራ ነው የመጣውት" አለው፡፡

#ጭብጥ ፡- ያልሆንከውን መስለክ ለመታየት አትሩጥ ፊልም ሰሪ ሚደነቀውም ሆነ የሚወደደው ፊልሙ እስኪያልቅ ብቻ ነው፡፡

በሰዎች ለመወደድ፤ ዝናን ለማትረፍ ስትል ጭምብል ለብሰክ አትዙር፡፡ ተዋናይ መሆንክ የታወቀ ዕለት የሀፍረት ካባን ትለብሳለክ። ስለዚህ ከቦታና ከሁኔታዎች ጋር አብረክ አትለዋወጥ፡፡


83 viewsĒsŧf ሀበሻዊ, 20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 22:20:08 # ፍጥነት_እና_ነፃነት

አልጋ ባልጋ ሆኖ…
የጥንቸሎች ፍጥነት፤ ፍጥነት ከተባለ
በኤሊዎች ጫንቃ……..
እራሱን ያልቻለ፤ ግዙፍ ድንጋይ አለ፡፡
ያንን ግዙፍ ድንጋይ …
ከኤሊ ጫንቃ ላይ፤ ላፍታ ቢነሳላት
ከጥንቸሎች ፍጥነት...
አስር እጅ የሚሻል፤ በቂ ፍጥነት አላት፡፡
ያንን ግዙፍ ድንጋይ…
ለዘመናት ቀርቶ፤
ለሰዓታት ያህል፤ ጥንቸል ብትሸከም
መሮጡ ይቅርና ፤
መራመድ አትችልም፤ ነፃ ባልሆነ ዓለም፡፡
ፍትህ በጎደለው፤ ነፃ ባልሆነ ሀገር
ድንጋይ ተሸክሞ ፤
የፈጠነ የለም፤ ከኤሊ በስተቀር!!
ፍትህ በሞላበት፤ ነፃ በሆነ ሀገር
ይቻላል ቀላል ነው፤ ክንፍ አውጥቶ መብረር!!
* * * *
# ገጣሚ_በላይ_በቀለ_ወያ
179 viewsĒsŧf ሀበሻዊ, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 22:27:01 ሙላ ነስሩዲን አንድ እጅግ አስቸጋሪ ፣ ተናካሽ አህያ እና ተራጋጭ አህያውን ለመሸጥ ገበያ ይዞት ወጣ። ወደሉ አህያ ማንንም ሊያሳቀርብ አልቻለም። የተጠጋውን ሁሉ ይናከሳል ይራገጣል።

" እውን ሙላ ይህን አስቸጋሪ አህያ እሸጣለሁ ፣ ሰው ይገዛኛል ብለህ ነው ግን ገበያ ይዘኸው የወጣኸው ?" አሉት አንድ ገበያው ውስጥ ያገኙት የሚያውቁት ሰው።

" ፈፅሞ ! ፈፅሞ ልሸጠው አይደለም ! ከምን አይነት አስቸጋሪ አህያ ጋር እየኖርኩ እንዳለሁ ዓለም እንዲያውቅልኝ ብዬ እንጂ ....”
111 viewsĒsŧf ሀበሻዊ, 19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 21:07:01 ዝቅ ብለኽ እንድታልፍ ሚያስገድድኽ ሁኔታ ላይ አለማጎንበስ ትርፉ በዛ ነገር መመታትና መጎዳት ነው።

146 viewsĒsŧf ሀበሻዊ, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:47:01 የነብር ጅራት ...
።።።።።።።።።።።።

ወድጄሽ ... ወድጄሽ
ወድጄሽ ... ወድጄሽ
እንደገና ጀመርኩ ፤ 'ሀ' ብየ መውደዴን
ተረት የሚቀይር ፤ ተመልከችው ጉዴን
'' ሲኖሩ ሲኖሩ ሞቱ '' ሲል ተረቱ ፣
ኑሬ ኑሬ ኑሬ - እንዳዲስ ተወለድኩ እኔ ያንቺ ገልቱ ፣
እንኳንም ተወለድኩ
እንኳን ሳትኩኝ አቅሌን
እንኳን አፀናሁት .. ላንቺ ያልኩት ቃሌን
እንደ ነብር ጅራት ስምሽን አንቄ
እንደ ርሃብ ስንቅ ፍቅርሽን ደብቄ
ያ'ሽሙር የተረቱን ስንክሳራ ሳልፈራ
እንቅ ፍቅርሽ እንደ ነብረሰ ጭራ
ሙጭጭ ካንች ጋራ
ጥብቅ !!
'ጅልና ወረቀት
የያዘውን አይለቅ '
ብለው ቢሞግቱሽ
አትከራከሪ ሀሰትም የለበት ፣
ወረቀት ልቤ ላይ
ጅል ፍቅርሽ ነውና የተከተበበት ፤!!
እንቅ እኔ ጅሉ ...
እንቅ እኔ ሌጣው እኔ ወረቀቱ ፣
ያዝ ለቀቅ የለም ለፍቅር ሲሞቱ ፤
አሰንቅ !!

#አሌክስ አብርሃም

150 viewsĒsŧf, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 21:49:01 ልክፍት
(በሚኑ የተፃፈ)

የምሰራው በአንዱ የሚድሮክ ድርጅት ውስጥ በግዥ ሰራተኛ ነው። በሶስት ዘርፍ ላይ ዲግሪ አሉኝ በአካውንቲንግ፣ በቢዝነስ እና በIT። ከዚህ በፊት አብረን የምንሰራ የነበረና IT መማሬን የሚያውቅ ሰው ችግር ገጥሞት መፍትሄ ፍለጋ እኔ ጋር ይደውላል። ይሄ ዲግሪ መቼም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ነው ያመዘነበኝ። አብዛኛውም ሰውም የ IT ትምህርት ምንምን እንደሚያካትት አያውቅም። በዚያ ላይ በየጊዜው የሚቀያየር መሆኑን፣ ካልተሰራበት እንደሚረሳ፤ ትንሿ የ ኦፊስ አፕልኬሽን እንኳን ዘመናዊ በሆነ ቁጥር ግር እንደሚል ይረሱታል። እና የተለያዩ ሰዎች በአካልም በስልክም እየደወሉ ኮምፒተሬ እንደዚህ ሆነብኝ ምን ላድርገው ያኛው እንደዚያ ሆነ ምንድነው የሚሉ ጥያቄዎች ይቀርባሉ። እኔስ መቼስ አዋቂ ተብዬ እላይ ተክቤ ተሰቅዬ ተጠይቄ ዝቅ ብዬ አይ አላውቀውም እንዴት እላለሁ! ከየትም ከየትም ብዬ የተጠየኩትን በከፊልና በሙሉ ስመልስ እዚህ ደረስኩ። አሁን ላይ አይን ፍጥጥ ጥርስ ግጥጥ የሚያደርግ ጥያቄ መጣብኝ
እሱ......ሄሎ ሚኑ እንዴት ነሽ ሰላም ቤተሰብ ደህና ነው?
እኔ.... ያው እንደሚታወቀው ድሮ የሚታወቅ ሰው በአካልም ሲገኝ ሆነ በስልክ ደስ የሚል ስሜት አለውና በፈገግታ እንዴት ነህ ብዬ ሞቅ አድርጌ ሰላም አልኩኝ
እሱ..... ምን መሰለሽ ሚኑ ኮምፕተሬ ...ሲል ጠላታችሁ ክዉ ይበል ቀልቤ ተገፈፈ እሱ ስለኮምፒዉተሩ ችግር ያወራል እኔስ ... ልዝጋውና ስልኬ ባትሪ ዘጋ ልበል? ዝም ብዬ በኔትወርክ አሳብቤ አይሰማም ሀሎ ሀሎ ልበል? ወይስ ... ብዬ ሳስብ ቆየሁና አይ ግዴለም ምንአልባትም ቀላል ሊሆን ይችላል ልስማው ብዬ ቀልቤን ሰብሰብ አድርጌ ማዳመጥ ስጀምር ....." ..... ይሄኛው ችግር አልበቃ ብሎት x ብዬ ስፅፍ zን ይፅፋል y ስነካ xን ይፅፋል እና ምን ሆኖ ነው?" አለኝ። ይሄኛዉ ችግር አልበቃ ብሎት የተባሉት ምን እንደሆኑ እግዜር ይወቃቸው። የፊድልላቱንም መቀያየር ምክንያት ምን እንደሆነ እኔም አላውቀውም ። ግን ያው መፍትሄ አላጣም አይደል አሰብኩኝና ይሄ ነገር ምን መሰለህ አልኩኝ እ ... ምን ሆኖ ነው አለኝ በጉጉት ችግሩ አውቄዉ መፍትሄ ልሰጠው የተዘጋጀሁ መስሎት። አይ አይዞህ ብዙ ከባድ አይደለም ቀላል ነው .... እ.... ልክፍት ነው አልኩኝ።
እሱ .... በድንጋጤ እእእ አለ
እኔ .... አዎ ልክፍት ነው ሁለት ሰባት አስጠምቀው ይለቀዋል አልኩኝኝ
እሱ..... በድንጋጤ ኮምፒውተሩን? አለ
እኔ..... አዎ ኮምፒውተሩን እንዲያውም ሶስት ሰባት አድርገው ሰባቴ ጮሆ ይለቀዋል አልኩት
እሱ..... ያማታል እንዴ ብሎ ስልኩን ዘጋው። ይሄ ነገር ስልኩንም አብሮ ሊያስጠምቀው ይሆን እንዴ?
133 viewsĒsŧf, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 21:09:01 እነሙላ ነስሩዲን ሰፈር ባለ አንድ ሻይ ቤት ውስጥ አንድ የሩቅ ሐገር ሰው ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ ነበር፡፡ ሻይ ቤቷ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በሰውዬው ለቅሶ ልቡ ተነክቷል፡፡

ከሰውዬው ጥቂት ራቅ ብሎ ሙላ ነስሩዲን ተቀምጧል፡፡

ሻይ ቤቷ ውስጥ ካሉት ሰዎች አንዱ ወደ ሙላ ነስሩዲን ቀረብ አለና፣ “ምን ብታረዳው ነው ግን እንዲህ የሚያለቅሰው…”

“ምን ባክህ.... ለክረምት ያከማቸው የግመሎቹ ድርቆሽ እንዳለ በእሳት መቃጠሉን ነግሬው እኮ ነው እንዲህ የሚነፋረቀው…”

“ውይይይ ሲያሳዝን…” አለ ሰውዬው ከንፈሩን እየመጠጠ፡፡

“ለነገሩ አታስብ ... አሁን አንድ ቆንጆ ወሬ ስነግረው ማንባቱን ያቆም የለ…” አለ ሙላ፡፡
“ጎሽ እንደዚያ ከሆነማ፡፡ ለመሆኑ ምንድነው ጥሩው ዜና?”

"ህ … ግመሎቹ ሁሉ እኮ በወረርሽኝ አልቀዋል ! ይህን ዜና ስነግረው ማንባቱን እንደሚያቆም እርግጠኛ ነኝ ... ግመሎቹ ካለቁ ድርቆሹ ምን ያደርግለታል።

115 viewsĒsŧf, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ