Get Mystery Box with random crypto!

#_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ_በወይን_አምባ_ማርያም! #ሰኔ_30_አርብ_የመጥምቁ_ዮሐንስ_የልደት | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ_በወይን_አምባ_ማርያም!

#ሰኔ_30_አርብ_የመጥምቁ_ዮሐንስ_የልደት_በዓል_ይከበራል!

#_ሰኔ_30_ወይን_አምባ_ማርያም_እንገናኝ!

"በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል" ሉቃ 1፥14

#_ሼር_በማድረግ_ለመጥምቁ_ዮሐንስ_ወዳጆች_አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች አርብ ሰኔ 30 ቀን በወይን አምባ ማርያም የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። በዚህም የተአምረኛው ብዙዎቹን ከጡት፣ ከአጥንት፣ ከማህጸን ካንሰርና ከተለያዩ በሽታዎች እየፈወሰ ያለው የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ታቦት ወጥቶ ሕዝቡን ይባርካል።

የመጥምቁ ዮሐንስ ታቦቱ ወደ መንበረ ክብሩ ከገባ በኃላ ሰፊ ዝክር አለ። ጌታችን "ዝክርህን የቀመሰ ዘሩን ቆጥሬ እስከ 55 ትውልድ እምርልሃለሁ" ስለላው መጥታችሁ ከበዓሉ ረድኤትን፣ ከዝክሩ ቃል- ኪዳንና በረከትን ተቀበሉ፣ 55 ትውልዳችሁን አስምሩ።

"በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል" "ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም" /ማቴ 11፥11/ የተባለለት ቅዱስ ዮሐንስ የተወለደው ሰኔ 30 ስለሆነ መጥተን በዓሉን አክብረን፣ እንደ ቃሉ ደስ ይበለን።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ተሳፍራችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በር ላይ ያወርዳቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ሰኔ 26/10/15 ዓ.ም
ኒዮርክ አሜሪካ