Get Mystery Box with random crypto!

#_አሜሪካ_በሰላም_ገብቻለሁ! ተወዳጆች ሆይ በአሜሪካ ለሁለተኛ ጊዜ ለአንድ ወር የጥምቀት፣ የ | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_አሜሪካ_በሰላም_ገብቻለሁ!

ተወዳጆች ሆይ በአሜሪካ ለሁለተኛ ጊዜ ለአንድ ወር የጥምቀት፣ የቅብዓ ቅዱስ፣ የንስሐ እና የቄደር ጥምቀት ለሚኖረኝ አገልግሎት በወለላይቱ እመቤት ጸሎት በሰላም አሜሪካ ገብቻለሁ።

ወዳጆቼ አሜሪካ ብሆንም በወይን አምባ ማርያም እሑድ ግንቦት 27 የሚኖረን የንስሐ እና የቄደር አገልግሎት እንደተጠበቀ ነው። እኔ ባልኖርም አገልግሎቱን እንደ እኔ፣ እንደውም ከእኔ በተሻለ የደብሩ ካህናት ስለሚሰጧችሁ እንዳትቀሩ! እሑድ ግንቦት 27 ወይን አምባ ማርያም ጾመ ሐዋርያትን በንስሐ ለመቀበል ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ!

ግንቦት-25-9-2015 ዓ.ም

አሜሪካ ቺካጎ!