Get Mystery Box with random crypto!

#_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ_በወይን_አምባ_ማርያም! #_ሰኞ_ግንቦት_21_ቀን! ሼር በማድረግ | ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

#_ታላቅ_የንግሥ_በዓል_ጥሪ_በወይን_አምባ_ማርያም!

#_ሰኞ_ግንቦት_21_ቀን!

ሼር በማድረግ ለእመቤታችን ልጆች አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች ሰኞ ግንቦት 21 ቀን በወይን አምባ ማርያም የእመቤታችን በደብረ ምጥማቅ የመገለጧ ዓመታዊ በዓል እንደተለመደው በደማቅ ሁኔታ ይከበራል። በዚህ ቀን የእመቤታችን እና የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ታቦታት ወጥተው ሕዝቡን ይባርካሉ።

የእመቤታችን እና የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው ከገቡ በኋላ ሰፊ የእመቤታችን ዝክር አለ። ስለዚህ መጥታችሁ ከበዓሉ ረድኤትን፣ ከጥምቀቱ ፈውስን፣ ከዝክሩ በረከትን ተቀበሉ።

#_የትራንስፖርት_መምጫው ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ተሳፍራችሁ ቤተ ክርስቲያኗ በር ላይ ያወርዳቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

ግንቦት /17/15 ዓ.ም
አዲስ አበባ