Get Mystery Box with random crypto!

“ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “

የቴሌግራም ቻናል አርማ memehir_girma — “ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “
የቴሌግራም ቻናል አርማ memehir_girma — “ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “
የሰርጥ አድራሻ: @memehir_girma
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.67K
የሰርጥ መግለጫ

<< ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል >> ወደ ቲቶ 2 ፤ 12-13

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-09 23:32:32 https://vm.tiktok.com/ZM2xUxSDd
2.8K views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-09 23:20:41 የእግዚአብሔርን መንግስት ከተናገርን በኋላ ድዉዮች ጋር መሄድ ነው፡፡ አይ እንዲህ እይነት ስጦታ አልተሰጠኝም ልትል ትችላለህ፡፡ እግዚአብሔር ይሄንን ስጦታ ላንተ ለመስጠት ላንተ የተለየ ፎርሙላ የለዉም፡፡ ብቻ በቅንነትና በቦጎነት፣ በእምነት ተስፋ እንድትራመድ ውስጥህን ከኃያል እግዚአብሔር ጋር እንድታያይዝ እንጂ ወደ ድዉዮችና ወደ ተቸገሩት እንዳትሄድ የሚከለክል ጸጋ እግዚአብሔር አይሰጥም፡፡ ስለዚህ አገልጋይ ማን ነው? የሚለው ጥያቄ ወደ ድዉዮች የሚሄድ ነው አገልጋይ፡፡ ይሄንን እውነት ልነግርህ እወዳለው፡፡ ከድዉዮች ጋር የሚውል ጌታን አየህ እንጂ ከባለጸጎች የሚውል ሃብታሞችንና ቱጃሮችን ባለስልጣኖችን እየመረጠ አብሯቸው የሚቆምና አብሯቸው ፎቶ ግራፍ የሚነሳ፣ አብሯቸው የሚበላና አብሯቸው የአነጋገር ቅላፄ የሚማር አይደለም አገልጋይ፡፡ አገልጋይ ክርስቶስን የሚናገር ነው፣ ከክርስቶስ የሚማር ነው፣ ወደ ድዉዮች የሚሄድ ነው፡፡

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከ መልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
02/11 /2015 ዓ.ም
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
2.6K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-09 23:20:41 በማቴዎስ ወንጌል 10፡6 ላይ ‹‹ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ›› ይላል፡፡ የጠፉ በጎች፣ የታሰሩ በጎች፣ መዋያና መድረሻቸውን ያጡ በጎች፣ የሚበሉትንና የሚጠጡትን ያጡ በጎች አሉ፣ የታመሙ የወደቁ በጎች አሉ፣ የተጨነቁ ባለቤት ያጡ በጎች አሉ፡፡ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ፡፡ ይሄ ነው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአገልጋዮች የሰጠው መመርያ፡፡ ይሄ ነው ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ፡፡
.
አንድ አገልጋይ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ከተናገረ በኋላ የጠፉበትን መንገድ ተከትሎ መፈለግ ነው፡፡ መሄድ ነው፡፡ ማቋረጥ፣ መቆም፣ መተኛት፣ መጋደም ማለት አይደለም፡፡ መሄድ ማለት መሄድ ነው፣ መራመድ ነው፣ መውጣት መውረድ ነው፡፡ ደግሞ ስንወጣ ስንወርድ የጠፉትን በመፈለግ ነው፡፡ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ፡፡ ዛሬ ብዙ ምዕመናን በህይወት ጠፍቷል፣ በኑሮ ጠፍቷል፣ በአስተሳሰብ ጠፍቷል፡፡ እንደጠፉ የማንቆጥር ነጭ ነጠላና ቀሚስ ለብሰው ቤተ ክርስትያን መገኘታቸው የጠፉ በጎች አለመሆናቸውን ማረጋገጫ አይደለም፡፡ ቤተ መቅደሱ ሞልቶ ከውስጥ እስከ ውጪ ድረስ የቆሙት ሰዎች በእውነት ውስጣቸው ጠፍቷው ግራ ተጋብተው በዕለት ኑሯቸው ውስጥ እምባ ሳያቋርጥ በአስተሳሰባቸውና በአካሄዳቸው፣ በታሪካቸው ውስጥ አንድም አይነት ስኬት ሳይኖር ነጭ ነጠላ ለብሰው በቤተ እግዚአብሔር ሲቆሙ እናንተ ብሩካን፣ እናንተ ቅዱሳን የሚባሉ ብቻ አይደሉም፡፡ በእውነት በውስጣቸው ያለውን ችግር እንዲያወጡና እንዲናገሩት ሸክማቸውን እንዲቀልላቸው ውስጣቸውን የጎዳዉን ኃይል ለማየት ወደ ጠፋው በኩል ለመሰለፍ ከእግዚአብሔር አቅም ያስፈልገናል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም የራሳችን በጎ ሕሊናና ንፁሕ ባሕሪ በአገልግሎታችን ላይ የሚያደርሰውንና የፈፀምነውን አካሄድ በመንፈስ ቅዱስ መመራትን ሁሉ ይጠይቃል፡፡
.
ወደ ጠፉት በጎች እኮ ግድ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ታድያ የጠፉ ያልመሰሉን ግን በደጁ ውስጥ የቆሙ፤ በጥሩ ንጹህ አለባበስ ሁሉ ግዜ የሚያስቀድሱ ምንም ችግር የሌለባቸው መስሎ የሚታየን ከሆነ ወደ ጠፉት ሕሊናና ልቦና ውስጥ ያልደረስን ከመሆኑ የተነሳ ዝም ብለን ጮሆንባቸው ውስጣቸውን ሳናገኝ በህይወታቸው ውስጥ ሁሉም ጎዶሎነት ሊያመጣ የሚችለውን ኃይል ሳንነካው ዝም ብለን በቃላት ተስፋ ብቻ የምሸኛቸው ከሆነ በእውነት ነገ ከነገ ወድያ ጣታቸውን በእናንተ ላይ ቀስረው አንዲህ አይነቶች ናቸው እኮ የኛ አገልጋዮች ከመባል አታመልጡም፡፡ ከመባልም አትድኑም፡፡ ስለዚህ ክርስቶስን በምናይበት ግዜ የክርስቶስን ትንሳኤ፣ የክርስቶስን መሰቀል፣ የክርስቶስን ጉዞ፣ የክርስቶስን መደብደብ መቸንከርንና መገረፍ፣ የዕሾክ አክሊል መሸከም እናም በመጨረሻም ወደ ሞት ጥላ ወስደው በመስቀል ላይ ሰቅለው ወደ መቃብር መወርወር እነዚህ ሁሉ ሂደቶች አንድ ትልቅ ነገር እንደሆነ አስታውስ፡፡ ያ ትልቅ ነገር ዛሬ በጎችን አርደን፣ ፍሪዳ ጥለን፣ ወይን ጠጅ ጠምቀን ክርስቶስ ተነሳ እያልን የምንደሰትበት ትንሳኤ ሚስጢሩ ወደ ጠፉት በጎች ከመሄድ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አትዘንጉት ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ ነው የሚለው፡፡ የጠፉት በጎች የመጣ ጌታ ዉስጣቸውን ፈልጎ ነው፡፡
.
አየህ የእግዚአብዘሔር ክብር፣ የእግዚአብሔር ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ሞጎስ ከውስጣቸው ከጠፋቸው ጋር መገናኘት ነው፡፡ ኑሮ፣ ግዜ፣ ዘመን ከከዳቸው ጋራ መሄድ ነው፡፡ ወደ ጠፉት በጎች ሄዱ፡፡ ዛሬ እኛ ወደ ጠፉት በጎች ከመሄድ ይልቅ እንደገና መንፈሳዊ ፅናት ፈልገው ወደ ቤተ እግዚአብሔር የመጡትንም የምናባርር ነን፡፡ የአገልጋይነት የመንፈሳዊ ህይወት ዓላማ በተለያየ ዓይነት ፈተና ውስጥ ወድቋል፡፡ ወደ ጠፉት በጎች ለመሄድ ብዙ መድከምን የሚጠይቅ ስለሆነ እና ያንን ድካም አንፈልገዉም፡፡ ወደ ጠፉት በጎች ጋር ለመድረስ ብዙ እንቅፋቶች አሉ፡፡ እዛ ጋር መሄድ አያስፈልገንም ብለን ነው የምንገምተው፡፡ የጠፉት በጎች እንዲመጡ እንጂ እኛ እንድንፈልጋቸው ዛሬ በህይወታችን አቋም እይደለም፡፡
.
የጠፉት በጎች ወዴት ሄይዱ?፡፡ ባዝነው ተኩላና አውሬ እየበላቸው፤ በክፉ መናፍሰት አደጋ ውስጥ ወድቀው እያለ ዛሬ በእነሱ ህይወት ላይ እናሾፍበታለን፡፡ ወደ ጠፉት በጎች መሄድ ስንጀምር የሚከተሉት መንፈሳዊ ኃይል ከጎናችን ይሆናሉ፡፡ ድዉዮች ይፈወሳሉ፣ ሙታኖች ይነሳሉ፣ ለምፃሞች ይነሳሉ፣ አጋንንት የገዝዋቸው ሰዎች ከአጋንንት አገዛዝ ነፃ ይወጣሉ፡፡ አገልጋይ ይሄ ነው አየህ፡፡ ይህንን በሚመለከት መጽሐፍ ቅዱስ ሲነግረን ሰማያዊ ኃይልን የተረከቡ የሰማይ ስልጣን የሚመሩ እንዲህ የሚል ቃል የማቴዎስ ወንጌል 10፡8 ላይ ታነባላችሁ፡፡ ‹‹ድዉዮችን ፈውሱ›› ይላል፡፡ ግዜ ዘመን ድዉይ ያደረጋቸው፣ ስልጣን ማዕርግ ድዉይ ያደረጋቸው፣ ሃብት ገንዘብ ድዉይ ያደረጋቸው፣ ድህነት መከራ ድዉይ ያደረጋቸው ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህን ማየት የማትፈልግ ከሆነ ስለ መንግስተ ሰማያት መቅረብና ወደ ጠፉት በጎች ስለመሄድ ጉዳይ ዕድልህ አይደለም፡፡ ስለዚህ እንዲሁ በሰማያዊ ቦታና ስፍራ ላይ በመቆም ብቻ የእግዚአብሔርን መንግስት እናገለግላለን ወይ ብሎ መጠየቅ በእውነት ሌላው ትልቅ ልናስብበት የሚገባ እውነት ነው፡፡ ቃሉ ድዉዮችን ፈውሱ ነው፡፡
.
ዛሬ ብዙዎቻችን ነው ከድዉዮች ነው የምንሸሸው፡፡ ብዙ ነገር አለና፡፡ ከተቸገሩት ጎን አንቆምም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ግን ከተቸገሩት ጎን መቆም ነው፡፡ ዛሬ ከተቸገረው ጎን የሚቆሙ ጥቂትም ቢሆን የእግዚአብሔር ጸጋ ያላቸው ከሆነ፣ ድዉዮችን የሚፈውሱ ከሆነ የምንናገራቸውና ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናወጣቸው ጥቅሶች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ለመቃወም ስንል ብቻ፡፡ አንዳንዶቹም እንደዚህ ነው መንፈስን ሁሉ አትመኑ ብለዋል፣ በዘመኑ መጨረሻ በክፉ በመናፍስት የሚሄዱ ብዙዎች አሉ ብለን አሁን ይህንን ቃል የምንጠቀመው ድዉዮችን ለሚፈውሱ ባለጸጋዎች አካሄዳቸውንና መንፈሳዊ ገዟቸው ለማጨለም እንጂ በእውነት መንፈስን ለይተን አይደለም፡፡ ወደ ድዉዮች የሚሄዱትን መንገዳቸውን ለማበላሸት የተለያየ ስም በመስጠት የፈውስ አገልግሎታቸውን አጭበርባሪ ለማድረግና ውሸታም ለማድረግ ለምናደርጋቸው ሩጫዎች በእውነት ላይ ያለውን ኃይልና ስልጣን ከመዘንጋትም በላይ የክፉ መናፍስት የአኗኗር የሰው ልጆች ህይወት እንዲያጠቃ ተጨማሪ አገልጋይ የሆነ ቋንቋ ያለን አገልጋዮች ሆነናል፡፡
.
ታድያ እምነት የቱ ጋር ነው?፣ ኃይማኖቱ የቱ ጋር ነው ስልጣኑ?፡፡ መድረክ በጥሩ ቅላፄና ድምፅ፣ ቆንጆ አለባበስና እጅግ በጣም በደመቀና በሚያበራ ፊት ሆኖ ነው መቆም ነው እንዴ የኃይማኖት አገልግሎት?፡፡ እንዴት ነው ነገሩ?፡፡ ልብሱ አያስፈልገንም ማለቴ አይደለም፣ ሰውነታችን ከተመቸንም አይመቸን ማለቴ አይደለም ግን ሰውነታቸው ያልተመቻቸው ሚስኪኖችና ድዉዮች፣ ዘመና ግዜ የጣላቸው፣ ወቅትና ሰዓት የረገጣቸው፣ ዲያብሎስ የተጫወተባቸው ድዉዮች ጋር ማን ይሂድ?፡፡ መናፈቁ ይሂድ?፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? ማን ይሂድ፣ ወደነዚህ ማን ይጠጋ?፡፡ እንዴ ሁሉግዜ ሃብት ወዳላቸው፣ ግዜና ዘመን ወደ ተመቻቸው ብቻ የምንሄድ ከሆነ ይሄ የእግዚአብሔር የክርስቶስ ዓላማ እይደለም፡፡ የመስቀሉ፣ የትንሳኤው፣ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋና በረከት መግለጫ አይደለም፡፡
.
2.2K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-09 23:19:37
<< የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል። >> 1ኛ ቆሮንቶስ 12 ፣ 4፤7

በጎፋ መብራት ኃይል ደብረመዊዕ ቅዱስ መርቆሬዮስና እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ እና በመልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ የወንጌል ትምህርትና የፀበል አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል ።

********************************************
(ሐምሌ 2 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፥ኢትዮጵያ)

ጌታ ባከበራት በእለተ ሰንበት ህያው በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ብዙዎች ነፍሳት ታድሰዋል በኃያሉ አምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ብዙዎች ከጠላት እስራት ተፈተዋል።

በአገልግሎታችን ብዙዎች ከጭንቀታቸው አረፈው ስር ሰዶ በስውር ከያዛቸው እና ካሰቃያቸው ጠላት ተላቀው እንደ ማየት በጎ ህሊና ላለው የሚያስደስት ነገር የለም

የቅዱስ እረኛችን በጎች ከክፉ መናፍስት ተላቀው የወንጌሉ ብርሀን በህይወታቸው አብርቶ ተስፋቸው ለምልሞ ለሌሎች ተስፋ ሆነው ማየት ምንኛ ልብን በሀሴት ይሞላል

ውድ ክርስቲያኖች ቀደምት አባቶቻችን ባቀጣጠሉልን የወንጌል ችቦ ህያው የሆነችውን መንግስተ ሰማያት እየሰበክን ለትውልድ ለማስቀጠል ዛሬም እንደድሮው ታጥቀን ተነስተናል
እናንተም በቁርጥ ሀሳብ በተማራችሁት መሰረት የእግዚአብሔር ን መንግስት እያሰባችሁ በሕይወታችሁ ተሰውሮ እያደባ ከሚያጠቃችሁ ጠላት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየተፋለማችሁ በወንድማማች መዋደድ እየተዋደዳችሁ እንትኖሩ ምክራችን ነው
2.1K views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 15:19:28
3.7K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 15:19:23 ከብዙ ሥፍራ ብዙ ድንንጋይ ተወርውሮብናል፤
እኛ ግን የተወረወረብንን ድንጋይ ሰብስን ለነፍሳችን የሚሆኑ ጥሩ ጥሩ ሕንፃዎችን ገንብተንበታል።

በየቀኑም እየተሳሉ የሚወረወሩብን የጦር እና የገጀራ ቁጥሮች በርካታ ናቸው፤
እኛ ግን የሚወረወርብንን ጦር እና ገጀራ ወደ ማረሻ እና ወደ ማጭድ ቀይረን ልማት ላይ ነን።

በሚሳደቡን ሰዎች ስድብ አንድም ቀን ተበሳጭተን አናውቅም፤
ይልቁንስ ከሚሰድቡን ሰዎች ስድብ ውስጥ ምክርን እያወጣን ስድቡን ለምክር ተጠቅመንበታል።

ጉልበተኞቹ ገፍትረው ቢጥሉንም፤
እኛ ግን መውደቃችን አጋጣሚ ሆኖልን ከወደቅንበት ሥፍራ ብዙ ነፍሳትን ይዘን ተነሥተናል።

ጳውሎስ እና ሲላስም የወኅኒ ቤቱን ጠባቂ ከነቤተሰቦቹ አጥምቀው የሥላሴን ልጅነት ያጎናፀፉት እጅ እና እግራቸው ታሥሮ ወደ ወኅኒ ቤት ተገፍትረው ተጥለው በነበሩበት ወቅት ነው።
የሐዋርያት ሥራ 16

ስለዚህ ወዳጄ!
አንተም ተገፍትረህ ስትጣል ምናልባት እግዚአብሔር ባወቀ ከወደቅህበት ሥፍራ የምታነሣቸው በርካታ ነፍሳት ይኖራሉ እና ችግርህን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመህ መልካም ሥራን እየሠራህ ለችግርህ ችግር ሁንበት እንጂ ዝም ብለህ በማጉረምረም ጊዜህን አታበላሽ!

ደግሞም በሐዋርያት ዘመን ለክርስትናው መስፋፋት
የነ እስጢፋኖስ መገደል ትልቅ ሚና እንደነበረው አትርሳ!
የእስጢፋኖስ መገደል ለአይሁድ በየሀገሩ መበትን ምክንያት ሆነ፤
የአይሁድ መበተን ደግሞ ለክርስትናው መስፋፋት መልካም አጋጣሚን ፈጠረ።
የሐዋርያት ሥራ 8 ፤ 1

ስለዚህ በክርስትና ሕይወት ውስጥ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚ ገልብጦ ሥራ ላይ ማዋል እንጂ ማለቃቀስ ብሎ ነገር የለም ወዳጄ!

ስትሰደድ በዚያ በተሰደድክበት ሥፍራ በወንጌሉ ቃል ልታጽናናቸው የሚገባ በርካታ ስደተኞች ይኖራሉ።

ስትታሠርም በዚያ በታሰርክበት ሥፍራ በወንጌሉ ቃል ከኃጢአት እሥራት የምትፈታቸው በርካታ እሥረኞች ይኖራሉ።

ስለዚህ ሁል ጊዜ፦
መንፈሳዊ ሕይወትህን ሊፈታተኑ ከዓለም ውስጥ የሚደርሱብህን ተግዳሮቶች ወደ መልካም አጋጣሚ የመቀየር መንፈሳዊ ብቃት ሊኖርህ ይገባል!

እንዲህ ስታደርግ
ችግሮች ለአንተ ችግር መሆናቸው ቀርቶ ለችግሮችህ አንተ ራስህ ችግር ነህ።

╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከ መልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
27 /10/2015 ዓ.ም
ከሕይወት ተራራ ላይ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
3.3K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 18:56:41 https://vm.tiktok.com/ZM2apBUqX
3.6K views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 18:43:08 የክርስቶስ ሥጋና ደም በተዘጋብን ነገር ላይ የምንወስደው መክፈቻ ቁልፋችን ነው፡፡ ትምህርቱ ሲዘጋ፣ ሥራው ሲዘጋ፣ ዕድሉ ሲዘጋ፣ ሰላምና ጤናው ሲታሰር፣ በረከትና ረድኤቱ ሲቆለፍ ያን ጊዜ የጌታችንን ሥጋና ደምን ስለተዘጋው ነገር ለይተን በርዕስ እንወስድበታለን፡፡ "ከሰማይ ከፍታ ይልቅ የኛን ዝቅታ መርጠህ ወደኛ የመጣህ የሰማይ አባታችን ሆይ፥ ሥራው ተዘጋብኝ፡፡ የትምህርት ዕድሌ ተዘጋብኝ፡፡ ሕይወቴ ውስጥ ያለው ጠላት መንገዶቼን ዘጋብኝ፡፡ አቤቱ የተዘጋው በር ሁሉ መክፈቻ ያለህ ቅዱስ አምላክ ሆይ፤ የተዘጋብኝን ክፈተው፣ ዕድሌ ላይ የተኛውን ጠላት አስወግድልኝ፣ እንጀራዬን ከበረከት ያራቀውን ጠላት ከመንገዴ ላይ አንሣው፤ ጸጋና ሞገስ የጠፋበት ኑሮዬን አስተካክልለው፤" ብለን ቅዱስ ቁርባንን ስንቀበል የተቆለፈብን ሁሉ ወለል ብሎ ይከፈታል፡፡ ደሞ ሲከፈት ተጨማሪ የዕድልና የበረከት መንገዶችን ይዞ ነው የሚከፈተው፡፡ የሚዘጋ የሚከፍት አምላክ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ "እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።" (ትንቢተ ኢሳይያስ 22፥22)

የጥንቆላ ፤ የአስማት ፤ ኑሮ ለዕድገት ማምለጫ በሕብረተሰብ ውሰጥ የአሰፈሪነት ግርማ ምገሰ በክፉ መንፈሰ አሠራር ሌላውን ጎድቶ እንደ ድል አድራጊ መፎከር ለመንፈሳዊ ሕይወት አርዓያነት ታላቅ ውርደት ከመሆኑም በላይ ሕብረተሰቡ እምነቱን በጥርጣሬ አያየ ከእምነት አንዲሸሸና የአሕዛብ ዓለማዊ እውቀትና እርኩስ መንፈሰ ውሰጥ እንዲደበቅ አድርጎል።
2.8K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 18:43:06
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጅታችኋል?
አባት እና ልጅ የፊታችን እሁድ ሐምሌ / 02 / 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3ሰዓት ጀምሮ በጎፋ መብራት ኃይል ደብረመዊዕ ቅዱስ መርቆሬዮስና እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የወንጌል ትምህርትና የፀበል አገልግሎት ይከናወናል ።

የቤተክርስቲያኑ አድራሻ ፦ ከጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ትንሽ ዝቅ ብሎ በጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ት / ቤት ጀርባ መሆኑን እየገለጽን ሼር በማድረግ ላልሰሙት አሰሙ

በባለፈው ሳምንት እሁድ ሰኔ 18 / 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በተካሄደው ጉባኤ በብዛት ከውጪ ዓለማት እና ክፍለ ሀገር ከተለያዩ ስፍራ ጉባኤውን ብለው የመጡ ከፍተኛ የምእመናን ቁጥር በመብዛቱ እንዲሁም በአስተናባሪዎች በኩል በቂ ዝግጅት ባለመደረጉ ምክንያት በስነስርዓት አገልግሎቱን ማከናወን አልተቻለም ። ሆኖም የአሁኑ ጉባኤ ለሁሉም እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ አገልግሎቱ እንደሚዳረስ እያሳወቅን በስነስርዓት እንድትስተናገዱ ከወዲሁ ማሳሰብ እንፈልጋለን!
3.4K viewsedited  15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 23:08:58

3.8K views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ