Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ምክር

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkammikr — መልካም ምክር
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkammikr — መልካም ምክር
የሰርጥ አድራሻ: @melkammikr
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 200
የሰርጥ መግለጫ

2ኛወደጢሞቴዎስሰዎች3፥16-17
የእግዚአብሔርሰው ፍጽምናለበጎስራ የተዘጋጀይሆንዘንድ፥የእግ/ርመንፈስን ያለበትመጽሐፍሁሉ ለትምህርትናለተግሣጽ ልብንምለማቅናት ለጽድቅም ላለውምክር ደግሞ ይጠቅማል

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-29 10:24:37 የዘሩ ምሳሌ
የዘሩ ምሳሌዎች በማቲ 13:3-23
ማር 4: 3-13
ሉቃ 8: 5-13 ተጠቅሰዋል::
በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ዘሪው አንድ አይንት ዘርን በአራት የተለያዩ መሬቶች ላይ እንደዘራ ይናገራል ::
መሬቶቹም
-የመንገድ ዳር መሬት
- ጭንጫ መሬት
- እሾሃማ መሬት እና
- መልካም መሬት ናቸው::

(የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 4)
2፤ በምሳሌም ብዙ ያስተምራቸው ነበር፥ በትምህርቱም አላቸው። ስሙ።

3-4፤ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀና ወፎች መጥተው በሉት።

5፤ ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀና ጥልቅ መሬት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤

6፤ ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።

7፤ ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው፥ ፍሬም አልሰጠም።

8፤ ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀና ወጥቶ አድጎ ፍሬ ሰጠ፥ አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ አፈራ።

. . .
14፤ ዘሪው ቃሉን ይዘራል። ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፥

15፤ በሰሙት ጊዜም ሰይጣን ወዲያው መጥቶ በልባቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል።

16፤ እንዲሁም በጭንጫ ላይ የተዘሩት እነዚህ ናቸው፥ ቃሉንም ሰምተው ወዲያው በደስታ ይቀበሉታል፥

17፤ ለጊዜውም ነው እንጂ በእነርሱ ሥር የላቸውም፥ ኋላም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው ይሰናከላሉ።

18፤ በእሾህም የተዘሩት ሌሎች ናቸው፥ ቃሉን የሰሙት እነዚህ ናቸው፥

19፤ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌላውም ነገር ምኞት ገብተው ቃሉን ያንቃሉ፥ የማያፈራም ይሆናል።

20፤ በመልካምም መሬት የተዘሩት ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት አንዱም ሠላሳ አንዱም ስድሳ አንዱም መቶ ፍሬ የሚያፈሩት እነዚህ ናቸው።

*እነዚህ መሬቶች አንድ አይንት ዘር ቢዘራባቸውም በሚገባ ያፈራው መልካሙ መሬት ብቻ ነበር እዚህ ላይ ማብቀል ብቻ በቂ እንዳልሆነ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ያሳየናል ::

ታዲያ አንቺም ልቧሟ እህቴ ይህ መልካሙ የወጣትነት ጊዜሽ
~የልዩ ልዩ የሰይጣን ሃሳብ መተላለፊያ መንገድ ሳይሆን

~በልዩ ልዩ እሾክ በሆነ በዚህ ዓለም ሃሳብ ያስታንቅ

~ጭንጫ ሆኖ በያዝ ለቀቅ እና በለብታ ሂወት ፍሬ ቢስ እንዳይሆን

ፍሬ ለማፍራት የአዝመራው ጊዜ ሳያልፍ እድሜሽ በጨለማው ኃይል ሳይታንቅ እና የቀኑ ክፋት ሳይጫንሽ በጉብዝናሽ ወራት
በመልካሙ ልብሽ ላይ መልካሙን ዘር ዝሪበት::

*ዘሪ ዘርን የሚዘራው በወቅቱ ነው ያለወቅቱ ከዘራ ትርፉ ድካም ነው ማለትም ሰኔ ላይ ካልዘራ ምስከረም ላይ አረም ያጭዳል በውቅቱ ከሆነ አመርቂ እና ያማረ ፈሬ ያፈራል :: ታዲያ አንቺም እህቴ ይህ ያማረው እግዚአብሔርም አለምም የሚፍልገው የወጣትነት ጊዜሽ ሳያልፍ በወቅቱ መልካሙን ዘር ዝሪበት ::

ደግሞም የምታጭጂውን የምታጭጂውን በአንቺ ውሳኔ ሳይሆን በምትዘሪው ዘር አይንት ነው ስለዚህ ምትዘሪውን በጥንቃቄ ምረጪ::

°°የዘሩም ምሳሌ ይህ ነው እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው°°
" ምሳሌው ይህ ነው። ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።"(ሉቃ8-11)
~ለመንገዳችን መብራት
~ለነፍሳችን መድሃኒት
~ ራሳችንን እንድናይ መስታወት
የሆነውን የአምላካችንን ቃል በዘመናችን ላይ እንዝራ እጥፍ ምናፈራ ትውልዶች እንሁን::

ጌታ በፍሬያማ ሂወት የባርከን
Share it
@lebamnegn
@lebamnegn
26 views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:59:30

46 views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 09:27:52 https://t.me/melkammikr
https://t.me/melkammikr
https://t.me/melkammikr
103 viewsedited  06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 10:03:16 ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ነገር ግን ክርስቶስ ይመጣ ዘንድ ላለው መልካም ነገር ሊቀ ካህናት ሆኖ፥ በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥
¹² የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።
¹³ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥
¹⁴ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?
¹⁵ ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።
117 views07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 21:22:35 (ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕ. 53)
----------
4፤ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

6፤ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
205 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 09:47:44
97 views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 07:50:07 ስኬት ምንድን ነው

" በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ። "
(ትንቢተ ኤርምያስ 1:5)

በእግዚአብሔር አቆጣጠር ስኬት ማለት እርሱ ለፈጠረን አላማ መኖር ማለት ነው።

ማካበት የምንፈልገው የሀብት ብዛት፣ እንዲኖረን የምንፈልገው ጤና፣ ውበትና ዝና እኛ በህይወት ስኬታማ ለመሆናችን ማረጋገጫዎች አይደሉም

ስኬታማ ለመሆን እግዚአብሔር እኛን የፈጠረበትን አላማ አውቀን ለተፈጠርንበት አላማ በተሰጠን አጭሯ እድሜ ልንኖር ይገባል።
117 views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 07:49:36 1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
³ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
⁴ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።
⁵ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
⁶ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
⁷ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
⁸ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
⁹ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
¹⁰ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
102 views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ