Get Mystery Box with random crypto!

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆች እኮነን ለምን ጠላኸኝ ወዳጄ የአን | 🔴 ምክረ አበው MEKRA ABAW™

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆች እኮነን
ለምን ጠላኸኝ ወዳጄ የአንድ እናት ልጆች እኮነን
ብዙ ነው መንግሥቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን
#አዝ
የተካፈልኩትን ንብረት አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል ብዙ ነው የሱ መንግስት
አይክፋህ ባክህ ወንድሜ ፍቅር ይበልጣል ከሃብት
#አዝ
ፊትህ በሃዘን አይጥቆር ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግ እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ የአንተም መስዋዕት ያደርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው መታዘዝ ንጉስ ያደርጋል
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ በባእድ ሃገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ የአንድ አባት ልጆች እኮነን

ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ

       ★ @mezmurtenat ★