Get Mystery Box with random crypto!

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምናና ትምሕርት ክፍል Fight Bl | Medical Laboratory

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምናና ትምሕርት ክፍል Fight Blindness in Ethiopia ከተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከመጋቢት 17/2015 እስከ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ለባሕር ዳር እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ይሰጣል፡፡

የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱም በሞራ ግርዶሽ ምክኒያት ለማየት የተቸገሩ ታካሚዎችን እይታ ለመመለስ ያለመ ነዉ።

በዚሁ መሠረት ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ክፍል በስራ ሰዓት በመገኘት ያለናችሁ ችግር ተለይቶ ወረፋ በመያዝ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሆስፒታሉ ጥሪ ያቀርባል።