Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ነው ታሪካችን! ⊰━━━━━━⊱ በአለም ላይ ካሉ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ በእንግሊዝ | Fezekir _ فَذَكِّرْ

ይህ ነው ታሪካችን!

⊰━━━━━━⊱

በአለም ላይ ካሉ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ በእንግሊዝ ሀገር የሚገኘው የዛሬው ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ ነው።የዘመናችን ታላቁ ዩኒቨርስቲ አመሰራረቱ ይህን ይመስላል:-

አቤላርድ የባቱ የተባለው ፀሀፊ እንድህ ይላል: "በሙስሊሞች የስፔን ቶሌዶ ከተማ በ11ኛው ክ/ዘመን ለትምህርት ጉብኝት አቅንቸ ነበር። በጊዜው ስፔን የአዉሮፓ ፈርጥ የስልጣኔ ሀገር ነበረች።የቶሌዶ ከተማ ደግሞ በሰአቱ በዘይት የሚነዱ የመንገድ መብራቶችም ጭምር ነበሯት። በአብያተ መፅሀፍቶቿ ውስጥ ደግሞ ከ400,000 በላይ የተለያዩ መፅሀፎች ነበሩ። "

ይህ የሆነው ከጆን ጉተንበርግ የማተሚያ ማሽን ፈጠራ 15ኛ ክ/ዘመን በፊት ነው።

ፀሀፊው ብዙ እውቀቶችን ቶሌዶ ከተማ ውስጥ ከተማረ በኋላ ለሀገሩ የሚጠቅሙ መረጃዎችንና ሰነዶችን ይዞ ተመለሰ። ከዚያም በሀገሩ ለነበረው የካቶሊክ ጳጳስ ስላየው ነገር ተረከለት። እዚያው በቆመበት ስፍራ እንደ ቶሌዶ ያለ "የጥበብ ማእከል" መገንባት እንደለበት አሳመነ።ጳጳሱም በሀሳቡ ተስማሙ። በዚህም ምክንያት እነሆ የዛሬዉ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እውን ሆነ።

የኛዎቹ የስፔን ከተሞች የእውቀት መፍለቂያ ነበሩ። በተለይ ቶሌዶና ኮርዶቫ ደግሞ የተለዩ ነበሩ።

ሀሳቡን የወሰድኩት የዘር ካርድ ከሚለው "የመሀመድ ዓሊ" መፅሀፍ ነው።



https://t.me/MdJemal