2022-02-27 17:26:36
የአእምሮ ክፍሎችና ስራዎቻቸው
The 3 Levels of the Mind
አእምሯችን 3 ክፍሎች አሉት።
እነዚህም:-
1. ንቁ (Conscious Mind)
2.ከፊል ንቁ(Subconscious Mind)
3.0ድብቁ (the Unconscious) ናቸው።
1. ንቁ የአእምሮ ክፍል
(Conscious Mind)
በምክንያታዊነተ ላይ ተመስርተን በርካታ በእለት ተእለት ድርጊቶችን የምናከናውነው በዚህኛው የአእምሮ ክፍል ውሳኔ መሰረት ነው።
ወደ እምሯችን የሚመጡ ሀሳቦችን ይመዝናል። ከውጭ የመጣውን መረጃ በውስጣችን ካለው ሀሳብ /እምነት ጋር የሚስማማ ወይም የሚፃረር መሆኑን ያረጋግጣል። የሚስማማ ከሆነ ይቀበላል የሚቃረነውን ያስወግዳል።
ለምሳሌ: ስለራሳችን የምናስበው አምራለሁ ብለን ቢሆንና የሆነ ሰው መጥቶ አታምሪም/አታምርም ቢለን ንቁ የሆነው የአእምሮ ክፍላችን መረጃውን በመመዘን ስለራሳችን ከምናስበው ጋር የማይሄድ መረጃ ስለሆነ ወዲያው ያስወግደዋል።
በአጠቃላይ አስበን፣ ሆን ብለን፣ ፈቅደንና በምክንያት/Logic ላይ ተመስርተን የምናከናውናቸው ድርጊቶች በሙሉ የንቁ የአእምሮ ክፍል ውጤቶች ናቸው።
2. ከፊል ንቁ የአእምሮ ክፍል (Subconscious)
ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮችን የምናደርገው በዚህኛው የአእምሮ ክፍል ነው።
ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች እንደ መተንፈስ፣ የልብ ምትና ቅፅበታዊ ነገሮችን የምናደርገው በዚህ የአእምሮ ክፍል በመታገዝ ነው። በስሜት ተነሳስተን የምናደርጋቸው ነገሮች የSubconscious mind ውጤቶች ናቸው።
ሳናስተውል ወይም ሳናገናዝብ ( በከፊል ንቁ የአእምሮ ክፍል ውሳኔ) ባደረግናቸው ነገሮች ኋላ ላይ የምናፍረውና የምንሸማቀቀው ድርጊቱ በንቁ የአእምሯች ክፍል ሲመዘን ነው። ብዙውን ጊዜ ይኼኛው አይሎ ሲመራ እናገኘዋለን።
3. ድብቁ የአእምሮ ክፍል
(the Unconscious)
ድብቁ የአእምሮ ክፍል ያለፉና የቆዩ ከልጅነት ጀምሮ ያጋጠሙን ነገሮችን አጠራቅሞ በመያዝ አሁን ባለው ማንነታችን ማለትም በባህሪያችን፣ ስሜታችን፣ አስተሳሰባችንና ውሳኔዎቻችን ላይ ተፅእኖ ያሳድራል።
በሰው ላይ የሚታዩ ያልተገመቱና ያልተጠበቁ አሉታዊ ባህሪያትና የስነልቦና ውጥረቶች ከድብቁ የአእምሮ ክፍል የሚመነጬ ናቸው።
@BiniGirmachew
1.3K views enbere Girma ⓐⓑⓔⓝⓔⓩⓔⓡ, 14:26