Get Mystery Box with random crypto!

በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም

የቴሌግራም ቻናል አርማ matter_of_facts — በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም
የቴሌግራም ቻናል አርማ matter_of_facts — በውቀቱ ስዩም፣ አሌክስ አብርሃምና ሌሎችም
የሰርጥ አድራሻ: @matter_of_facts
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

የ በውቀቱ ስዩምና አሌክስ አብርሃም አንድሁም ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ጽሁፎች ለማገኘት ከፈለጉ join አደርጉን
🙏እባካችሁ ለሌሎችም አጋሩልን🙏
@matter_of_facts

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 19:25:32 የሌት ማሕሌት
(በእውቀቱ ስዩም)

ትንሽ ቆየት ብሎ ፥ ኮረንቲው ይጠፋል
እሱን ተከትሎ፥ደምኖ ያካፋል
ከናፍቆትሽ በቀር፥ ሁሉ ነገር ያልፋል ::
አሁን መብራት ጠፋ ፥ ተረኛ ነን አይደል
ቁና ይዠ ቀረብሁ፥ ጨለማ ሲታደል ፤
እያገላበጠ ብቻነት አመሰኝ፥
“ ዝናቡ እየጣለ ጋራ ጋራውን
ጎርፍ ያመጣሽ ‘ንደሁ ልጠብቅ ጎርፉን “
የሚል እንጉርጉሮ፥ በድንገት ታወሰኝ ::
ግን ይሄ ትውስታ
አራራይ ትዝታ
ለቆሰለው ልቤ፥ መዳኒት አልሆነም
ያባቶቼ ዘፈን፤ ለኔ አልተዘፈነም፤

ማዶ ዝናብ ዘንቧል፤
ዶፉን ተከናንቧል-
-እንጦጦ-ዲልዲላ
በገፈጅ ይመስል ፥ቀበናም ቢሞላ
ምንም አያመጣም፤ ከ’ድፍ ውሀ ሌላ
እሳት ነው ፍጥረትሽ፥ ከውሃ ጋ አትኖሪም
አንቺ መብረቅ እንጂ፥ ጎርፍ አትሳፈሪም::
( አዳምኤል)

https://t.me/matter_of_facts
98 views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:14:02 እልል ያለ የፍቅር ታሪክ !

(በእውቀቱ ስዩም )
አማረችን እወዳታለሁ፤ እሷም ትወደኛለች
ፍቅራችን የታይታ ሳይሆን የታይታኒክ ነው ፤
የዛን ቀን የተቀጣጠርንበት ቦታ ስደርስ፥
“ በጣም አስጠበቅኸኝ” አለችኝ
“ ትራፊክ ፖሊስ ይዞኝ ነው “ ብየ መለስኩላት፤
“ መኪና ሳይኖርህ ትራፊክ እንዴት ሊይዝህ ይችላል? “
“ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ሮጠሀል ብሎ ያዘኝ “
ቢራ አዘዝኩ፤
አማረች ፥ አማሩላ አዘዘች፤
ከውስጥ የሂሩት በቀለ ተወዳጅ ዜማ ይንቆረቆራል፤
“ እንደ መሽኮርመም ይላል ምነው
አፋር አይሉት ሶማሌ ነው “

ቀዝቃዛ ነፋስ መንፈስ ጀመረ፤
ሰማዩ ብልጭ አለ፤
ፊቷ ላይ አማተብኩላት፥
ሰማዩ ማጉረምረምና ማካፋት ጀመረ፤
የመብረቅ መከላከያ የተገጠመለት ጃንጥላየን ዘረጋሁ፤

“ በረደሽ ? “ ስል ጠየኳት፥

ጭንቅላቷን ባዎንታ ነቀነቀች፥
ካቦርቴን ምሽልቅ አድርጌ አወለቅሁና ኮሌታውን አስተካክየ መልሸ ለበስኩት፤

ከፊትለፊታችን የተንጣለለው የአበባ እርሻ የፍቅር ስሜቴን ቀሰቀሰው፤ በአበባ እርሻው ውስጥ ልዩ ልዩ ቀለም እና መአዛ ያላቸው ፌስታሎች ተበትነዋል፤

ከአበባ ርሻው አጠገብ የሚገማሸረው የግንፍሌ ወንዝ አካባቢውን የበለጠ ግርማ ሞገስ ሰጥቶታል፤ ወንዙ ከአቃቂ ወንዝ የተረከበውን የውሻ አስከሬን በመሸኘት ላይ ነበር፤
“የልጅነት ትዝታየ ተቀሰቀሰብኝ “ አልኳት፤

“ አባብልህ አስተኛው “ አለችኝ፤

“ በልጅነቴ አሳ እያጠመድሁ ቤተሰቤን እደግፍ ነበር “ በማለት ቀጠልኩ፤
“ በመረብ ወይስ በመንጠቆ?”

“ በወንጭፍ”

“ እንዴት ተደርጎ?”

“ ከሰፈራችን ብዙ ሳይርቅ አንድ ግዙፍ ዋርካ ነበር ፤ዋርካዋው ስር ጋደም እልና ማንጎራጎር እጀምራለሁ፤ ገዴ የተባለችው አሞራ እየበረረች ትመጣና ዛፉ ላይ ጉብ ብላ ታዳምጠኛለች፤ ለረጅም ጊዜ ስራ ፈትታ ስለምታደምጠኝ ይርባታል፤ ራቡ ሲጠናባት ከዛፉ አጠገብ ካለው ከሚገማሸረው ወንዝ ስር ከሚርመሰመሱ አሶች አንዱን ባፏ ይዛ ወደ ዛፉ ትመለሳለች፤ ወድያው ወንጭፌን አውጥቼ አነጣጥሬ እጥላታለሁ፤ አሳውን ለግብጽ ግምበኞች፥ ወፊቱን ለኩባ ወታደሮች እሸጣለሁ”

ጠጋ አለችኝና ትስመኝ ጀመር፤
አንባቢ ሆይ! ታሪኩን እዚህ ላይ ልጨርሰው አስቤ ነበር፤ ግን ደስታ በራቀው ዘመን በደስታ እሚጠናቀቅ ታሪክ መጻፍ አልፈቅድም፤

ለሁለት ሳአት ያክል ስትሰመኝ ከቆየች በሁዋላ፤ ከንፈሯን ከግንባሬ ላይ አንስታ፥
“መጀመርያ ስታገኘኝ ፥ ምኔ ነው አይንህን የሳበው? “ የሚል ጥያቄ ደቀነችብኝ ፤

“ ሁለመናሽን ወድጄው ነበር ፤ ግን “ ቶ “ የሚለውን ምልክት አንገትሽ ላይ ተነቅሰሽ ሳይ ተረታሁ”

“ እንዴት ?”

“ ምን ብየ ላስረዳሽ ፤ አየሽ “ ቶ” የሚለው ምልክት ለኔ ከጌጥ በላይ ነው፤ በጥንታዊ የኩሽ ህዝቦች ዘንድ “ የሕይወት ቁልፍ ‘የሚል ትርጉም አለው፤ እና ምልክቱን ሳይ “ እቺ ሴት የተዘጉ በሮችን ሁሉ የምትከፍትልህ ቁልፍ ናት የሚል ሃሳብ ብልጭ አለልኝ”

አሜክስ ትንሽ ስታመነታ ከቆየች በሁዋላ እንዲህ አለች፥

“ህምምምም! To be honest with you “ ቶ “ የሚለውን ምልክት የተነቀስኩት “ ቶፊቅን “ ለማስታወስ ነው “

“ቶፊቅ ደሞ ማን አባቱ ነው ?’

“ የመጀመርያ ፍቅረኛየ ነበር”

እሷ የሞተ ፍቅረኛዋን አስባ፥ እኔ የሞተ ፍቅሬን አስቤ መላቀስ ጀመርን፤

https://t.me/matter_of_facts
251 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 16:53:01 የማለዳ እንጉርጉሮ
(በእውቀቱ ስዩም)
አንዳንዴ ደግሞ ጎህ ቀዶ
አብሮኝ ያደረው ደወል ፥ ከራስጌየ ተጠምዶ
ከወፍ ቀድሞ ሲያመጣልኝ፥ ነግቶብሀል የሚል መርዶ
ብትት ብየ ደንብሬ፥
ግማሽ ፊቴን፥ ትራሴ ውስጥ ቀብሬ
“ እኮ ዛሬም እንደ ወትሮ
ካውቶቢስ ወደ ቢሮ
ከኬላ ወደ ኬላ
ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ
እሺ ከዚያስ በሁዋላ
እያልሁ ስሞግት ልቤን፥ መልሱን አያመለከትተኝ
ይሄን ያህል ነው የታከተኝ።

ጉዞየ ካዋላጅ እቅፍ፥ እስከ ገናዦች አልጋ
ባራት እግር ተጀምሮ፤ ባራት ሰው ሸክም እስኪዘጋ
መንገዱ መንገድ እየሳበ
ትንንሹ ዳገትም፤ ለትልቁ እያስረከበ
እንደ ሐረግ ስጎተት፥ እንደ ጥንቸል ስፈጥን፥
ምን ሽልማት ታሰበልኝ ?” ይህ ልፋቴን የሚመጥን፥
እያልሁኝ ሳውጠነጥን ፥

አንዳንዴ ደግሞ ሲመረኝ፥
እንደ ለማዳ ፈረስ ፥ ሞትን በፉጨት መጥራት ሲያምረኝ፥
ዛፉን የተቀማ አሞራ
በኮረንቲ ምሶሶ ላይ፥ ቤቱን ባዲስ መልክ ሲሰራ
ማሯን የተዘረፈች ንብ፥ በያበባው ስትሰማራ
አይና
እንዲህ እንዲህ እላለሁኝ፤ ራሴን በራስ ሳጽናና
‘ ሺህ ጊዜ ብትራቀቅ፥ ቃላት መርጠህ ብትገጥም
ከዚህ አሞራ አታንስም፥ ከዚች ንብም አትበልጥም
ተፈጥሮ ትግልን እንጂ፥ የድል ዋስትና አትሰጥም’’
ቻለው!

https://t.me/matter_of_facts
468 views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 07:51:38 ሰሞንኛ ጨዋታ
(በእውቀቱ ስዩም)
ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ ውስጥ በሚገኘው የ” አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼ ለረጅም ጊዜ እቆያለሁ፤ ባጭሩ ፥ሬስት ሩምን ርስት ሩም አደርገዋለሁ፤ ያን ቀን ወደ ቤተ-ሰገራ ወሽንቤቱ ስራመድ መብራት ድርግምም አለ፤ ከግማሽ ሰአት የፈጀ ዘለግ ያለ ሽንት ሸንቸ ሳበቃ እያፍዋጨሁ ስወጣ የጽዳት ሰራተኛዋ ፥

"ሴቶች ሽንት ቤት ውስጥ መሽናትህ የሚያሳፍር ነው “ አለችኝ ::

“ በዚህ ጨለማ ፥ ኪችን ውስጥ ባለመሽናቴ ልታደንቂኝ ይገባል “ ስላት ፈገግ አለችልኝ ፤ (ግን ጨለማ ከሆነ ፈገግታዋ እንዴት ሊታየኝ ይችላል ? ሰው ምን ይለኛል አይባልም? )

ባጭር ጊዜ የሌለ ተመቻቸን ፤መጨረሻ ላይ ቁጥርሽ ስንት ነው ?” ስላት፤ “ የጫማየ ወይስ የወገቤ” ብላ ስለመለሰችልኝ አጥብቆ ደበረኝ!

ድብርቴን ለማባረር የሚከተሉትን ሁለት ቀደዳዎች አስታወስኩ፥

ጉዋደኛየ ባለፈው ለአለቃው ‘ የሞተር መኪና አደጋ ስለደረሰብኝ ዛሬ መምጣት አልችልም “ ብሎ ለአለቃው መልክት ሰደደለት፤ አለቅየው “ ይገርማል፤ ዛሬ በጀት መዝጊያ ስለተቃረበ በመስርያ ቤታችን ውስጥ ሰርፕራይዝ ፓርቲ አዘጋጅተን ነበር ፤ ለሰራተኞች ዳጎስ ያለ የገንዘብ ስጦታም አሰናድተናል፤ እንዲሁም ዳጎስ ዳጎስ ያለ መቀመጫ ያላቸው ሴቶች ፓርቲውን ያደምቁታል ፤ በዚህ ዝግጅት ተሳታፊ ባለመሆንህ የተሰማኝ ደስታ ማለቴ ሀዘን ወሰን የለውም ፤ ለማንኛውም ነፍስ ይማር፤ I mean እግዜር ይማርህ” ብሎ መለሰለት፤

ግብዣው በመጦፍ ላይ እያለ ረፍት የጠየቀው ጉዋደኛየ እንደቆሰለ አርበኛ በሁለት ወንድሞቹ ግራናቀኝ ተደግፎ ከች አለ፤
አለቅየው እንዳየው ምን አለ ?

“ እያመመው መጣ! “

በዙ ጊዜ የሰይፉ ሾውን ስመለከት የራሴን ፈጠራ ነስነስ አደርግበታለሁ፤ ባለፈው ሰይፉ የሀይሌ ገብረስላሴን ፊት ይዞ የተፈጠረ ሰውየ አቀረበ፤ ሰውየው ሀይሌን እንዳገኘው “ ወንድሜ ! ብሎ እንደበረኛ ተጠመጠመበት ፥

ሀይሌ;- ወል እንግድ ! በአርባ ደቂቃ ውስጥ ለሚ ኩራ ደርሰህ ከተመለስህ ወንድሜ መሆንህን እቀበላለሁ”

ሰውየው;- “ እሺ! አውቶቢስ ልያዝ ወይስ ራይድ ትጠሩልኛላችሁ? “

በመጨረሻ የዲኤን ኤ ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ መጣ
;
ሰውየው ;- በምርመራው መሰረት ወንድምህ መሆኔ ተረጋግጧል ፥ የሆነ ነገር አታካፍለኝም?”

ሀይልሽ፤- ነገ ቢሮ ብቅ በልና የህይወት ልምዴን አካፍልሀለሁ”
392 views04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 20:18:10 ዛሬ ጧት አንድ ታዋቂ ፀሐፊ ጓደኛየ ጋር በስልክ እያወራን ነው! ሲያወራኝ ከባድ ስራ እንደሚሰራ ሰው ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ ይላል! ምን እየሰራህ ነው?
ቡና ልጠጣ ከአራት ኪሎ ወደፒያሳ እየሄድኩ
እንዴ አተነፋፈስህ ኪሊማንጃሮን የምትወጣ ነው የምትመስለው
ያው በለው ብዙ እቃ ስለያዝኩ ደከመኝ
የምን እቃ ?
አንሶላ ብርድ ልብስ ፒጃማ ስሊፐር ጫማ ፌርሙዝ ሁለት ረዢም ልብወለድ መፅሐፍ ባይብል የጥርስ ቡርሽ የጢም መላጫ ጋቢ ... በቦርሳ አዝየ ነው የምሄደው
ቡና ልጠጣ ነው የምሄደው አላልክም እንዴ ?ይሄ ሁሉ ምንድነው ?
እሱማ አወ ድንገት ካፈኑኝ ተዘጋጅቸ ልታፈን ብየ ነው

https://t.me/matter_of_facts
356 views17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:21:50 "ሞቱማ ሰበቡ"

ከዓመታት በፊት ኦሮምኛ ቋንቋ አልችልም ነበር(ነበር ስል አሁን የቻልኩ አልመስልም?) እና ያኔ ሁሉም ነገር በኤርትራ መንግስት የሚሳበብበት ጊዜ ነበር! ምንም ነገር ኮሽ ይበል የኤርትራ መንግስት ነው ... በአማርኛ ዜና በትግርኛ ዜና በተለይ በኦሮምኛ ዜና ኤርትራ ቋቅ እስኪላት ይሳበብባታል! በነገራችን ላይ ኤርትራ ስሟ ተደጋግሞ ከመነሳቱ የተነሳ ብቸኛዋ ስቅ የሚላት የዓለማችን አገር ነበረች! እና እስከአሁን ልክ እንደአማርኛ የቻልኩት ኦሮምኛ ቃል "ሞቱማ" የሚለው ቃል ነው "ሞቱማ ኤርትራ..." እውቀቴ መስማት ላይ የተመሠረተች ስለነበረች ቃሏን በትክክል ስለማስታወሴ ጥርጣሬ አለኝ

አሁን ዋናው ጥያቄየ "ሞቱማ ኢትዮጵያ" መቸ ነው ሰበብ አቁሞ ሂሱን ውጦ (ሂሱ ብዙ ነው ጠጥቶ ቢባል ይሻላል) እንደአገር እንደህዝብ ሰላም የሚያሰፍንልን? ቢያንስ በቀን ሶስት ጊዜ መብላቱ ቀርቶ ባመት ሶስት ጊዜ በጅምላ አፈር እየበላ የሚኖር ህዝብ እንዴት ነው ወደሰላሙ ወደአብሮነቱ የሚመለሰው? አሁንም ብዙ "ሞቱማዎች" ላይ እያሳበብን ልንኖር ነው በቃ? ሞቱማ ግብፅ ሞቱማ ሱዳን ...እነሱ ሰልችቷቸው ቢያቆሙ እንኳን "ሞቱማ ብራዚል" እንዳንል እፈራለሁ የሰበብ አገር ሰዎች!

https://t.me/matter_of_facts
395 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 15:43:26 ላንቱም ለኔም ነው
(በእውቀቱ ስዩም)

ማንኛውም ሰው አይደለም ደሴት
ክፍለሀገር ናት እያንዳንዷ ሴት
ያገር ክፋይ ነው ወንዱ በሙሉ
የድር ጥሩንባ በምንሰማ ቀን
ማን ሞተ ብለን ምን አስጠየቀን
ሁሌም አንድ ሰው ህይወቱን ሲያጣ፤
የኛም ህይወት ነው የተሸረፈው፥
ላንቱም ፤ ለኔም ነው የተለፈፈው!

መነሻ ሀሳብ ፥ ዮሀንስ ደን( John Donne ) , For Whom The Bell Tolls

https://t.me/matter_of_facts
448 views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 20:41:52 ኑ መርጠን እናልቅስ!
(አሌክስ አብርሃም)

የጨረባ ችሎት የክፉ ዘመን ክስ
"ለገደልኩት ሳይሆን ለሞተብኝ አልቅስ!"
ደም ባጠቀሰ ጣት ወደሰው አጠቁም
ከቻልክ ታጠብና ከሚስኪኖች ጎን ቁም
"መርጦ አልቃሽ " ባይ አንተ "መርጦ አራጅ" ወመኔ
አጨብጭብ ለገዳይ ላልቅስ ለወገኔ
መግደል እጣህ ሁኗል ማዘን እጣው ለ'ኔ!

ካፈራበት ማሳ የሰው ነፍስ ቀንጣሽ
"መርጦ አራጅ" ሳያፍር ለምን ይፈር አልቃሽ ?"
በደም እየዋኘህ አላግጥ አንጓጥጥ
ንፁህ ደም ልትሸፍን አኞ መግለጫ ስጥ
የግፍህ መሠረት አሸዋ ላይ ቢጣል
ፍትህ እንደዝናብ ዶፍ ሁኖ ይመጣል
የት'ቢት ባቢሎን በእንባ ጎርፍ ይናጣል
እስከዚያው ለሰዎች ሰው ሰው ለሚሸቱ
ሰው ከመሆን ኪዳን በግፍ ላልተፋቱ
((እጩ ሟቾች )) ስሙ ግፈኛን አንቀድስ
የፍጅት ኪዳኑን የደም ሱሱን ሲያድስ
"መርጦ ላረዳቸው" ኑ "መርጠን እናልቅስ!"

https://t.me/matter_of_facts
557 views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 12:48:28 በደንባራ በቅሎ ስልጣን ተጨምሮ !
(አሌክስ አብርሃም)

የመረረ አክራሪ ብሔረተኝነትን ያውም አዙሮ ከሚደፋ ጥላቻ ጋር ከኬጂ ጀምሮ እየተጋተ ያደገ ሀይል አሁን እየሆነ ያለው ነገር ያስደነግጠዋል ማለት ዘበት ነው! የበዙ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ የሚበዛው "አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኝነት" አቀንቃኝ ደጋፊ እንዲሁም የዘር ሀረግ ቆጥሮ ከጥቅማ ጥቅሙ ቅንጥጣቢ ለመለቃቀም ያሰፈሰፈው ሁሉ አሁን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያላቸው አመለካከት ስልጣን ይዞ አገር የመምራት ሳይሆን የነብርን ጅራት የመያዝ አይነት ነው! ከአገር እድገት... ከዜጎች ደህንነትና አለም አቀፉ ነባራዊ ሁኔታ በላይ የሚያሳስባቸው ...ራሳቸው አጋነው የሳሉት "ነብር" ነገር ነው! ብንለቀው ዙሮ ይበላናል በሚል ፍራቻ ላባቸው ጠብ እስኪል በፍርሃት ጅራቱን ይዘው እየጎተቱ ናቸው! ሲጎትቱ ግን ነብር ነው እያሉ አይደለም አህያ ነው እያሉ ነው!እንኳን ከሌላው አመለካከት ጋር ቀርቶ ራሳቸው አፍና ልባቸው አይተማመንም!

ከዚህ መጓተት የሚቀድም ዓላማም ሀሳብም የላቸውም! ይሄ መጓተት "ለነብሩም" ለ"ነብር ጅራት ጎታቹም" ፍፃሜ የሌለው ድካም ነው! የመጨረሻ አላማቸው እንደምንም እጃቸው የነብሩ አንገት ላይ ቢደርስ አንቀው መግደልና መገላገል ብቻ ነው! ቢያንስ ያንን ለማድረግ መጀመሪያ የነብሩን ጥፍሮች መቆራረጥ ጥርሶቹን መነቃቀል ያስፈልጋል ብለው ያምናሉ! እያደረጉ ያሉት ግን "ነብር" ብለው ከፈረጁት አካል ላይ ፀጉር መንጨት ነው! ፀጉር ደግሞ ተነቅሎ አያልቅም! በየቀኑ የሚያድግ ተፈጥሯዊ ኡደት አለው! ለዛም ነው በምድራችን ላይ የተፈፀሙ ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋዎች ትዝብትና ፍርድ እንዲሁም የእርስ በርስ እልቂት አትርፈው ያለፉት! የመጨረሻው ጅል እንኳን ይሄን ያውቃል!

የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ፈፅሞ አልገባቸውም! ይሄ የምንጎትተው ነገር ሲሰበከን እንደኖረው ነብር ነው ወይስ በግ አልያም አያያዛችን ያስቆጣው ሰው ብለው ለማሰብ ፍርሃታቸው አፍታ የሚሰጥ አይደለም! ደንባራ ብሔረተኝነታቸው ላይ የስልጣን ቃጭል ተጨምሮ በተቅጨለጨለ ቁጥር ደንብረው አገርና ህዝብ እያጠፉ ነው! በዚች አገር ላይ የመረረው የኦሮሞ ብሔረተኝነት የፈጠረው ትርምስ መቸም አይፈወስም! እንደውም ከቀን ወደቀን እጅግ እየከፋና አድማሱንም እያሰፋ ነው የመጣው! ምክንያቱም አሁንም ስብከቱ ቀንድና ጅራት እየቀጠለ በስርዓት ደረጃ በባለስልጣናት የሐሰት ትርክት ቀጥሏልና!

በእነዚህ አራት ዓመታት የተፈፀመውን ቁጥር ስፍር የሌለው ጥላቻ አቆይተነው ...ለኦሮሞ ህዝብ መብት ተቆርቋሪ ነን በሚሉ ፖለቲከኞች ዩቲዮበሮች ፌሰሰቡከሮች " የሐይማኖት" ሰዎች ጭምር ሌላው ህዝብ ላይ የሚሰነዘር ዘለፋ የጥላቻና እልቂት ቅስቀሳ እንዲሁም ፀያፍ ስድብና ማንቋሸሽ ለሰሚው ይዘገንናል! ተራውን ህዝብ ተውት ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ እንደፈለገ ጥላቻ የሚሰብከውን ለተመለከተ ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ አይነት ብልግና እንዲህም አይነት ባለጌና ጋጠዎጥ ስርዓት በአደባባይ ሰምታ ታውቃለች ወይ ያስብላል! ይሄ ተራ ዘለፋ ብቻ አይደለም ! ለነገም ከዛሬ የከፋ ነገር መሰነቁን ጠቋሚ ምልክት እንጅ! አሳዛኙ ነገር ደግሞ ለዘብተኛ የሚባሉት ሳይቀሩ ከዚች "ለውጥ" በኋላ እንደቀልድ ጭልጥ ወዳለ ጥላቻና የዚህ ቡድን ደጋፊነት እየተንሸራተቱ መግባታቸው ነው!

በነገራችን ላይ ... ብዙ ሰው እዚህና እዚያ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን ተራ የጫካ ቡድን ድርጊት አድርጎ በማየት ዝቅ ያለ ግምት ሊሰጥ ይችላል! ነገሩ ግን ሙሉ ወታደራዊ አደረጃጀትና ስምሪት ያላቸው የሰለጠኑ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቁ የከተማ ክንፍ ያላቸው ስልጣን ላይ ያለው ድርጅት ውስጥ የተሰገሰገ ደጋፊ ሞልቶ የተረፋቸው በወጉ እንኳ ጥፋታቸው እንዳይዘገብ እሹሩሩ የሚባሉ ጭካኔያቸውና እንስሳዊ ድርጊታቸው የሚድበሰበስላቸው ስማቸው በክፉ እንዳይጠራ የሚጨነቅላቸው አካል ያላቸው /በተዘዋዋሪ የሚዲያ ድጋፍ ያላቸው ድጋፉ አበጃችሁ በሚመስል ዝምታ/ አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኞች ናቸው!

እነዚህ ብሔረተኞች ኦሮሚያ ጫካ እና ከተሞች ውስጥ የሚወሰኑ ከመሰለን የዋህነት ነው! (((ነገ አዲስ አበባም ይሁን ሌሎች ከተሞች ህንፃወችን በፈንጅ ከማንጎድና በየቦታው ተመሳሳይ ጥቃት ከመሰንዘር አይመለሱም! የቀራቸው ይሄ ነው በጣም በቅርቡ ደግሞ ያደርጉታል ...ይሄን ))) ዘመናዊ መሳሪያዎችን በገፍ የሚያገኙ ከመከላከያ ሰራዊቱ እኩል የሚታጠቁ ከሞላ ጎደል የክልሉ ህዝብና መንግስት ድጋፍ ያላቸው ሰዎች አሁንም የትና በማን ምን አይነት ስልጠና እየወሰዱ እንዳሉ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው!

መፍትሔው ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣት በተዋረድ እስከወረዳና ቀበሌ ድረስ ለዚህ እልቂት በአለም አቀፍ ደረጃ በለየለት የዘር ፍጅት ተጠያቂ እንዲሆኑ እና በክልሉ ውስጥ ላሉና የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ዜጎች የደህንነት ዋስትና እንዲሰጥ ሁላችንም መጣር! ሁሉም እንደሰው የሚያስብ ኢትዮጵያዊ በዚህ ጉዳይ መስራት ! እንዲሁም በተለይ ኦሮሚያ ክልል ጋር የሚዋሰኑ ክልሎች ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ከዚህ ክልል እንደሚመነጭ አውቀው እንዲሁም የክልሉ አመራሮች ይህን እልቂት የመከላከል ፍለጎቱም ብቃቱም እንደሌላቸው ተረድተው የየራሳቸውን የፀጥታ መዋቅር ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል! ከፓርላማ እስከ"የህዝብ" ሚዲያዎቻችን ጉዳዩ እንዳይወገዝ ለማፈን ያደረጉት ጥረት ታሪክ ይቅር የማይለው አስነዋሪ ተግባር ነው!

ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ ይህን ዘግናኝ ጭፍጨፋ "ጠላቶቻችን አገር ለማፍረሰሰ ምናምን" በሚል እንጩጭ ስብከት ትክክለኛ የአገር ጠላቶችን ከነአስተሳሰባቸው ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ድርጊት ነው! በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ዋና ቀዳሚ ጠላት አክራሪው የኦሮሞ ብሔረትኝነት የወለደው ፅንፍ የለሽ የጥላቻ ትርክት ነው ! በዚህ ትርክት የተጠመቀ ሁሉ አገርን እንደጋንግሪን ቀስ በቀስ እየበከለ ከመግደል ያለፈ ሚና አይኖረውም! ለዜጎቻችን የግፍ ጭፍጨፋ ተጠያቂው ይሄ አካል ነው! የትርክቱ አጥማቂና ተጠማቂ!!

https://t.me/matter_of_facts
511 views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 15:12:01 እንደቆመብኝ ዓለም አይቶኝ ቢሆንስ ?
(አሌክስ አብርሃም)

ይሄ የተረገመ ኮሮና ሳያጠፋፋን በፊት አንድ ሶሪያዊ ጓደኛ ነበረኝ …ከመሬት ተነስቶ ኢትዮጲያን ይወዳል …በተገናኘን ቁጥር ግብፅን ተባብረን እንረግማለን እናማለን ! አገሩ የዩኒቨርስቲ መምህር ነበር ፣ወሬን እሱ ያውራት! ስንትና ስንት መከራ አልፎ ነው አሜሪካ የገባው ግን ሁልጊዜ ሳቅ ከፊቱ ላይ አይጠፋም አወራሩ ራሱ የሆነ ድራማ ነው የሚመስለው ….

‹‹ሚስቴ ጋር የተለያየነው የጋብቻችን ቀን ማታ ነው ›› አለኝ

‹‹አግብተህ ነበር ?››

‹‹ታዲያ! ያውም አይኖቿ እንደዳይመንድ የሚያንፀባርቁ ….ሳቋ ልብህን እንደሳሙና አኩረፍርፎ የሚጨርስ …የእጆቿ ጣቶች እንደባህር እንጉዳይ የሚስልከለኩ ….ከንፈሯ …የሚሳም ሳይሆን እንደአቮካዶ ጁስ በወፍራሙ ፉት የሚባል ዓይነት ….››
አገላለፁ አማሎኝ ‹‹እህት አላት ?›› ልል አስቤ ከአፌ ላይ መለስኩትና

‹‹እድለኛ ነህ ›› አልኩት

‹‹አይደለሁም ባክህ !››

‹‹ምነው? ››

‹‹የጋብቻችን ቀን ማታ … ከተማችን ውስጥ አለ ወደሚባል ኢንተርናሽናል ሆቴል ነበር የሄድነው …እዛ ነው ክፍል የተያዘልን …ሰፊ ይሄን አዳራሽ የሚያክል ክፍል ! በአበባ በተሞላ ክፍላችን ውስጥ ገብተን …የጓጓሁለትን ሰውነቷን በምኞት እየተቃጠልኩ አያለሁ !ጫማወቿን ስታወልቅ በሂና የተዋቡ በወርቅ አልቦ ተተሸቆጠቆጡ ከአንተ የእጅ ጣት የረዛዘሙ ውብ የእግር ጣቶቿ ….ሽፍንፍኗን ከፀጉሯ ላይ ስታነሳው ወገቧ ላይ የሚገማሸር ከክረምት ጨለማ የጠቆረ ውብ ፀጉሯ ….የሙሽራ ቀሚሷን ስትከፍተው የወርቅ ሃብል የሚጫወትበት የብርሃን ሜዳ የመሰለ ሰፊ ደረቷ ….ግራና ቀኝ ሙሉ ጨረቃቃ የመሳሰሉ ክብ ጡቶቿ …ከተፈጠረች እህል ቀምሳ ታውቃለች ወይ የሚያስብል እንዲህ በአንድ አጅ መዳፍህ የምትከበው ውብ ሽንጥ ….ወረድ ስትል በእቅፍ የማትደርሰው ኩርት ያለ ዳሌ ….

ምራቄን ዋጥኩና ‹‹እና ምን ተፈጠረ ?›› አልኩት

‹‹በቃ ያደረገችውን የወርቅ ጌጣጌጥ ሁሉ አወላልቃ ራቁቷን ስትሆን …ወርቅኮ ውበት ይቀንሳል አልኩ …ወርቁን ስታወላልቅ ውበቷ ወጣ ….በቃ እሷን ፈዝዠ ስመለከት የራሴን ልብስ ማውለቅ ረስቸ ነበር ….ወላሂ ! ስልምልም እያለች ‹‹አውልቅ እንጅ ›› ስትለኝ የድምፅዋ ፍስስስ ማለትና መለስለስ እንኳን ልብስ ቆዳን ማውለቅ ያስመኛል .... የአልጋ ልብስና አንሶላውን ገለጥ ሳደርገው የገነት በር የተከፈተ ነበር የሚመስለው …ሽቶው …በቃ በሽቶ የታጠበ አንሶላ በለው ….በባህላችን እንደዛ ነው ….ቀስ ብላ በነዛ ረዣዥምና ውብ እግሮቿ ወደአልጋው ሳብ ሳብ ሳብ እያለች …ስትመጣ በቃ እንደዚህና እንደዛ ጠረጴዛ …ነበር ርቀታችን ….. ፈገግ ብየ ስመለከታት ጅስሜ ሁሉ እንደእሳት እየነደደ ወንድነቴ ሁሉ ከተፈጠረ እንደዛ ቁሞ አያውቅም …እንኳን ሌላ ጆሮየ ቁሞ ነበር …ፀጉሬ ቁሞ ነበር ….

ድንገት አልጋው ጋ ልትደርስ አንድ ሁለት እርምጃ ሲቀር ያለንበት ሆቴል ምድር በሚያናጋ ፍንዳታ ወደፍርስራሽነት ተቀየረ …. የማስታውሰው እነዛ ውብ አበቦች በአየር ላይ ሲንሳፈፉ ነው .... ክፍሉ በአቧራ ብናኝና በሚፈነጣጠር እቃ ሲሞላ ነው …በቃ !!›› ብሎ ትክዝ አለ

‹‹ምን ተፈጠረ ከዛ …ባለቤትህ ….?››

‹‹እኔጃ ! የነቃሁት ከምንኖርበት ከተማ ውጭ ቃሬዛ ላይ ተሸክመውኝ ሲሮጡ ነበር …ከተማችን በጦርነት እየተናጠች ነው …ከሳምንት በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካምፕ ገባን …ሚስቴ ትኑርም ትሙትም አላወቁም አላገኟትም …ከሶስት ዓመት በኋላ እዚህ ያሉ ቤተሰቦቸ ጋር መጣሁ …ፈለኩ አስፈለኩ በቃ አልተገኘችም …. የአላህ ....ህልም ነበር የምትመስለው ! ከሁሉም ግን እስካሁን ሳስበው የሚያስቀኝ ....›› ወዲያው ከትካዜው ወጥቶ መሳቅ ጀመረ

‹‹የሚያስቀኝ ምን መሰለህ? …ከፍንዳታው በኋላ ሲያገኙኝ …እንደዛ እንደቆመብኝ ይሆን ?….እያልኩ እስቃለሁ …ሃሃሃሃሃሃሃሃ ›› ጎርናና ሳቁ አካባቢውን ሞላው ...የነበርንበት ኮፊሾፕ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ዙረው አዩን ...ማን ያምናል ያሳቀውን ነገር ቢሰማ …

‹‹…አስበኸዋል ? አልጀዚራ ፍንዳታውን ሲዘግብ እኔ ራቁቴን ከፍርስራሽ ውስጥ እንትኔን ሚሳኤል አስመስየ ተጎትቸ ስወጣ ….የአላህ ! ጦርነት ክፉ ነው ...አገርህንም አንተንም ከነገመናህ ነው ለአለም የሚያሰጣህ ››

https://t.me/matter_of_facts
467 views12:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ