Get Mystery Box with random crypto!

#ማደግ_ግዴታችሁ_ነዉ የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በዕድገታችሁ ልክ ይገለጣል። 'የጌታን | የእግዚአብሔር ምኩራብ ቤተክርስቲያን/ SYNAGOGUE OF GOD CHURCH/ ⭐ ሲኤምሲ አጥቢያ ⭐

#ማደግ_ግዴታችሁ_ነዉ

የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በዕድገታችሁ ልክ ይገለጣል። "የጌታን መልክ በመወለድ ትካፈሉታላችሁ በዕድገት ትገልጡታላችሁ።" በጌታ ያልተወለደ ዘሩ እንደማይገኝበት ሁሉ እንዲሁ ያላደረገ ደግሞ መልኩ አይገለጥበትም። እግዚአብሔር በመወለዳችሁ ደስ ይለዋል። በማደጋችሁ ግን ይከብራል። መፅሐፍ ቅዱስ በሉቃስ 15. ላይ እንደሚነገረን የጠፋዉ ልጅ ሲገኝ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል ይለናል። በዮሐንስ ወንጌል 15. መሠረት ግን እግዚአብሔር ይከብራል ብሎ ከማደግና ብዙ ፍሬ ከማፍራት ጋር ያይዘዋል።

“ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።”
— ዮሐንስ 15፥8

ስለዚህ መወለዳችሁ ለእግዚአብሔር ደስታ እንጂ ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም። እግዚአብሔር ከእናንተ ህይወት ክብር የሚያገኘው ስትወለዱ ሳይሆን ስታድጉ ነው። "የክርስትና ውሃ ልክ ወይም መለኪያው ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን የልጁ መልክ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የምትለኩት ባላችሁ ፀጋ ወይም ቅባት ሳይሆን ምን ያህል የልጁን መልክ ገልጣችኃል በሚለው ነዉ።" ቅባት የእግዚአብሔርን ሀይል ይገልጣል ዕደገት የልጁን መልክ ይገልጣል። ቅባት በእግዚአብሔር የመቀባት ውጤት ነው መልክ ግን ክርስቶስን የመኖር ውጤት ነው። የትኛውም ፀጋና ቅባት ክርስቶስን ለመምሰላችሁ ዋስትና ሊሆናችሁ አይችልም። የልጁን መልክ የሚያመጣው የእግዚአብሔር ህይወት በመኖር የመንፈስ ፍሬን በማፍራት ነዉ። ይህ ደግሞ ራስን እግዚአብሔርን መምሰል በማስለመድ የሚገኝ ውጤት ነዉ።

“ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥7

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።