Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት እነዶክተር ወንደሰንን ከእስር እንዲለቅ እጠይቃለሁ፤ * «ፋኖን ለማደራጀት ተንቀሳቅሳችኋል | Christian Tadele Tsegaye

መንግስት እነዶክተር ወንደሰንን ከእስር እንዲለቅ እጠይቃለሁ፤
*
«ፋኖን ለማደራጀት ተንቀሳቅሳችኋል» በሚል ሰበብ ወንድማችንን ዶክተር ወንድወሰንን ጨምሮ በጨነቀለታው ለአገራቸው አንድነትና ለሕዝባቸው ደኅንነት ከመንግስት ጎን ተሰልፈው ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩ ወገኖች ባሕር ዳር ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የሰባታሚት ማረሚያ ቤት በግፍ ከታሰሩ ሰነባበቱ። ጉዳዩን የግፍ ግፍ የሚያደርገው እነዚህ ወንድሞቻችን እስከዛሬ ድረስ በማረሚያ ቤት የሚገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድቤት የዋስ መብታቸውን ካስከበረላቸው በኋላም መሆኑ ነው።

ይኼ ጉዳይ አሳሳቢነቱ እጅግ ከፍ ያለ ነው። ዜጎች በመንግስታዊ ተቋማት በተለይም የፍትኅና የፀጥታ ተቋማት ላይ ያላቸው አመኔታ ከተሸረሸረ ሁሉም በእጁና በየደጁ ፍትኅን ለራሱ እንዲወስድ በር የሚከፍት ይሆናል። የፍርድቤቶች ውሳኔዎች በአስፈፃሚ አካላት ሳይከበሩ ሲቀሩ ዜጎች በሕግ የበላይነት እምነት ሊኖራቸው አይችልም። ይህ ደግሞ በውጤት ደረጃ ማንንም የሚጠቅም አይሆንም። ስለሆነም የሚመለከታችሁ አመራሮች ይህን ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ ትሰጡት ዘንድ እጠይቃለሁ።