Get Mystery Box with random crypto!

ማራኪ ገፆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ maraki_getsoch — ማራኪ ገፆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ maraki_getsoch — ማራኪ ገፆች
የሰርጥ አድራሻ: @maraki_getsoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ማራኪ ገፆች ነው ቻናሉ ለእናንተ የተለያዩ ዝግጅቶችን ያቀርባል
👉 ልብ አንጠልጣይ ትረካ
👉ግጥም በጀማሪ እና ታዋቂ ገጣሚያን
👉የፍቅር ታሪኮች
👉የስነልቦና ምክር
👉 አስተማሪ ፅሁፎች
👉 መፀሀፍት በ pdf
👉 አዝናኝ እና አስቂኝ ቪዲዩዎች
👉 አዳዲስ ሙዚቃዎች
👉 የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች
ከታች የምታገኙትን ሊንክ በመንካት ጆይን ይበሉ
ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው🙏

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 12:18:30 #ፍቅር_ያስተምራል

አፍቅሮ #የተከዳው የወፍጮ ቤት ሰራተኛ የጻፈው ደብዳቤ

አንቺ ከረጢት ቢገባሽ አንድ መቶ ኪሎ ብልሹ ባህሪሽን ችዪ
ነበር ያኖርኩሽ

የሰጠሽኝ ፍቅር አምስት ኪሎ አይሞላም ነበር ፡
ልቤን ዱቄት አድርገሽው ስትሄጂ ትንሽ አታፍሪም??

የሰራሁልሽን ሁሉ ውለታ ፍጭት ታደርጊዋለሽ?? ጥፋተኛው
እኔ ነኝ ልመዝንሽ ይገባ ነበር!!

፡ ፍቅርሽ #ሽርክት መሆኑን ማወቅ ነበረብኝ በበርበሬ ወፍጮ
ከተሽ አነደድሽኝ

ሰፌዱ ልቤ አመልሽን ማበጠር ነበረበት እንዲ ወንፊት
አድርገሽኝ ብትሄጂም የምታበረታኝ ሴት አላጣም
፡ እመኚኝ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ጓያ እሆናለው እጠነክራለሁ

እንደ ጤፍ የበዛ ብዙ ኩንታል ፍቅር እንደማገኝ አትዘንጊ

ደሞ ገብስ ገብሱን ነዉ የፃፍኩልሽ
፡ አንቺ ሽንብራ ራስ!

401 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:03:53
306 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:19:55
የከተማችን ምርጥ እቃዎች መገኛ እንደሆነ ያውቃሉ? ማንኛውም አይነት እቃ ቤቶ ድረስ አምጥተን እናስረክባለን ይዘዙን በተመጣጣኝ ዋጋ ለአዲስ አመት ከልዩ ቅናሽ ጋር
290 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:45:52 በፀሎት .…… ..
.........ክፍል 14
የማየውን ማመን አልቻልኩም ማመንም አልፈለኩም እንዴት ብዬ? በሩ መከፈቱን ሲመለከቱ ሁለቱም ከተቀመጡበት ተነሱ ሳግ አፍኖኛል አይኔ በእንባ ጭጋግ ዳምኗል ኤርሚያስ በድንጋጤ ፊቱ አመድ መስሏል በፀሎትን እየሸሸ አንዴ እኔን አንዴ በፀሎትን እያፈራረቀ ግራ በመጋባት ይመለከተናል ከዚ በላይ መቋቋም አልቻልኩም እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ ‹‹ማናችሁ! አንቺ ማነሽ? ምንድነው ነገሩ ቆይ የትኛዋ ናት በፀሎት?›› ኤርሚያስ ይጠይቃል መልስ የሚሰጠው የለም ለካስ ስሜ በፀሎት እንደሆነ ነው የሚያውቀው የእርሱ እንዲህ ግራ መጋባት ደግሞ የበለጠ ነገሮችን ለመረዳት እንዳልችል አወሳሰበብኝ አሁን እርሱም እንደኔ የበፀሎት ወጥመድ ውስጥ እንደወደቀ ገባኝ ወደ በፀሎት ተጠግቶ ‹‹ማነሽ አንቺ ?›› ትከሻዋን ይዞ ሲወዘውዛት ‹‹በፀሎት እኔ ነኝ!!›› አለችው ወደ እኔ ሲመጣ ጭቅጭቃችንን የሰማችው እናቴ ወደ እቤት ገባች ሶስታችንንም እያፈራረቀች ተመለከተችን እና ‹‹በፀሎት!!….. ልጄ… እ›› ብላ ዝልፍልፍ ስትል ልትወድቅ እንደሆነ ቀድሞ የገባው ኤርሚያስ ተንደርድሮ መሬት ከመድረሷ በፊት ተቀበላት ምድር ሰማዩ ዞረብኝ ‹‹ልጄ ነው ያለችው? የምን ልጅ? በፀሎት የእኔ እህት ናት? ሊሆን አይችልም! ቆይ እንዴት መንታ የሌላቸው ጥያቄዎች ጭንቅላቴን ወጥረው ሊያሳብዱኝ ደረሱ ‹‹ኸረረረ ኢቺ ሴትዮ ትቀልድ የለ እንዴ የሞተችው እናቴ ተነሳች እኮ!!!›› ብላ ከጣሪያው በላይ ሳቋን ለቀቀችው እና ቦርሳዋን አንስታ ስትወጣ አንዲት የድንጋጤ ወይም የጥርጣሬ ስሜት ሳይታይባት ‹‹ይሄን ቦታ ለቀሽ ካልሄድሽ ልብሽን እንደምሰብረው ነግሬሽ ነበረ አሰታወሽ? ያውልሽ በፍቅርሽ ትንሽ ተደብሬበታው ከአሁን በኋላ ደግሞ አልፈልገውም ያንቺ ነው መልሼልሻለው ›› ብላኝ ወጥታ ሄደች፡፡ ሰዎች ተሰብስበው እናቴን አፋፍሰው ወደ ሀኪም ቤት ሲወስዷት የሚሆነውን እያየው ከመደንገጤ የተነሳ ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ በፀሎት ይሄ ሁሉ ሲፈጠር ምንም ሳይመስላት ትንሽ እንኳን ሳትረበሽ መሄዷ ደግሞ ሌላ ተአምር ሆኖብኛል፡፡ ከታማሚነት ወደ አስታማሚነት በሰአታት ልዩነት ውስጥ ሽግግር አደረግኩ ግን እኔም በቂ እረፍት ማድረግ ስለነበረብኝ ከእናቴ አጠገብ ተቀምጬ አይን አይኗን አያታለው እንጂ ሁሉም ቦታ እየተሯሯጠ የእናቴን ሂወት ያተረፈልኝ ኤርሚያስ ነው፡፡ ባየወት ቁጥር ስለ እርሱ ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ትኩር ብሎ አንዳንዴ ሲያየኝ አይን ለአይን እንገጣጠም እና አይኔን እሰብራለው ለእርሱ ይቅርታ ማድረግ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም በተለይ እናቴ እንዳለችው በፀሎት እህቴ ሆና ከተገኘች ነገሮችን ለመቀበል ከምገምተው በላይ እንደሚከብደኝ ይሰማኛል እናቴ የደም ግፊት ስለበረባት ነው በፀሎትን ስታይ በድንጋጤ የወደቀችው ኤርሚያስ ሰዎች አስተባብሮ በፍጥነት ሀኪም ቤት ባትሄድ ኖሮ እህን ግዜ አጥቻት ነበረ፡፡ በነጋታው በጠዋት የኤርሚያስ ስልክ ጮኸ እኔንም ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ እርሱ ነው ከዛን ቅፅበት በኋላ እንኳን ልናወራ በሙሉ አይን ተያይተን አናውቅም ነበር የተደወለለትን ስልክ ትንሽ ካወራ በኋላ ‹‹ላንቺ ነው›› ብሎ ሰጠኝ የማን መሆኑን ሳይ የእራሴ ስልክ ቁጥር ነው ‹‹ሄለው ›› አልኩኝ በፀሎት ነበረች አባቷ በሂወት እና በሞት መካከል እያጣጣረ እንዳለ ነገረችኝ እና አንድ ውለታ እንድውልላት ‹‹አባቴ ስላንቺ ሰምቷል እና አንድ ጊዜ አይንሽን ማየት ይፈልጋል እባክሽ አባቴ እንዳደርግለት የጠየቀኝን ነገር አለማድረግ አልችልም አንዴ መጥተሸ እይው ?›› ነበር ያለችኝ አባትዋን እንደምትወደው በአንደበቷ ስትናገር ሰምቻታለው ሆስፒታል መሆኑንም ጭምር ታድያ የእርሷ አባት በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ እኔን ማየት ለምን አስፈለገው? እናቴ ያለችው ነገር እውነት ነው ማለት ነው? በአንድ በኩል እንደዚ አስባለው በሌላ በኩል ደግሞ ስንት ጊዜ ትታለያለሽ ቃል ኪዳን እረፊ የጀመረችውን ነፍስሽን የመንጠቅ ስራ ልትጨርሰው ነው! አርፈሽ ተቀመጪ! አላየሽም እንዴ እናትሽ ልጄ ስትላት እንዴት ስቃ እንደሄደች? በዛ ላይ እርሷ ለማንም ነፍስ የምትራራ አይደለችም አትሂጂ ይለኛል፡፡ …..በመጨረሻ ከእራሴ ጋር ብዙ ስጣላ ከቆየው በኋላ አባቴ ተኝቶበታል ወዳለችበት ሆስፒታል ሄድኩ የተኛበት ክፍል በሩ ላይ ስደርስ በፀሎት ብቻዋን ተቀምጣ በግልኮስ እርዳታ ነፍሱ የቆየውን አባቷን ትጠብቃለች እንዳየችኝ ከተቀመጠችበት ተነሳች ፊቷ ላይ የተመለከትኩት የሀዘን እና ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ግን እድሜ ልኬን የሚረሳኝ አይመስለኝም ያኔ ዘናቡ ላይ ቆማ ሳያት ተስፋ የቆረጠች የመሰለኝ ትክክል ነው ሁለታችንም ከቃላት በላይ የሆኑ ንግግሮችን በአይኖቻችን ተነጋገርን ተስፋ መቁረጧን በአይኗ ብቻ እንደተረዳውት የአባቷን ፍላጎት ለማሟላት ስለመጣው በአይኗ አመሰገነችኝ ‹‹ አባ አባቴ..እቺውት መጥታለች›› አለችው ቀ ስ ቀ ስ ቀ ስ ቀ ስ እንደማድረግ ብላ የአባቷ አይኖች በቀስታ ተገለጡ ገና ጎልማሳ ነው አባቷ ግን በሽታው ሰውነቱን ጨርሶት አቅም አሳጥቶታል እጆቼን ለመያዝ ሲሞክር አቅም አንሶት ተዝለፈለፈ ሰውነቱ ከመመናመኑ ብዛት እጆቹ እንኳንስ ለመያዝ ሲታይም ያስፈራል እጆቹ መያዝ ሲያቅታቸው እኔ ለመያዝ ስፈራ ተመልክታ እጆቼን ያለ ፍቃዴ ጎትታ የአባቷ እጆች ላይ አሳረፈቻቸው ተሳቀቅኩ እሷ ደግሞ በግልምጫ ከመሬት አንስታ ደባለቀችኝ እጄን ስትጎትተኝ ሙሉ ለሙሉ ያልዳነው ቁስሌ በሀይለኛው አመመኝ እና አቃሰትኩ እሳቸው ሲይዙኝ ግን በቀስታ እና በልስላሴ ስለሆነ የቁስሉ ህመም ቀስ በቀስ እየተወኝ ሄደ ‹‹ ቃል..ኪዳን…ልጄ…››ሲሉኝ ልቤ ለሁለት ተከፈለ እናቴ እስከ ዛሬ አባቴ በህይወት እንዳለ እህትስ እንለኝ ለምን ደበቀችኝ? እውነት ይህ ሰው አባቴ የተንኮል ቋት የሆነቸው በፀሎት ደግሞ እህቴ ናት? ይሄ እውነት ውስጤን ምንኛ ጎዳኝ እንዲህ ያለ አባት ከሚኖረኝስ ዝንት አለም አባት ሳይኖረኝ ቢቀር ይሻለኛል፡፡ ‹‹አ ባ ት ሽ እኔ ነኝ ልጄ ›› አለና ሀይለኛ ሳል ያጣድፈው ጀመር ሳሉ እረፍት አልነበረውም ሲስል በየመሀሉ አክታውን ሲተፋ ሙሉ ለሙሉ ደም ነው ከአፍ የሚወጣው ይህን ማየት ስለዘገነነኝ በፀሎት በማስታጠቢያ አጠገቡ ሆና ስትቀበል ክፍሉን ለቅቄ ወጣው ፡፡ አንድ ማህፀን ያፈራን አንድ ላይ ተቃቅፈን የተረገዝን ልጆች ነን እናቴ እናቷ አባቷ አባቴ ናቸው ግን አንዳችን ለአንዳችን ምንም ስሜት የለንም ከመወለድ በላይ አብሮ በማደግ የምናገኘውን የእህትማማችነት የወላጅ ፍቅር ቤተሰቦቻችን ነጥቀውናል በፀሎት ጠላትነ በሀይል እንዴት ማሸነፍ እንደምትችል ተንኮል ተምራ አደገች እኔ ቃል ኪዳን ከሰው ጋር እንዴት በፍቅር መኖር እንደሚቻል ተምሬ አደኩ ወላጆች ሁሌም የልጆች መሰረት ናቸው እሾህ እየዘሩ ስንዴ መጠበቅ ቂልነት ነው የተዘራ ይበቅላል አውሬ እንኳን ፍቅር ለሰጠው ፍቅር ያውቃል ፡፡
ይቀጥላል …….
@maraki_getsoch
@maraki_getsoch
316 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:29:34
: ማስተዋል እያዩ
:ጀግና
137 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:28:44
ዩቲዩብ ክፍያ እንደጀመረ ያውቃሉ? ገቢዎትን ማሳደግ ይፈልጋሉ......
227 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:13:00 """"""""""""""""""በፀሎት""""""""""""""""" """""""""""""""ክፍል 13"""""""""""""""""
ከመስሪያ ቤት ስወጣ ሰአቱ እየመሸ ነው መጨላለም ጀምሮአል እስከዚ ሰአት ድረስ እነዛን ፋይሎች ለማጣራት ስሞክር ነበር ምንም ነገር ላገኝባቸው አለመቻሌ ደግሞ ጊዜዬን እንዳባከንኩኝ እንዲሰማኝ አድርጎኛል ልክ ከመስሪያ ቤት ወጥቼ በር ላይ ስደርስ የኤልያስን ጃኬት የለበሰ ሰው በሞተር አንዲት ሴት ጭኖ ከመስሪያቤታችን በር ላይ ተነስቶ ሲሄድ ተመለከትኩ አኳኋኗ በሙሉ እኔን ይመስላል ልበል? አከባቢዬን በሙሉ በጥንቃቄ መመልከት ጀመርኩ እጅግ በፍጥነት የሚመጣ ሞተር ሳይክል አይኔ ላይ መብራቱን በረጅሙ ለቀቀብኝ ‹‹ እንዴ ምን ሆኖ ነው ሰውየው መንገዱ ላይ አያበራም እንዴ?›› እያልኩ ስነጫነጭ በሚያስደንቅ ፍጥነት ከኪሱ አንድ ጥቁር ነገር አወጣ ቆምያለው! እንዴ! ኸረ ሽጉጥ ነው! ፊት ለፊቴ አፈሙዙን ደቅኖ ተመለከትኩ ሁሉም ነገር የሆነው በፍጥነት ነው ደረቴ አከባቢ ሀይለኛ ህመም ተሰማኝ ህመሙን ለመግለፅ አልችልም እጆቼን ደረቴ ላይ ሳደርገው በደም ተነከረ ሁሉም ነገር ቀስ በቀስ ጨለመብኝ፡፡ በሰመመን ጢጥ ጢጥ ጢጥ የሚል ድምፅ ይሰማኛል አይኖቼን በቀስታ ገለጥኩ ሙሉ ክፍሉ በነጭ ቀለም የተቀባ ነው፡፡ ክፍል ውስጥ ግልኮስ እና ኦክስጂን ተተክሎልኝ ነው የተኛውት በቀስታ በክፍሉ ውስጥ ማን እንዳለ ለማየት ስሞክር እናቴ አጠገቤ ካለ ወንበር ላይ ኩርምት ብላ ተኝታለች ‹‹ምን ሆኜ ነው …?›› የተፈጠረውን ነገር ለማስታወስ ሞከርኩኝ ከመስሪያቤት እየወጣው ነበር በፀሎት እና ኤርሚያስ በሞተር ተቃቅፈው ሲሄዱ ተመለከትኳቸው እና አንድ ሰው በሞተር መጥቶ ሽጉጥ! …. በጥይት ተመትቼ ነው ማለት ነው ሁኔታዎችን ሳስታውስ ሳላውቀው ለካስ እየተወራጨው ነበር በመወራጨቴ ምክንያት በማሰማው ድምፅ እናቴ ከእንቅልፏ ነቅታ ኖሯል ‹‹ ቃልዬ ቃልዬ ልጄን!!!!!!..... ዶክተር….!›› እየጮኸች እየተጣራች ወጣች ምን እንደሆንኩ አላውቅም ዶክተሮች እየተሯሯጡ መጥተው መርፌ ወጉኝ፡፡
ስነቃ ሰውነቴ እንዳለ ዝሏል መተንፈስ ብቻ ኦክሲጅኑ እረድቶኛል ጭንቅላቴ ውስጥ መአት ጥያቄዎች ይራወጣሉ ‹‹ማነው እንዲህ ያረገኝ? ኤርሚያስ በፀሎትን ያውቃታል ማለት ነው? ለሁለት ሆነው አብረው ሲጫወቱብኝ ነበር ማለት ነው? እነዴት እስካሁን ልጠረጥር አልቻልኩም ግን? ምን አይነት ደደብ ነኝ ግን›› ሳላስበው እንባዬ ፈሰሰ በጆሮዬ አድርጎ በተኛውበት ወደ ፀጉሬ ሲሰርግ ታወቀኝ ድምፅ እያወጣው ማልቀስ ስጀምር እናቴ እጄን ይዛ እያሻሸች እርሷም ተከትላኝ ማልቀስ ጀመረች ‹‹አልቻልኩም ከዚ በላይ አልችልም እማ ከዚ ይዘሽኝ ሂጂ›› ልላት ፈልጌ ነበር ግን እንዴት ብዬ? መናገር አልቻልኩም፡፡ ነገሮች ቀስ በቀስ መሻሻል ጀመሩ ከቀን ወደ ቀን የጤናዬም ሁኔታ ለውጥ እያሳየ መጣ የደረሰብኝን አደጋም በተመለከተ ለፖሊስ ቃሌን ሰጠው እስካሁን ግን ሆስፒታል ውስጥ ነኝ፡፡ በጣም የገረመኝ ግን እስከዛሬ ድረስ ከመስሪያቤትም ሆነ አብሬያቸው ከምኖርባቸው ጎረቤቶቼ አንድም ሰው ሊጠይቀኝ አለመምጣቱ ነው የሞባይል ስልኬን ከአደጋው በኋላ ላገኘው አልቻልኩም የደረሰብኝን በደል እና የኤርምያስን ክህደት ሳስበው ልቤ በሀዘን ይደማል ልቋቋመው የማልችለው ሀዘን መላ ሰውነቴን ይቆጣጠረኛል አንዳንዴ ብቻዬን ስሆን ስቅስቅ ብዬ አለቅሳለው ሀዘኑ ይከብደኛል በጸሎትን ግን ምን ባደርጋት ነው ይህን ያህል የመረረ የሀዘን ቀንበር እንድሸከም የፈረደችብኝ ብዬ አምርሬ እወቅሳታለው፡፡ ዛሬ ጥሩ የሆነ ለውጥ እያሳየው ስለሆነ ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን ነው፡፡ ከአስራ አምስት ቀን ቆይታ በኋላ ወደ እቤቴ በኮንትራት ታክሲ ከእናቴ ጋር መሄድ ስጀምር ውስጤ እርብሽብሽ እያለብኝ ምንም መረጋጋት አልቻልኩም ኤርሚያ ትዝ አለኝ ምን ያህል አስመሳይ ቢሆን ነው ለ25 አመታት ማንም ደፍሮት የማያውቀውን ገላ በዚህች አጭር ቀናት ውስጥ እንዲህ ያረከሳት? ‹‹እርካሽ! እርካሽ! ነሽ ቃል ኪዳን! እንዴት በአንድ ጊዜ ከእቅፌ ብትወጪ እንደዚህ ትረክሻለሽ? ›› ያለችኝ መሰለኝ እናቴ ይሄንን የማስረዳት አቅሙ ይኖረኝ ይሆን? እቤት ስንደርስ በሬ ገርበብ ተደርጎ ተዘግቷል የዚህ ቤት ቁልፍ ያለን እኔና ኤርሚያስ ነን እርሱ ደግሞ እንዴት ቢደፍር ነው እኔ በህይወት እና በሞት መካከል ሆኜ በጥቶ ያልጠየቀኝ ሰውዬ እኔ የሌለውበት ቤት ምን ይሰራል? ደግሞ እንደዛ ሲያታልለኝ ኖሮ ትንሽ እንኳን አያፍርም እንዴ ? የቤቱን መከፈት እናቴ ስታይ ወደ እኔ ዞራ በጥርጣሬ ተመለከተችኝ በምድር ላይ የምኖርላት እና የምትኖርልኝ ብቸኛዋ አለችኝ ብዬ የምላት እናቴ ናት በኔ ጣጣ ምንም እንድትሆንብኝ አልፈልግም እንደጀመሩ እኔኑ ይጨርሱኝ ብዬ እሷን በር ላይ አቁሜ እኔ ሰተት ብዬ ወደ ውስጥ ገባው …አይኔ የሚያየውን ማመን አልቻልኩም በፀሎት እና ኤርሚያስ የኔ ኤርሚያስ ሶፋው ላይ ተቃቅፈው እየተሳሳሙ ነው ባለውበት ደርቄ ቀረው፡፡ ይቀጥላል.....ሼር አርጉ እንጂ
@maraki_getsoch
209 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 04:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:57:30 የ Platinum ደረጃ አጋራችን መልዕክት
የ አለም አቀፍ እብዶች ህብረት

Yohannes'
#Sleenee

''ይምጡ ይጎብኙ ይመዝገቡ ቀጥታ ወደ ስራ ይሰማሩ
ኢትዮጵያ በእብዶቿ ህብረት ታፍራ እና ተከብራ ለዘላለም ትኑር''
Makbeal Endale
240 views♪♫•*¨*•.¸¸Mäķbêł¸.•*¨*•♫♪, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:57:16 ድካም አልባ ውጤት የለም!
፨፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨፨
መሱዓትነት የሌለው ግኚት ጠዓም የለውም፤ በልፋት ያልታገዘ ከፍታ አያስደስትም፤ ትጋት አልባ ስኬት የለም። እያንዳንዱ ለውጥና እድገት ውስጥ ልፋት፣ ትጋት፣ ጥረት አለ። በዚም በዛም፣ በላይም በታችም ያለድካም የመጣ ነገር ለመጥፋትና ለመበተን እጅጉን የቀለለ ነው። የጉጉት ብዛት (temptation) ያለድካም አንዳች ነገር አያስገኝም። የማትፈልገው ልማድ ቢኖርብህ ከማቆም ጉጉት በላይ ልትሰራበት ይገባል፤ የምታልመው ስፍራ ቢኖር ያለምንም ጥረት ከምትመኘው ይልቅ መጣር ይኖርብሃል። ጥረት ሲባል ግን ትንሿና ማንም የሚያደርጋትን ጥረት አይደለም። በሃሳብህ ልክ የገዘፈ፣ በህልም ልክ የረቀቀ፣ ስኬትህን ከፍታህን የሚመጥን የማይገታ ብርቱ ጥረት።

አዎ! ጀግናዬ..! ድካም አልባ ውጤት የለም፤ ካልለፋህ፣ ካልሰራህ፣ እራሰህን ካላሻሻልክ ስኬት አይኖርም። በስኬት አለም አንድና አንድ ህግ አለ "እያንዳንዱ ግኚት የልፋትህ ውጤት ነው፤ እድል የሚባል ነገር የለም"። እድልን ጠብቆ ከስኬት የደረሰ የለም፤ ለስኬቱ ግን ለፍቶ ተግቶ እድልን ለእራሱ የፈጠረ አለ። ባዶ አጋጣሚ፣ ባዶ እድል የሚባል ነገር የለም። ባልተገነባ ማንነት ውስጥ እድል ኬትም አይመጣም። ምንም አድርግ ምን ለተለወጠ ህይወት፣ ለተቃና ኑሮ፣ ለተስተካካለ ማንነት፣ ከፍ ላለ አስተሳሰብ፣ ለላቀ ለውጥ እራሱን የቻለ መሱዓትነት ያስፈልገዋል። መሱዓትንተ ሲባል የአንድ ቀን አይደለም፤ ዛሬ ወጥቶ ነገ እንደሚደርቀው ጤዛም አይደለም፤ ፍላጎቱን የሚመጥን፣ ከመሻቱ ደረጃ ጋር የሚሄድ ከፍ ያለ መሱዓትነት።

አዎ! ያለውበት ስፍራ አይመጥነኝም ስላልክ፣ ስለተማረርክበት፣ አብዝተህ ስለጠላሀው ብቻ አንዳች የሚቀየር ነገር የለም። ጥረት አልባ ምሬት ሁሌም ምሬት ነው፤ አዲስ ነገር የማያስሞክር ሰቆቃና ችግር ሁሌም ችግር ነው። ችግር ችግርነቱ የሚያበቃው የመፍትሔ አካል ስትሆን ብቻ ነው። ስራህን የመቀየር ፍላጎት ካለህ አማራጮችን መመልከት ይኖርብሃል፤ ባልለመድከው መንገድ መጓዝ አለብህ፤ የማታውቀውን ማወቅ፣ ያልተማርከውን መማር ይጠበቅብሃል። ከማትፈልገው ህይወት ለመውጣት የማትፈልገውን ነገር ማድረግ ሊኖርብህ ይችላል፤ ከሞቀው ጎጆህ ውጪ ለዝናብ፣ ለብርድና ለውርጭ ልትጋለጥ ትችላለህ። እርሱ ለፍላጎትህ የምትከፍለው ትንሽ መሶዓትነት ነው። መቀየር ስለምትፈልገው ሁኔታ የመቀየር አቅሙና ብርታቱ ይኑርህ፤ እያንዳንዱ ድካምህ፣ ጥረትህ ዋጋ እንዳለው ተረዳ፣ አሻጋሪ መሰላልህ፣ ህይወት ቀያሪ ምዕራፎችህ የምኞትና የጉጉት ጊዜያቶችህ ሳይሆኑ የጥረትና የትጋት ጊዜያቶችህ እንደሆኑ ተረዳ።
@maraki_getsoch
@maraki_getsoch
427 viewsBebo, 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:08:47 https://t.me/Real_FeelingsCH
350 viewsKebab ki kira , 09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ