Get Mystery Box with random crypto!

manyazewal motivational speech

የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewal_eshetu — manyazewal motivational speech M
የቴሌግራም ቻናል አርማ manyazewal_eshetu — manyazewal motivational speech
የሰርጥ አድራሻ: @manyazewal_eshetu
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.64K

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-31 11:22:37
ወደዚህ ስራ ስገባ አላማው ብዙ ተከታይ ማፍራት አልነበረም::
-
እኔ ራሴው ዞሮብኝ እና ጨንቆኝ የራሴን ችግር ለመቅረፍ ያደረኩት ጥረት ወደአልጠበኩት የህይወት ጎዳና መራኝ::
-
ስራዬ ሽልማት ይገባዋል ባይ አይደለውም::ይህንን ስራ መስራቱ ብቻ በራሱ ከትልቅ ሽልማት ይበልጣል::
-
አምላክ በሰጠኝ ጥበብ አያሌ ሰዎችን ለውጦ ያሳየኝ ጊዜ እንደተሸለምኩኝ አውቅያለው::
-
ግን ሁላችሁም ስለምትከታተሉኝ እና በትምህርቴ ስለተበረታታችሁልኝ አመሰግናለሁ::
-
ለስራ ቡድኔ: ለተከታዮቼ: በመላው አለም ለምትገኙ ደንበኞቼ እንዲሁም ውድ ለሆናችሁ በመንፈስ ንቁ በአለም ብቁ የማንያዘዋል እሸቱ የቡድን ስልጠና የመጀመርያ ባቾች ሁላችሁም ተባረኩልኝ ::
-
ተመስገን!!
-
Celebrating our 100,000 YouTube subscribers milestone at our office with Team Manyazewal and our first group coaching batch!!
2.2K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 21:16:08 በእድል ካልሆነ በአምላክ ሞክረው::ዩኒቨርሱ የሚሰራው በእርሱ ህግ ነው!
-
አምላክህ ቀን ከሌት ቢሰራልህም አንተ ካልሰራህ ምንም አይሆንም::ወፍ የለም::
-
ሲፈጥርህ እንደራሱ ነፃ የሆነች ነፍስን በሰውነትህ አኖረ::
-
ፈጣሪ ሁሉን ነገር መቆጣጠር ቢችልም ያንተን ነፍስ ግን ላንተ ቁጥጥር ትቷል::
-
ዋጋህ እጅግ ትልቅ ነው::የንጉሶች ሁሉ ንጉስ ልጅ ከመሆንም በላይ ነው::
-
ይህ ካልገባህ ግን ነገር ይበላሻል::
-
ከሁሉ አስቀድመህ ነፍስህን እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ተማር::
-
ያንተ ነፍስ ከአምላክ ባህር በረከቶችን የምትጨልፍ ልዩ መሳርያ ናት::ባለማወቅ ግን እርግማንም ልትጨልፍ ትችላለች::
-
ነፍስህን በጥበብ መጠቅ ካስቸገርህ ለእርሱ መንፈስ አስገዛት:: "ያንተ ፈቃድ በእኔ ላይ ይሁን!" በለው የሚገባህንም ይስጥሃል::
-
Melkam ሰንበት

የማንያዘዋል እሸቱ ስልጠናዎች!
-
እሁድ ጠዋት ከ3:00 እስከ 6:00
ሰኞ ማታ ከ12:00 እስከ 2:00
-
ቦሌ በአለም ሲኒማ!!
መግቢያ 100 ብር ብቻ
4.2K views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 21:13:37
3.4K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 08:42:33 እባካቹ በምትችሉት ሁሉ እርዳታቹ ይድረሳት
3.7K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 08:40:01
3.9K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 08:39:43
4.4K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 23:39:42 እንደ ሰማይ ሩቅ አድረገሽ የምታስቢው አምላክ እንደ እስትንፋስሽ ቅርብ ቢሆንስ?

-

ካንቺ ውጪ የምትፈልጊው አምላክ በአንቺ ውስጥ ሆኖ እየፈለገሽ ቢሆንስ?
-

ጨረቃ እና ጸሐይ የሚሰግዱለት : እልፍ አእላፍ መላዕክት የሚያመሰግኑት አምላክ ባንቺ ውስጥ ነው::
-
እስከ ዛሬ የአምላክን ፍቅር ካልቀመስሽ ካንቺ ውጪ በማይገኝበት በመፈለግሽ ነው::
-
እግዚአብሔር ባንቺ ልብ አዳራሽ ያለና የሚኖር አምላክ ነው::እንቺ በሱ ልብ እናዳለሽ እርሱም ባንቺ ልብ ይኖራል::
-
በልብሽ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ከጠፋ የክፋት: የቅናት: የፍርሃት: የጥላቻና የሐጢያት ሀሳብ ስለበዛ ነው::
-
የአምላክን እውነተኛ ሐይል: ውበትና ፍቅር ለመቅመስ? ልብሽ በይቅርታ ሳሙና ይታጠብ::
-
መፈሳዊነት ውስብስብ የህግ ጨዋታ አይደለም::መንፈሳዊነት የልብሽን መንፈስ ከአምላክ መንፈስ ጋር በፈቃድ የማገናኘት ጨዋታ ነው::ይህም ከዓለም ችግሮች ሁሉ መውጪያ ቀዳዳ ነው::
-
በአለም ነገር ከአለም ችግር ያመለጠ አንድም ሰው በአለም ታሪክ የለም::በመንፈስ ግን ብዙ ተዓምራት እንደሚሆኑ ስምተናልም አይተናልም::

-
ያለን አንድ ሐይል መንፈሳዊነት ነው::እርሱም የፈጠረን አምላክ ሐይል ነው::የሚገኘውም በእኛ ልብ ውስጥ ነው::
-
ይህ የወደድነው በጎ ስኬት እንድንፈጥር የሚያስችል ሐይል ነው::በጎ ልብ መያዝ ይህንን ሐይል ለመጠቀም ቁልፍ ነው::
-
መልካም እንሁን:: መልካሙ የአምላክ መንፈስ በልባንችን ይፍሰስ::ከራሳን አልፎ ለአለም ይተርፋል::
-
#መልካም_አለተ_ሰንበት


ቦሌ በአለም ሲኒማ የማንያዘዋልን እሸቱን ስልጠና ታደሙ!!
-
እሁድ ጠዋት ከ3:00 እስከ 6:00
ሰኞ ማታ ከ12:00 እስከ 2:00
-
3.5K views20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 23:39:25 ድርጅቱን የሚያከስረው የሰራተኞቹ የከሰራ አስተሳሰብ ነው::
-
ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ አእምሮ ባላቸው ሰራተኞች የተሞላ ድርጅት ዘመኑን ቀድሞ የሚሄድ ስኬት ያመጣል::
-
ሁሉም ነገር የሚመጣው ከሰው መንፈስ እና አእምሮ ውስጥ ነው::ውድቀትም ኬትም ምንጫቸው ይህ ነው::
-
ንቁ የድርጅት መሪ ይህንን የተረዳ እና የሰራተኞቹ አእምሮ እና መንፈስ ላይ ኢንቨስት ያደረገ ነው::
-
መልካም የስራ ቦታ መንፈስን የሚያበረታቱ ስራተኞችን መፍጠር የድርጅት ስኬት ሁሉ መሰረት ነው::እንዲህ ያለ የስራ ቦታ መንፈስ(company culture) የሚፈጠረው በስልጠና እና በትምህርት ወይም በመረዳት ብቻ ነው::
-
በግሌ የኢትዮጵያ ቢዝነሶች በእውቀት የሚነዱ ከመንፈስ የሚፈጥሩ እንዲሆን የማድረግ ህልም አለኝ::እንዲህ ያሉ ድርጅቶች ደግሞ ንቁ ሆነው አለም የመለወጥ አቅም ይኖራቸዋል::
-
የሜንቶርሺፕ እና የማይንድሴት ስልጠና ከተለያዩ የአዲስ አበባ ሆቴልች ለተወጣጡ ሰራተኞች!
-
በጁፒተር ሆቴል!!
-

ቦሌ በአለም ሲኒማ የማንያዘዋልን እሸቱን ስልጠና ታደሙ!!
-
እሁድ ጠዋት ከ3:00 እስከ 6:00
ሰኞ ማታ ከ12:00 እስከ 2:00
-
2.8K views20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 23:38:40 የቤታችሁን ቧንቧ ተመልከቱት::ውሃው ከየት እንደመጣ አስቡት::
-
ውሃው የሚገኘው ጫካ ውስጥ ወይም ተራራ ላይ ወይም ከቤታችሁ ርቆ ሊሆን ይችላል::
-
ወደ ቤታችሁ ግን ራሱ በራሱ አልመጣም::ውሃው እንዲመጣ እናንተ ያደረጋችሁት ነገር አለ::
-
የአምላክ ሀይልም እንደ ውሃው ነው::ባለበት ሁሌም አለ::እኛ ግን ወደ እርሱ ቀርበን በረከቱን ወደቤታችን ማምጣት አለብን::
-
የእርሱ በረከት የህይወት ሁሉ በረከት ነው::ወደ እርሱ መቅረብ ለችግር ሁሉ መፍትሄ ነው::
-
ወደ ፈጣሪ የምንቀርበው በፍፁም በእምነት እና በንፁህ በመንፈስ ነው::
-
መንፈሱ ላይ ያለውን መጥፎ ሀጥያት ይቅር ብሎ የአእምሮውን የጥርጣሬ ሀሳብ ያለፀዳ የፈጣሪ መንፈስ ባይጎበኘው እንዳያዝን::
-
ጥፋቱ እርሱን የፈጠረው አምላክ ሳይሆን የራሱ አለማወቅ ነው::
-
ከምድራችን ከሁሉም ስራ በላይ ስራ ሊሆን የሚገባው የፈጣሪን መንፈስ አሰራር መረዳት ነው::
-
ዝነኛው ሳይንቲስት አልበርት አኒስታይን ብዙ ነገር መረዳት ጥቅም እንዳለው ያውቃል::ባምድ ወቅት ግን "ዋናው ነገር የእግዚአብሔር አእምሮን አሰራር መረዳት ነው::እርሱን ከተረዳን ሁሉም ነገር ቀላል ነው!" ብሎ ነበር::
-
አሰራሩ ልብን ማንፃት እና በሁሉም ነገር አምላክን መፈለግ ነው::ሁሉን ትቶ ፈጣሪን የሚከተል ሁሉ ነገር እርሱን ይከተለዋል::
-
ከአምላክ መራቅ ወደ ችግር ያቀርባል::ወደ አምላክ መቅረብ ከችግር ያርቃል::
-
መንፈሳዊነት አላማው ወደ ፈጣሪ ዘንድ ቀርቦ ሀሳብን እንደ ፈጣሪ ሀሳብ በጎ ማድረግ ነው::
-
እንዲህ ያለ ሰው የህይወት መልካም ነገሮች ይከቡታል::ልቡ ሰላም ነፍሱ ደግሞ ሀሴት ታደርጋለች::በስጋዊ ህይወቱም በቀላሉ ይባረካል::
-
"ለምን አምላክ ወደ እኔ አልቀረበም?" በማለት የሚጠይቅ አንባቢ ካለ እርሱ ራሱ ወደ አምላኩ ስላልቀረበ እንደሆነ ይረዳ::
-
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት
-
የማንያዘዋል ስልጠናዎች!
-
እሁድ ጠዋት ከ3:00 እስከ 6:00
ሰኞ ማታ ምሽት ከ12:00 እስከ 2:00
-
ቦሌ በአለም ሲኒማ
መግቢያ 100
2.8K views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-16 06:52:03 የ13 ዓመት ልጅ ከመደብር ዳቦ ሰረቀ ዘበኛው ይዞት ነበርና ሊያመልጥ ሲል የመደብሩ መደርደሪያ ወድቆ ተሰበረ።
ዳኛው የወንጀሉን ክስ ሰማና ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው!
"የሆነ ነገር፥ ማለትም ዳቦ ሰርቀህ ነበር?"
ልጁ - እያፈረ "አዎን ሰርቀአለሁ"
ዳኛው - "ለምን?"
ልጁ - "አስፈልጎኝ"
ዳኛው - "መግዛት አትችልም ነበር?"
ልጁ - "ገንዘብ አልነበረኝም"
ዳኛው - "ከቤተሰብህ ለምን አትወስድም?"
ልጁ - "እናት ብቻ ናት ያለችኝ፥ እሷም በጠና ታምማ እቤት ተኝታለች"
ዳኛው - "ምንም ስራ የለህም?"
ልጁ - "መኪና እጥበት እሰራ ነበር፥ ነገር ግን እናቴን ለማስታመም አንድ ቀን ከስራ ስቀር አባረሩኝ"
ዳኛው - "ሌሎች እንዲረዱ አልጠየቅህም?"
ልጁ - "በጧት ነው ከቤት የወጣሁ፥ እንዲረዱኝ 50 የሚሆኑ ሰዎች ጋ ሄጄ ነበር፤ አንድም የሚረዳኝ ሰው ግን አላገኘሁም፤ በቃ መጨረሻ ላይ ይህንን
መጥፎ ውሳኔ ወሰንሁ"
ጥያቄው ሲጠናቀቅ ዳኛው ውሳኔ ማስተላለፍ ጀመረ።
እንዲህም አለ
"ዳቦ መስረቅ፥ በተለይ የተራበ ልጅ ዳቦ መስረቅ እጅግ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው፤ እናም እኛ ሁላችንም የዚህ ወንጀል ተጠያቂ ነን። እኔን ጨምሮ
በዚህ ቤት ውስጥ ያላችሁ በሙሉ ወንጀለኛና ተጠያቂ ነን። ስለዚህ እያንዳንዱ በዚህ ችሎት ላይ የታደመና እዚህ ቤት ውስጥ ያለ አስር (10) አስር
ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ማንም ሰው ሳይከፍል መውጣት አይችልም በማለት አስር ዶለር ከኪሱ አውጥቶ ወረቀት ላይ መመዝገብ
ጀመረ።
በተጨማሪ ዳቦ ቤቱ የተራበ ልጅ ለፖሊስ አሳልፎ በመስጠቱ 1000 ዶላር እንዲከፍል ውሳኔ አስተላለፈ።
ይህ በ24 ሰአት ውስጥ ካልተፈጸመ ፍርድ ቤቱ ዳቦ መደብሩን ያሳሽጋል።
ፖሊስም የተራበ ልጅ ፍርድ ቤት በማቅረቡ 1000 ዶላር እንዲቀጣለት ወሰነ።
የተወሰነለትን ገንዘብ ለልጁ ካስረከበ በኋላ ፍርድ ቤቱ ልጁን ህዝብ ፊት ይቅርታ ጠየቀው!
የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ በችሎቱ ላይ የነበሩ ታዳሚዎች ሁሉ በእንባ ተራጩ።
የልጁ እጅ ላይ የነበረው ሰንሰለት ተፈታለት። ዳኛው እንባ እየተናነቀው ሲያወራ ልጁ ያይ ነበር።
---------------------------------------
በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ያለው የፍትህ ስርዓት ግን ምን ይመስላል?
የተራበ ልጅ ዳቦ ሰርቆ ቢያዝ ወንጀሉም እፍረቱም ለህዝቡ ነው
ይህ መልዕክት ልብህን ከነካ እባክህን ለአንድ ሰው ዳቦ ግዛ።
አንተ እያለ ሌላው ጾም ማደር የለበትም።
በዙሪያህ ካሉ ከብዙዎች አንድ ሰው መርጠህ አስደስተው!
ሰው ለመርዳት ሀብታም መሆን አይጠበቅብህም!
ከብዙዎች ትሻላለህና ካለህ ጥቂት ነገር ላጡት አካፍል!
ይህንን ከባድ ጊዜ ተጋግዘን እንለፈው

ይህንን በማረጋችሁ ፈጣሪ ያስብላችኋልና

share በማድረግ ለሁሉም አድርሱ
ዋልተንጉስ


https://t.me/manyazewal_eshetu
https://t.me/manyazewal_eshetu
7.1K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ