Get Mystery Box with random crypto!

ነፍስ ስታፈቅር ምዕራፍ -24 ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ /// የቢላል ህይወት ካለፈ 15ቀን ቢያ | ከመጽሐፍት መንደር💠💫

ነፍስ ስታፈቅር
ምዕራፍ -24

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ


///

የቢላል ህይወት ካለፈ 15ቀን ቢያልፈውም ሲፈን ግን ዛሬም ወደቤቷ አልተመለሠችም።ወላጆቾ ቤት እዛው ክፍሏ ነው ያለችው።ይህ የሆነው ከደረሰበት የሀዘን ስብራት አባቷ እንዲያፅናናት ወይም እናቷ ጉያቸው ሸጉጣ ተስፋ እንዲሰጧት ፈልጋ አይደለም።እዛ ቤት የመሸገችበት ብቸኛው ምክንያት ክፍሏን ፈልጋ ነው ።እዛች ክፍል ውስጥ ቢላል ከ20ቀን በላይ ኖሯል...በሰፊው አልጋ ላይ ከዳር እስከዳር ተንከባሎበታል..እያንዳንድን የክፍል ወለል እየደጋገመ ረግጦታል ፤በሻወር ቤቱ ደጋግሞ ተጠቅሞል....የጠጣባቸው ብርጭቆዎች፤ የተመገበባቸው ሳሀኖች ፤እዛ ክፍል ይገኛሉ።እያንዳንድንን ቢጃማዎን ፤ሠፋፊ ቀሚሶቾን :ቲሸርቶቾን እየቀያየረ ለብሶቸዎል..።አሁንም ሙሉ ክፍሉ..እጅ ያረፈባቸው እቃዎች በጠቅላላ የእሱን ጠረንና ትዝታ አዝለዎል..እና የእሷ እዛ ክፍል በራሷ ላይ ጠርቅማ ስትተክዝና ስታልም መዎል ምክንያቱ ይሄ ነው።

ይሁን እንጂ ጉዳዩ ቤተሠቦቾን በተለይ አባትዬውን ክፍኛ አሳስቧቸዎል።እና ዛሬ ሊያናግሯት ወስነው ክፍሎ ድረስ መጥተዎል።

"ልጄ...አይበቃም...እስከመቼ እራስሽ ላይ ዘግተሽ?"
‹‹አባ አንድ ክፍል ውስጥ ታፍኖ መቀመጥን አንተ እኮ ነህ ያስጀመርከኝ..."
"ለአንቺው አስቤ እኮ ነበር ...ይገድላታል ብሎ ሄኖክ ሲያስፈራራኝ ምን ማድረግ ነበረብኝ...?"
"ቢሆንም የእኔንም ፍላጎት ከግምት ልታስገባ ይገባ ነበረ....ከማታውቀው ሰው ምክር ከመቀበል ይልቅ እኔ ልጅህን ብትማከር ይሻል ነበረ"

‹‹"እሱስ እውነትሽን ነው ...እንደዛ አድርጌ እራሱ መች አዳንኩሽ...እንደው ልጅ እግዚያብሄር ይባርከውና እንደተባለው አድርጎ ቢሆን ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር...?እኔ ያቆምኮቸውን ወጠምሾች አልፎ ክፍልሽ ገብቷል..ከመግባትም ለቀናት ኖሯል....እና እዛው በገዛ ክፍልሽ አንቆሽ ቢሆን ኖሮ...አረ በስመአብ.."ግሽግሽ አሉ፡፡

" ....ግን አላደረገውም...በጣም ስለሚያፈቅረኝ ምን አልባት በበሽታው ተፅዕኖ አንድ ቀን እንዳይገድለኝ በመፍራት ብቻ ቀድሞ እራሱን አጠፋ...ከራሱ ሊጠብቀኝ እራሱን ገደለ ፤ይሄንን ሰው ነበር ሁለታችሁም ስታሳድዱት የከረማችሁት››

"አዎ ልጄ ትክክል ነሽ አጥፍተናለ..ብቻ ነፋሱ በአፀደ ገነት ትረፋ.."

ረጂም ዝምታ.....
"ልጄ"
"አቤት አባዬ"
"አንድ ሌላ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለው..."አሉና እጃቸውን ወደጃኬት ኪሳቸው በመስደድ አንድ ወረቀት አወጡ....
"ይሄ ያንቺን ጋብቻ በተመለከተ ተዋውለን የነበረ ውል ነው...ቀነ ገደብ ሊገባደድ አንድ ወር ብቻ ነው የቀረው.."

ፊቷን በንዴት አጨማደደች"አባዬ አሁን ስለዚህ ጉዳይ ለማውራት አቅሙ የለኝም"

"አውቃለው ልጄ "ብለው ሁለት ቦታ ከዛም አጥፈው አራት ቦታ ቀዳደዱና ወለሉ ላይ በተኑት...ሲፈን በጣም ደነገጠች
"እንዴ አባዬ!! ምን እየሰራህ ነው?"

"ልጄ ሀሳቤን ሁሉ ሰርዤዎለው...በፈለግሽ ሰዓት የፈለግሽውን ማግባት ካለበለዚያም አለማግባት ትቺያለሽ...እኔ ልጄ ደስተኛና ጤነኛ ብቻ እንድትሆን ነው የምፈልገው....ካንቺ የሚበልጥብኝ ምንም ነገር የለም"አሉና ከመቀመጫቸው በመነሳት ግንባሯን በመሳም ወደ ውጭ መራመድ ጀመሩ።

"አባዬ..በጣም ነው የማመሠግነው..ደግሞ ቃል ገባልሀለው…በጣም በቅርብ አስደሳች ዜና አሰማሀለው"አለች ሆዷን በቀኝ እጇ በስሱ እየዳበሰች።
"ይሁን ልጄ..ይሁን...በእኔ በኩል ምንም ብታደርጊ ቅሬታ የለኝም ...ለሁሉም ነገር ከልቤ መርቄሻለው... ደህና ሁኚልኝ..."ወጥተው ሄድ።
///
በማግስቱ…..
በጥዎት ነው ከእንቅልፏ የተነሳችው፡፡ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቀለል ብሏታል።አዎ በሀዘን የጎበጠ ትከሻዎ ቀና ማለት ፤የደፈረሱ ዓይኗቾ መጥራት፤ የተሠነጣጠቀ ልቧ ክፍተቱን ማጥበብ ጀምሮል ...ለዚህ ደግሞ የሄኖክ አባት ድርሻ ቀላል አልነበረም....ቢላል ከሞተ ብኃላ በራሷ ፍላጎት ስልክ አንስታ በመደወል የምታዋራቸው ብቸኛ ሰው ናቸው።እና በደወለችላቸው ጊዜ ሁሉ ከልስልስ አንደበታቸው እየሾለኩ በጆሮዎ የሚሰርጉ የምክር እና የማፅናናት ቃላት በትክክል ልቧ ላይ እያረፉ ሲቀልጡና ከሰውነቷ ሲዎሀድ ይታወቃት ነበር...በዛ ላይ በየሰዓቱ ልዩነት በሚሴጅ የሚልኩላት አጫጭር መልዕክቶች ለተሠበረ መንፈሶ መታሻ ቅባቶች ሆነውላታል።

ዛሬ ግን ከእሷቸው ጋር የምሳ ቀጠሮ አላቸው።ከሁለት ወር ብኃላ ነው በአካል የሚገናኙት።ከዛ በፊት ግን ቀርስ ላይ ከፕሮፌሰሯ ጋር ለመገናኘት ወደ ቤቷ ትሄዳለች..ስለልጅ ልጇ ማውራት ፈልጋለች.በዛ ላይ አራት ሰዓት አብረው ሀኪም ቤት ይሄዳሉ የፅንሱን ጤንነት ለማወቅ.፡፡..የዛሬዎ ቀጠሮ በዚህ አያበቃም 11ሰዓት ደግሞ ከሄኖክ ጋር ትገናኛለች።ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት ለፊት አግኝታው ስለወደፊታቸው እልባት ለመስጠት ስለፈለገች ነው ላግኝህ ያለችው፡፡እሱም በደስታ እየፈነጠዘ ነበር ቀጠሮውን የተቀበለው፡፡

ብቻ ዛሬ ህይወቷን አዲስ አቅጣጫ የምታሲዝበት ቀን ነው።ለዚህ ደግሞ በዙሪያዋ በአውንታም ሆነ በአሉታ ተፅዕኖ ያላቸውን ሰዎች የምታናግረውን አናግራ የምታማከረውን አማክራ የመጨረሻ የመፍሰሻ አቅጣጫዎን ትወስናለች።
///
ወደኘሮፌሰሯ ቤት እየሄደች ሳለ ቤቷ ጋር ስትደርስ መኪናዋን አቆመችና ክላክሱን አንጫረረች…ተዘራ በራፉን ከፈተና ዱላውን እየወዛወዘ ወደእሷ ቀረበ…

"እንዴ እትይ ..እንደው ለመሆኑ ሰላም ነሽ.?.ስልኪቱን ብደውልም እኮ አታነሺም››
‹‹ምነው ችግር ነበረ እንዴ?››አለቸው በመስኮት አንገቷን አውጥታ እጇን ወደእሱ በመሰንዘር እየጨበጠችው፡፡
‹‹ኸረ እዚስ ሰላም ነው...ግን እትይ የአንቺ ነገር በጣም አሳስቦኝ ነው?"
‹‹እኔ ሰላም ነኝ...ከሳምንት ብኃላ ሙሉ በሙሉ ወደቤቴ እመለሳለው"
"ውይ እትዬ እባክሽ ተመለሽ...እባክሽ...መሽቶ ከልነጋ አለኝ እኮ...እንደው እትዬ አትታዘቢኝና በራፍ ከፍቼልሽ ስትገቢና ስትወጪ የምምገው ሽቶሽ እራሱ ናፈቀኝ ልሞት ነው››...ፈገግ አለች"ምን አለ ሰው ሁሉ እንደአንተ የዎህ ቢሆን? አለች በውስጧ
‹‹ደሞዝ ገብቶልሀል አይደል?"
‹‹አይ እትዬ ...አዎ ገብቶልኛል...አንቺ ጋር እየሠሩ የብር ችግር የት አለ..?.ብቻ አንቺ ሀዘኑን በልክ አድርገሽ ..ቃል እንደገባሽው ወደቤትሽ ቶሎ ተመለሺ"
‹‹እሺ ..አሁን ቸው..."መኪናዎን አስነስታ ሄደች።
///
ፕሮፌሰር ቤት ስትደርስ 3 ሰዓት ሆኖ ነበር።እንደምትመጣ ስለሚታወቅ ጠረጰዛው በምግብ ተሞልቶ ነበር የጠበቃት።አቀባበላቸው ደማቅ፤ መስተንግዶቸው ልብ ሚያሞቅ ፤እንክብካቤያቸው ልክ እንደንግስት ነበር.፡፡
.ከቁርስ ቡኃላ ሁለቱም ሳይነጋገሩ ተያይዘው ቢላል ክፍል በመግባት ዕቃዎቹንና ስዕሎቹን እያዩና እዳበሱ ሲያለቅሱ እና እርስ በርስ ሲፃናኑ አረፈዱ.፡፡በመጨረሻም አንድ የተቀደሰ ሀሳብ በሁለቱም ተከሰተላቸው .በእምሮ ህመምተኞች ላይ የሚሰራ ፋውንዴሽን በስሙ ለማቋቋምና በዛ ፋውንዴሽንም ስራዎቹን ቋሚ ስፍራ እንዲያገኙ ለማድረግ አብረው ሊሰረሩና ሙሉውን ወጪ የሲፈን ካማፓኒ ሊሸፍን ተስማሙ፡፡በዚህም ሁለቱ ከብዙ የሀዘን ቀናት ቡኃላ ደስ ተሰኙ፡፡.አምስት ሰዓት ሲሆን አብረው ሲፈን ለፅንሱ ክትትል ወደምታደርበት የግል ሆስፒታል ሄዱ፤