በረንዳውን ለቃ ወደእነሱ ተጠጋች..በውድቅት ለሊት ባልተለመደ ሁኔታ ግቢ ውስጥ ሲያዬት ሁለቱም ግራ በመጋባት እርስ በርስ ተያዪ...አንደኛው ወደእሷ ተራመደ "እመቤቴ እባክሽ ወደመኝታሽ ተመለሺ...እንድትወጪ እንደማንፈቅድልሽ ታውቂያለሽ..ለዛውም በዚህ ሰዓት?" "እኔ መች ልውጣ አልኩ?" "ይቅርታ አድርጊልኝ እንደዛ መስሎኝ ነው...ታዲያ ምን እንርዳሽ?" ‹‹አይ የሆነ የመንጓገጓት ድምፅ ግቢው ውስጥ የሠማው መስሎኝ ነው..!ሁሉ ነገር ሰላም ነው ግን?" ….ፈገግ አለ ‹‹