Get Mystery Box with random crypto!

ማንችስተር ዩናይትድ ቤት የተለመደ ነገር ነው! መንሱር አብዱልቀኒ ማጓየር አሰቸጋሪ ጊዜ እያሳለፈ | ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ

ማንችስተር ዩናይትድ ቤት የተለመደ ነገር ነው!

መንሱር አብዱልቀኒ ማጓየር አሰቸጋሪ ጊዜ እያሳለፈ በነበረበት ጊዜ ለምን ማጓየር እንዲ ያለ አቋም አሳየ በሚል ፕሮግራም ሰርቶ ነበር

በወቅቱም ተጠያቂ ካረጋቸው ነገሮች መካከል የዩናይትድ ደጋፊዎችን ጠቅሶ ነበር፤ ከሌላ ክለብ ባልተናነሰ እሱ ላይ ሲቀልዱ እንደነበር አንስቷል

አሁንም አንድ ስህተት ለሰራ ልጅ መጥፎ አስተያየት አይገባውም፤ ለክለባችን ዩናይትድ መጫወት አስተያየት እንደመስጠት ቀላል አይደለም

ቫንዳይክ በባለፈው ጨዋታ ትልቅ ስህተት ሰርቶ ክለቡን ዋጋ አስከፍሎት እንኳን ያን ያክል የሰላ ትችት አለደረሰበትም ወደ ዩናይትድ ስንመጣ ግን አንድ ስህተት ልጁ አቅም የለውም ያስብላል

ይህ ነገር አንቶኒም ራሽፎርድም ላይ ይሰተዋላል፤ ማንችስተር ዩናይትድን እሰከወደድን ድረስ ለተጫዋቾች ክብር ያስፈልጋል ልክ እንደ ተቃራኒ ደጋፊ የክለባችንን ተጫዋቾች ላይ መሳለቅ አግባብነት የለውም!

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans