Get Mystery Box with random crypto!

ኤሪክ ቴን ሀግ ስለ አንቶኒ ለFootballDaily ይህንን ብለዋል..... 'አንቶኒ እራሱን አስ | MANCHESTER UNITED

ኤሪክ ቴን ሀግ ስለ አንቶኒ ለFootballDaily ይህንን ብለዋል.....

"አንቶኒ እራሱን አስቀድሞ አሳይቷል። በሻምፒዮንስ ሊግ ፣ በብራዚል ብሄራዊ ቡድን እናም እሱ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነው"

"ብራዚል በጣም ጥሩ ችሎታ ያላቸው በርካታ ተጫዋቾች አሏት።እነሱ ሁለት ወይም ሶስት ቡድኖችን መምረጥ ይችላሉ እናም እሱ ጫናውን መቋቋም ይችላል ለቡድናችን ፈጥነት እና ፈጠራን ያመጣል"

"ለእሱም(ለአንቶኒም) ይህ አዲስ ጅምር ነው እና ከቡድኑ ጋር መላመድ አለበት ወደ ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ጥንካሬ ወደ ሚጠይቀው ቦታ ነው የመጣው ነገርግን እሱ ቶሎ እንደሚላመድ እርግጠኛ ነኝ"

ቴን ሃግ አንቶኒ በዋጋም ምክንያት የሚኖረውን ጫና ይቋቋማል ወይ ተብሎ ሲጠየቅ ይህንን ምላሽ ሰጥቷል......

"እሱ ይህን መቋቋም ይችላል እሱ ለእግር ኳስ ነው የሚኖረው እናም የሚደሰትበት ነገር ነው በዛ ላይ ትኩረት በማድረግ እና የቡድኑን ጨዋታ ለማሻሻል እየሰራ ነው ይህን የሚገጣጠም ከሆነ ብቃቱን የምትመለቱት ይሆናል።

@Starboyana
@man_united_ethio_fans