2022-04-22 21:58:51
ወርቁን ማን ሰረቀው
ክፍል ዘጠኝ
(ነኢማ ኸድር)
........በጣም ተጎድተሻል እያለች ወደኔ መጣች
ግራ ገባኝ ስለማነው እምታወራው ከሰአታት በፊት ለካ ጤነኛ ነበርኩ ገረመኝ እኛ ሰወች እንዲህ ደካማ መሆናችንን ሳስብ አምላኬን ለመጥራት ተሸማቀኩ ለካ እንዲ ደካማ ነን እንደምንም ለመናገር ልሞክር ስል አፌን ማንቀሳቀስ ተሳነኝ ምግብ ስላልበላሁ ነው መሰለኝ እናቴ እንደነቃሁ ስላወቀች እንደ ምንም እራሷን አረጋግታ ወደ ክፍሉ ገባች ገና አልጋው ላይ ስታየኝ እሪታዋን አቀለጠችው እኔም ድምፄ ባይወጣም እንደተኛሁ በቀኝ በግራ አጣደፈኝ እንደማይነጋ የለምና ነጋ ጠዋት ላይ ሂክማ የምትባል ጎረቤታችን ቁርስ ሰርታ ይዛልኝ መጣች ገና ሳያት ገረመኝ ሴትየዋ ከኛ ቤት ፊት ለፊት እንደሆነች አቃለሁ እሱንም ያወኩት አንድ ቀን ከሰፈር ወጥቼ ታክሲ ስጠብቅ ሸኝታኝ በአይን እንደምታቀኝ ነገረችኝ እንደዛ እያወራን ነው ጎረቤቴ መሆኗን ያወኩት
ገና ስትገባ ሳቄ መጣ አይ ሀበሻ ለካ ለችግር ደራሽ ነው የያዘችውን ዘንቢል እያስቀመጠች "ፈርሁ እንዴት ነሽ? አሁን ለውጥ አለሽ?ሀኪሞቹ ምን አሉሽ?" የጥያቄ መአት አዘነበችብኝ እስቲ ፍረዱ አሁን ለህመምተኛ እንዲ ይጠየቃል ያውም ለንደኔ አይነቷ ሆሆሆሆ
አክስቴ ከአፏ ቅብል አርጋ አልሀምዱ ሊላህ ደና ነች እንደው በጊዜ ታውቆላታል አልሀምዱሊላህ ማለቱ ነው የሚበጀው እያለች ወደውጪ ወጣች
ወዲያው ዶክተሩ በሩን ከፍቶ ገባ አሰላሙ አለይኩም ብሎ ወደኛ መጣ ሂክማ ድምፁን ስትሰማ በቅፅበት ዞር ብላ አየችው መርዋን ብላ ተነሳች ሁለቱም ለረዥም አመት እንዳልተገናኙ ያስታውቃል ሂክማ ከመቀመጫዋ እየተነሳች "ያ አላህ 7 አመት ቡሀላ ማለት አዏ ግን በጣም ተለውጠሀል"እያለች በአግራሞት ታየዋለች ግን ሁለቱም እንደመነፋፈቃቸው አልተጨባበጡም አልተቃቀፉም እሱም በግርምት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ካገላበጣት ቡሀላ
"ትዳር ተስማምቶሽ የለ እንዴ ሂኩ በአላህ እንዴት እንደናፈቃቹሁኝ አክስቴ እንዴት ናት ? "ሲል ገባኝ
እህህህ የ አክስቱ ልጅ ናት እህህ ትንሽ ካወሩ ቡሃላ"ኦኦ ፈርሁ እንዴት አደርሽ አሁን እየለቀቀሽ ነው ሳናስበው ስለተገናኘን ነው እሺ እንዲህ ቁመን ያወራነው"እያለ ወንበሩ ላይ ተቀመጠ ሂክማ ወደኔ እያየች ጥሩ ጎረቤቴ ናት ተንከባከብልኝ ብላው ፈገግ አለች
ዶክተር መርዋን ወደኔ እያየ እሷ ከረዳቺኝ አለ
"ምን ለማለት ፈልጎ ነው "ማለት አለች ሂክማ ዶክተር መርዋን ከተቀመጠበት እየተነሳ ምግብ እና መጠጥ በደንብ የምትወስድ ከሆነ ነው"እያለ ለመሄድ በሩን ከፈተው እና እንደመመለስ እያለ ኦ ሂክ ስልክሽን ንገሪኝ ስራ በሌለ ጊዜ እንገናኛለን"ብሏት ስልኳን ተቀብሏት ወጣ ሂክማ የሌለ ተንከባከበችኝ ከባሏ ጋር እየተቀያየሩ ሳምንቱ ሙሉ ከ እናቴ ጋር ቆይተው ይሄዳሉ ሰው እንዴት ለማያውቀው ሰው እንደዚህ ይሆናል ወይ ሀበሻ እንደምቀኝነቱማ እኮ ሆዱ ባዶ ነው ከሁሉም ግን የገረመኝ የዶክተር ተብዬው ነው ስራ በሚወጣበት ሰአት ከኔ ጋር
ከ 2 እስከ 3 ሰአት ይቀመጣል እና ዘና አርጎኝ እናቴ ስትመጣ ይሄዳል የሌለ ምርጥ ሰው ነው እርጋታው አወራሩ በቃ ሁሉ ነገሩ ቀልብ ይመስጣል ዶክተር መርዋን አላገባም እንደውም እሱ እኔ ጋር ሆኖ ሂክማ ከመጣች ስለትዳር እያወራች ታሸማቀዋለች እንደውም አንድ ቀን በቁም ነገር ጠየኩት ???
የኔ ሀዋ ገና አልተፈጠረችም ብሎኝ ጥሎኝ ወጣ እንዲህ እንዲህ እያልን ሳምንቱ አልቆ ከሀኪም ቤት እምወጣበት ቀን ደረሰ ሂክማ ከነ ባለቤቷ አክስቴ እና እናቴ ሁነው መተው በነ ሂክማ መኪና ወሰዱኝ አማር ግን ሳምንቱን ሙሉ አልመጣም አልጠየቀኝም ሀጂም ኢነብንም አላየሁዋቸውም ለምን ግን አንዳቸው እንኳን አልመጡም አማር ምን ሆኖ ነው የጥያቄ መአት ጭንቅላቴ ላይ አዘነብኩበት ....
የነ ሀጂ ቤተሰቦች እየገረሙኝ ሳለ 3 ቀን ሞላኝ ህመሜ በደንብ ባይለቀኝም ግን እንቀሳቀሳለው ዛሬ ግን ገና ከጠዋቱ ጭንቅላቴን ወጥሮ ይዞኛል እንደነገሩ የአቅሜን ሰርቼ ፍራሽ ላይ በጎኔ ተኝቼ ቴሌቪዥን እየተመለከትኩኝ ሳለ የጊቢው በር ተንኳኳ እማዬ ከ አክስቴ ጋር ከትንሽ ደቂቃ በፊት ወጥታለች በሩን ለመክፈት ወደ ውጪ ወጣሁ የመግቢያውን በር ጨርሼ በረንዳውን እንዳለፍኩ ጭልም አለብኝ እዛው ቁጭ አልኩኝ በሩ አሁንም እየተንኳኳ ነው እንደምንም በሩን ከፈትኩት ዶክተር መርዋን ነበር
"አሰላሙ አለይኩም ፈርሁ ደና ነሽ በአላህ አልተቀየምሺኝምማ" እያለ ፈገገ አለ እኔ ልውደቅ ልቁም እያልኩ ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ነው ሳላስበው የ መርዋንን ክንድ ጥብቅ አድርጌ ያዝኩት "ምነው ፈርሁ አሞሻል እንዴ "እያለኝ ደገፈኝ መቆም ስላልቻልኩ "ወደቤት እንግባ" ብዬው ደገፈኝ እና ወደቤት ልንገባ እግሬን ሳነሳ ተዝለፍልፌ እጁ ላይ ቀረሁ ከትንሽ ደቂቃ ቡሀላ አማር በመኪና አደጋ እንዳረፈ ተነገረኝ የሆነ የማቀው ሰው ይመስለኛል እነ አማር ቤት ወሰዶኝ ጊቢው በሰው ታፍኗል ሀጂ እንባቸው ብቻ ይፈሳል የአማር ጀናዛ
(አስክሬን)ተሸክመው ሲያወጡት ኢነብ ወንድሜ ብላ ስትጮህ አይኔን ከፈትኩና "አሚሚሚ"ብዬ ጮህኩኝ እናቴ አክስቴ መርዋን እና ሂክማ ዙርያዬን ከበውኛል ሁሉም ተጨንቀዋል መርዋን ወደኔ እየተጠጋ "ምንድነው ፈርሁ ማነው" እያለ በ አትኩሮት ያየኛል በሰለለ ድምፅ "እማዬ አማር ሞተ" አልኳት ከተቀመጠችበት ብድግ እያለች "የምን ሞት ነው ጠዋት መቶ እኔ አንተ አትገባም ብዬ የመለስኩት" እያለች አፈጠጠችብኝ
መርዋን በአትኩሮት እየተመለከተኝ ድምፁን ቀነስ አርጎ ጎደኛሽ ነው" አለኝ እንዴት እንዲ ሊል ቻለ? ጭንቅላቴን ከቀኝ ወደግራ ነቅነቅ አረኩት መርዋን ከ ዶክተርነት በዘለለ የ ስነ ልቦና ሀኪም ና አማካሪ ነው ይህንንም ያወኩት ሀኪም ቤት በነበርኩበት ወቅት ነግሮኝ ስለነበረ ነው እነ አክስቴን ወደ ስራቸው እንዲመለሱ አሳምኖ አጠገቤ መቶ ያወራኝ ጀመር "አማር ምንም አልሆነም ስለሱ ስለተጨነቅሽ ነው አንዳንዴ አይምሮአችን ስለ አንድ ሰው ከመጠን በላይ ሲያስብ እራሳችንን እንስታለን ከዛ የምንነቃው ስለዛ ሰው አይምሮአችን መልክት ሲልክ ነው እያለ ብዙ ተነተነልኝና በመሀል ዝም አለ ወንድን በሙሉ አይኔ ከ አንዴ በላይ ማየት አልወድም ሀይማኖተኛ ምናምን ሆኜ ሳይሆን በቃ ደስስ አይለኝም መርዋን ከፊትለፊቴ ተቀምጧል ሁለታችንም ዝም ብለናል ዝምታውን ለመስበር ሁለታችንም እኩል "ግን" አልን መገጣጠማችን ገርሞን ሳቅን " ግን ምን ልትይኝ ነበር " አለኝ እየፈገገ " አንተ ምን ልትል ነበር " አልኩት ጥያቄውን በ ጥያቄ ስመልስ "አንቺ ንገሪኝ" ቅድሚያ ለ ሴት" እያለለ አሁንም ፈገገ " ታካሚዋን በ ጥያቄ መወጠር ክልክል ነው" ብዬው ከት ብዬ ሳኩኝ ነገረ ስራዬ ስለገረመው እየተያየን ሳቅን መርዋን በቅፅበት ሳቁን አቁሞ "ግን እስከዛሬ ለምን አላገባሽም ? ማለቴ ቆንጆ ነሽ ስርአት አለሽ ታዲያ እንዴት ?" ብሎኝ ፈገግ አለ ጥያቄው ቢያስደነግጠኝም ፈገግ እያልኩ "የኔ አዳም ገና አልተረገዘም" ብዬው ሙድ ያዝኩበት እንደ ድንገት በሩ ተንኳኳ አክስቴ በሩን ልትከፍት ወጣች " ግቡ "ስትል ይሰማል ማን ነው?
የሳሎኑ በር እየተንኳኳ.....
ይቀጥላል.......
➥ሼር እንዳይረሱ
JOIN ⇒ @mame_graphics
293 viewsΜαμε, 18:58