Get Mystery Box with random crypto!

አንዱ አጋዘን በባህሩ ዳርቻ ላይ ቆሞ እንዲህ ሲል ቀጭኔን ጠየቀው #አጋዘን ፡ የባህሩ ውሀ ጥል | Malcolm x ethio

አንዱ አጋዘን በባህሩ ዳርቻ ላይ ቆሞ እንዲህ ሲል ቀጭኔን ጠየቀው
#አጋዘን ፡ የባህሩ ውሀ ጥልቀት ምን ያህል ይደርሳል ?
#ቀጭኔውም ፡ እስከ ጉልበቴ ድረስ ይሆናል አለው

አጋዘኑም ዘሎ ባህሩ ውስጥ ገባ ወዲያው ውሀው ሙሉ በሙሉ ሲውጠው ጭንቅላቱን በመከራ ከውሀው ውስጥ ለማወጣት ደፋ ቀና እያለ እንደምንም ከውሀው ዳርቻ ደርሶ የተወሰኑ ትንፋሾችን እንደሰበሰበ ቀጭኔው ላይ እንዲህ ሲል ጮኸ ውሀው ጉልበት ላይ ይደርሳል አላለከኝም እንዴ ሲለው ቀጭኔውም አዎ እስከ ጉልበቴ ይደርሳል ብዬሀለው አለው

^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ቀጭኔው ትክክል ነበር የተሳሳተው ራሱ አጋዘኑ ነው ሌሎች ያሉበት ሙያ ላንተ አይሳካልህም ይሆናል እነሱ ግን ውጤታማ ሆነውበታል

በህይወትህ አንድ ሰው ሰርቶት የተሳካለት ነገር ላንት ይሳካልሀል ማለት አይደለም
ያንተ ህይዎት እንደሌሎች አይደለም
የእነሱ ልምድ ባንተ አትመዝነው
አንተን የሚያስደስት ሁሉ እነሱን አያስደስትም አንተን የሚያስከፋህ ነገር ሁሉ እነሱን አያስከፋም

የሁሉም ሰው እጣፈንታው ይለያያል