Get Mystery Box with random crypto!

#ልጅ መውለድ ሀላፊነት ነው# ልጅ በመውለድ ውድድር ውስጥ መግባት የለብንም የተሻለ ትምህርት አግ | Malcolm x ethio

#ልጅ መውለድ ሀላፊነት ነው#

ልጅ በመውለድ ውድድር ውስጥ መግባት የለብንም የተሻለ ትምህርት አግኝተው እና በቂ ምግብ በልተው ማደግ አለባቸው መንከባከብ የምንችለው ልጅ ያክል መውለድ አለብን
የልጆቻችን ሃላፊነት የተሰጠን ለእኛ እንደመሆኑ ነገ ያስጠይቀናል
ልጅ ማሳደግ በጣም ፈተና ነው ፍላጎቶቻቸውን ማማላት ባይቸግረንም እንኮን በጥሩ ስነ-ምግባር ማሳደግ ግን አልቻልንበትም ልጅ ማሳደግ ማለት ሚፈልገውን ገንዘብ መስጠት ብቻ አድርገን ምናስብ ሰዎች አለን
አንዳንዶች ደግሞ ምን ይላሉ በድሮ ጊዜ አባቶቻችን እኮ 10/20 ልጆች ይወልዱ ነበር ይሀው አድገናል ሲሉ ይሰማሉ ልክ በዛው ልክ በየቦታው የማይተዋወቁና የማይፈላልጉ ልጆች በርሀብና በሱስ፣ ከትምህርት አለም የራቁ ጎዳና የውድቁም እናዳሉ ዘንግተውታል
ብቻ ነገሩን ለማሳጠር ልጅ ስንወልድ ስለ ሚመገበው ምግብ ብቻ ሳይሆን እንዴት ፈጣሪውን አሳውቀን እንዲፈራው ማድረግ ብቁ ዜጋ ማድረግ ሀይማኖቱን እንዲወድ የሌላውንም ሀይማኖት እንዲያከብር ሀገሩን እንዲወድ ወላጆቹን አክባሪ የሌላውንም ሰው ወላጅ እንዲያከብር ማስተማር አለብን ሰውን በሰውነቱ እንዲያከብር ጎረቤቱን አክባሪ ዘረኝነትን እንደቆሻሻ እንዲጠየፍ ከውሸት ከጥላቻ ከራስ ወዳድነት ከምቀኝነት ራሱን ከፍ ከፍ አርጎ ማየት እንደሌለባቸው ማስተማር አለብን .............
ልጆች ስጦታ እንደመሆናቸው በተሰጠን ስጦታ ድግሞ መጠየቃችን አይቀርም!