Get Mystery Box with random crypto!

''''''ኢየሱስ ያድናል አጋጣሚውን ተጠቅማችሁ በድፍረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክር | የኦርቶዶክስ ጥቅሶች

""""""ኢየሱስ ያድናል

አጋጣሚውን ተጠቅማችሁ በድፍረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስን አታውቅም ኢየሱስን አሰብክም የሚል የሞኝ ከበሮ አትደልቁ! ይህንን እንድል ያደረገኝ በአንዲት ግለሰብ ሰበብ ብዙ ሚሊዮን ተከታይ ያላትን ቤተክርስቲያንን ብዙ ሲሉ ስላየው፣ዝም ማለት አልፈለኩም።ምክንያቱም ያደኩበት ነው።


“ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም!

የዛሬ 2000 ዓመት ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ እጅመንሻ ይዛ ለተገኘች፡

ኢየሱስ ክርስቶስን በሕፃንነቱ ሲሰደድ ለተቀበለች፡

ኢየሱስ ባረገ በዓመቱ በጃንደረባዋ በኩል በስሙ ለተጠመቀች፡

ከማንም በፊት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን እምነት በንጉሥዋ በኢዛና በኩል በይፋ ለገለጠች፡

በዓለም ጥንታዊዉን በእጅ የተጻፈ የኢየሱስ ወንጌል በአባ ገሪማ ገዳም ለያዘች፡

በዓመት ከ1825 ጊዜ በላይ የኢየሱስ ወንጌል እንዲነበብ ሥርዓት ለሠራች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፡-

“ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም፡፡
ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል ሆኖ ነው እንጂ ነገሩ፡፡ #ሼር ማድረጎን አይርሱ


https://t.me/makiba_16