Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ለሰው ቢተማመን ምነው!!ባልና ሚስት ወደ ኢጣልያን እየበረሩ ሳለ የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ | ማኅቶተ ቶኔቶር ፩

ሰው ለሰው ቢተማመን ምነው!!ባልና ሚስት ወደ ኢጣልያን እየበረሩ ሳለ የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያ አንድ ነገር ተናገረ " ክቡራንና ክብራት ይህን ስናገር ባጣም አዝናለው አንደኛው የአውሮፕላኑ ሞተር አይሰራም ሁለተኛውም ቆሞአል በጥቂት ደቂቃዎች የመከስከስ አደጋ ይደርስብናል ግዜው የመናዘዝና የይቅርታ ግዜ ነው ጸልዩ ንስሐ ግቡ ማስተካከል ያለባችሁን ነገር ሁሉ አስተካክሉ " አላቸው።ዳኒ የሚስቱን የኤልሳቤጥን እጅ ይዞ.. የኔ ማር ይቅር በይኝ በጣም ይከብዳል ታውቂያለሽ እህትሽ ሳምራዊት ከእኛ ጋር ከምትኖረው አብሬያት እተኛ ነበር እሷ በጣም ልክ እንደ እንዝርት ናት ብዙ ግዜ አስወርዳለች ከጣልያን ስንመለስ አንቺን በመርዝ ገድላ ወደ አሜሪካ ሄደን አብረን እንድንኖር አቅዳለች። እባክሽ ይቅር በይኝ ሲላት...ኤልሳቤጥ... ምንም ማለት አይደለም ይቅር ብየሃለሁ ግን እኔም የምናዘዘው ነገር አለኝ አለች .. እባክህ ይቅርበለኝ.. እእእእ ካሉን ሦስት ልጆች መሃከል ሁለቱ ማለት ዮሐንስና አስቴር ያንተ ልጆች አይደሉም ያንተ ልጅ ቪክቶሪያ ብቻ ናት የቀሩት የውድ ጓደኛህ የኤሳው ናቸው። የኔ ማር ታስታውሳለህ አንዴ ሌቦች አልዘረፉህም ነበር ?አቶ ዳኒ... አዎ የኔ ማር አስታውሳለሁ ኤልሳቤጥ.. ....ሌቦች እንዲዘርፉህ ያደረኩት እኔ ነበርሁ ምክኒያቱም ቦይ ፍሬንዴ አሌክስ የትምህርት ክፍያ አልነበረውም ያየተዘረፍከው ገንዘብ ለእሱ የትምህርት ክፍያ አውሏል። ታውቃለህ ከጣልያን እንደተመለስን አንተን ለማስገደል ሰው ቀጥሬያለሁ ..ይቅር በለኝ የእኔ ውድ ዳኒ.. ምንም አይደል ይቅር ብዬሻለው አለ።ድንገት የአውሮፕላኑ ካፒቴን በድምፅ ማጉያው "እናንተ ልዩ እምትገርሙ ናችሁ ፈጣሪ ፀሎታችውን ሰምቶዋል ሁለቱም ሞተሮች በትክክል መስራት ጀምረዋል በሰላም እናርፋለን አለ።ሁሉም ተሳፋሪዎች ከመደሰት ይልቅ ፀጥ አሉ። አንድ ተሳፋሪ በድንገት ብድግ አለና አንተ አብራሪ ስማ እባክህ ማረፍ የለብንም አውሮብላኑን ከስክሰው ጣለው ጣለው ሲልሁሉም ተሳፋሪዎች በአንድ ድምፅ ፈጥፍጠው ከስክሰው ብለው ጮኹ! ለሰው ሞት አነሰው ...ቀበሮ
@mahtotetonetor2