Get Mystery Box with random crypto!

ማሕቶት

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahtot — ማሕቶት
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahtot — ማሕቶት
የሰርጥ አድራሻ: @mahtot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 357
የሰርጥ መግለጫ

እይታዎች
ጥበባዊ ምልከታዎች
አጫጭር ጽሁፎች
ፍልስፍናዎች
ምን እናርግ
ታላላቅ ጥቅሶች
For any comment use
@aesoph

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-09 19:30:08
Shocked?

@mahtot
32 viewsMokap, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 22:42:42 የአጎቴ አነቃቂ ንግግሮች እና የእኔ መፍዘዝ!

እንደማንኛውም ዕድሜው ለማትሪክ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ወጣት፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት መጥቶልኝ፣ ዩኒቨርሲቲ የመግባትና ተመርቆ የመውጣት ዕድል ገጥሞኛል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ አጎቴ ብዙ ምክርና ትንሽ የኪስ ገንዘብ በመላክ እያማረረ አስተምሮኛል። (አጎቴ ግን ለሰዎች ሲናገር “እያዝናናሁ አስተማርኩት” ነው የሚለው) የሚልክልኝ ብር በጣም ከማነሷ የተነሳ፣ አንዳንዴ እንደ ደሃ የሻምፖ ዕቃ፣ ኪሴን አለቅልቄ ነበር የምጠቀምባት።

ተመርቄ እንደወጣሁ አጎቴ ድል ያለ ድግስ ደግሶ፣ ያንን ሁልጊዜ ፍርድ ቤት ሲሄድ የሚለብሰውን ሰማያዊ ኮትና ሱሪውን ለብሶና ነጭ ከረቫት አስሮ ፣ ለታዳሚው ረዘም ያለ የመክፈቻ ንግግር አደረገ። “አብርሃም ከድሮውም ገና ከልጅነቱ አንጎሉ ለትምህርትና ለነገር እንዲሁም ለእንስቶች ጨዋታ ክፍት ነበር፤ እንሆ አሁንም ከታላቁ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ ተመርቆ አኩርቶናል” አለ። ታዳሚው ቀልቡንም ዓይኑንም ወደተዘጋጀው ቡፌ እንደላከ፣ በየአራት ነጥቡ ያጨበጭብ ነበር። ወደጆሮው ጠጋ ብዬ ‹‹ሳይኮሎጂ አይደለም አጎቴ ሶሾሎጂ ነው›› ብዬ አረምኩት! ወደኔ ገልመጥ ብሎ ‹‹ተወው ይኼ ሕዝብ የወሬ ጅራት ይዞ ነው የሚሮጠው … ምናለ በለኝ ‹ሎጂ› የሚለውን ብቻ ነው የሚያስታውሰው›› አለኝ ! እውነትም ታዳሚው ከበላና ከጠጣ በኋላ ‹‹በምን ሎጂ ነበር የተመረቅኸው?›› እያለ ይጠይቀኝ ነበር። ኑሮና ዕድሜ አጎቴን በሳይኮሎጂ ሳያስመርቁት አልቀሩም!

እንደአብዝሃኛው ኢትዮጵያዊ ተመራቂ ሁሉ እኔም ሥራ አጥቼ ለአንድ ዓመት ተቀመጥኩ። በዚህም አጎቴ በጣም ከመበሳጨቱ የተነሳ እቤት ተቀምጨ፣ ወይም አየር ልቀበል ብዬ የሰፈራችን ልጆች የሚቆሙባት ሱቅ ቆሜ ባዬኝ ቁጥር ‹‹አሁን እኔ ሰው አስመረኩ ነው የምል ወይስ ሐውልት አስመረኩ?›› እያለ ያጉረመርማል።
እንዲያው ‘ጨለምተኛ’ አልባልና፣ የአገራችን ሥራ አጥነት በዚህ ከቀጠለ በቅርቡ ተመራቂዎች ‹‹እንኳን ደስ ያላችሁ! ›› የሚለውን መዝሙር እንደሙሾ ደረታቼውን እየደቁ መዘመራቼው አይቀርም!

ሥራ አጥቼ በተቀመጥኩባቸው ጊዚያት ከምንም በላይ ያስመረረኝ እና ያፈዘዘኝ ‹‹የአጎቴ አነቃቂ ንግግር›› ነበር። አንድ ቀን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ይዞ መጣና እፊቴ እንደምንጣፍ ዘረጋግቶ ‹‹ ተመልከት ›› አለኝ። እኔ ደግሞ የሥራ ማስታወቂያ መስሎኝ ጋዜጣውን አዬት አደረኩት ‹‹ሁለት እጅ የሌለው የእንጨት ባለሙያ ›› ይላል …ጋዜጣው ላይ በአንድ እግሩ ጣቶች፣ ባለባርኔጣውን ሚስማር ፣ በሌላኛው እግሩ፣ መዶሻ የያዘ አካል ጉዳተኛ ኩርሲ ወንበር ሲሠራ ይታያል። አጎቴ ኮስተር ብሎ ‹‹ አዬህ አብረሃም፣ አንተ በእግርህ ሮጥ ሮጥ ብለህ ሥራ መፈለግ ሰንፈሃል፣ሰው በእግሩ የሚሠራውን ተዓምር አዬህ አይደለም? …እንድትነቃቃ ብዬ ነው ጋዜጣውን የገዛሁት …በእርግጥ አዋጅም ታትሞ ከሆነ ብዬ ነበር፤ አለና ጋዜጣውን አጣጥፎ ሄደ።

ሌላ ቀን ወደቤት ስገባ፣ አጎቴ በእጁ በያዘው ሪሞት ወደ 15 ኢንች ቴሌቪዥኑ እየጠቆመኝ ‹‹ና ተቀመጥ ! እግርህ ጥሩ ነገር ላይ ነው ዛሬ የጣለህ …. ተመልከት …እየው ይኼ ሰውዬ እንዳንተው ሰው ነው …ግን በምን እንደሁ እንጃ እንደምታየው እግሩ አይሠራ ፣እጁ አይንቀሳቀስ ፣ አፉ አይናገር፣ ከንፈሩ አይላወስ …. ዓይኑ ብቻ ናት የምትርገበገበው:: አንተ በጥቅሻ የሰፈሩን ልጃገረድ ስታማልል ፣ እሱ በጥቅሻ ሰማዬ ሰማያት ዘልቆ፣ ፀሐይ አልቀረው ጨረቃ ….እስተ ሰባተኛው ሰማይ ዘልቆ ስንት ሳይንስ፣ ስንት ምርምር ሠራ !…አሁን አንተ ተሱ ታንሳለህ አብርሃም ? እንድትነቃቃ ነው ይኼን የምነግርህ …አዚምህ እንዲለቅህ ›› ቴሌቪዥኑ ላይ ፈጥጨ ቀረሁ ። ከሱ አታንስም ያለኝ ታዋቂው እንግሊዛዊ ፊዚስት እና ኮስሞሎጅስት ስቴፈን ሃውኪንግን ነው! የፊቱን ስሜትና የዓይኑን እንቅስቃሴ እየተረጎመ በሚተነትን የዘመነ ዊልቸሩ ላይ እጥፍጥፍ ብሎ ተቀምጦ ስለብላክ ሆል የሠራው ምርምር ይተረክለታል … ምነው ይቺን ዊልቸር ባገኘኋትና ሸጨ የዶሮ እርባታ በጀመርኩ እላለሁ በውስጤ!

ሌላ ቀን ሥራ ፍለጋ ስንከራተት ውዬ በድካም ወደቤት ስንከላወስ…አጎቴ ከኋላ ጠራኝ ‹‹አብርሃም …ጠብቀኝ አንዴ የማሳይህ አለኝ …›› ኮቱ እስኪውለበለብ እየገሰገሰ መጣና ቁና ቁና እየተነፈሰ፣ በእጁ የያዘውን የግል ጋዜጣ ነፋስ ጋር እየታገለ መንገድ ላይ ዘረጋጋው …‹‹ስኬታማ ሥራ የሠሩ የዓለማችን አስደናቂ የአካል ጉዳተኞች›› ከሚል ርእስ ሥር አንዷን እየጠቆመ …. ‹‹ይችን ሴት ታያታለህ ?….ይች ሴት…እ… ?ሁለት እጅ የላትም ….አዬህ … ! እጇን አጣጥፋ እንዳንተ እቤት ቁጭ አለች ?…አለች ወይ? ››
‹‹እጅ ከሌላት እንዴት እጇን አጣጥፋ ቁጭ ትላለች አጎቴ? ››
ጥያቄዬን እንዳልሰማ አለፈኝና ….
‹‹ምን እያረገች ነው ….?አንብብልኛ?! ›› ብሎ አፈጠጠብኝ። ጀሲካ የምትባል በእግሮቿ አውሮፕላን የምታበር ሴት ታሪክ ነበር…ጭራሽ ጋዜጣው ‹‹ብዙዎች እግርና እጅ እያላቸው ለሥራ በሰነፉበት ዘመን …ይች አሜሪካዊት አካል ጉዳተኛ ግን ››….ይላል ! ጸሐፊው አጎቴ መሰለኝ! እንዳቀረቀርኩ ወደቤት መንገዴን ልቀጥል ስል…
‹‹ቆይ! ይኼን ደሞ ተመልከት!›› አለና ከሥር ሌላ ፎቶ ጠቆመኝ …ይኼንኛው ሁለት እጅም፣ ሁለት እግርም የለውም …ኒኮላስ ጀምስ የሚባል አውስትራሊያዊ ነው ….አጎቴ አንዴ እኔን በትዝብት፣ አንዴ ደግሞ በአድናቆት ጋዜጣውን እያዬ …‹‹ ሥራ ከመያዝ አልፎ ሁለት ወርቅ የመሳሰሉ ልጆች ወልዷል …አዬህ? …እያት ሚስቱ ማማሯ … አንተ ሥራው እንኳን ቢቀር፣ ሙሉ አካል ይዘህ ደህና ሴት ጓደኛ አታደርግም! ዝም ብለህ ከዚች ከቦጋለች ልጅ ጋር ትጓተታለህ! …ይኼን የማሳይህ ሮጥ ሮጥ ብለህ ሥራ እንድትፈልግ ለማነቃቃት ነው ….ለሌላ አይደለም …››

ምርር አለኝ …‹‹ አጎቴ! …ለምንድነው አንዴ እግር አንዴ እጅ የሌላቸው ሰዎች እያመጣህ የምትነዘንዘኝ? …እዚህች አገር ላይኮ ደህና ዘመድ ካለህ ፣ እንኳን እግርና እጅ ጭንቅላት ባይኖርህ ራሱ ጥሩ ሥራ ታገኛለህ! ›› ብዬ አጎቴን በቆመበት ትቼው ወደኋላዬ ተመለስኩ።
ከኋላ ድምፁ ይሰማኛል ‹‹እኔ እንድትነቃቃ ብዬ ነው አብርሃም …››

በ አሌክስ
@mahtot
77 viewsMokap, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 20:40:34 ቀውስጦስ የት ነው?

ከጥንት አዋልድ መጻህፍት ባንዱ ያነበብኩት ታሪክ ይህንን ይመስላል፤ ባንዱ መንደር በሚገኝ ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ይካሄዳል፤ ወላጆቻውን ተከትለው የመጡ ጥቂት ህጻናት ወድያ ወዲህ እየተራወጡ ቅዳሴውን መረበሽ ጀመሩ፤ እግዚር ከላይ ሆኖ ሲያይ ተቆጣ፤ ረባሽ ህጻናትን እንዲቀስፉ መላእክትን ላካቸው፤ መላእክት ወርደው የህጻናቱን አንገት በሰይፍ መቅላት ጀመሩ፤ በዚህ መሀል አንድ መላእክ ካንድ ህጻን ጋር ተገጣጠመ፤ መላእኩ፥ ህጻኑን የሚቀስፍበት አንጀት አልነበረውም፤ እና የእግዜርን ትእዛዝ ቸል ብሎ ህጻኑን ማረው፤ አሁን የእግዜር ቁጣ ከህጻናቱ ላይ ተነስቶ ትእዛዙን ባልፈጸመው መላእክ ላይ ሆነ፤ የመላእኩን ክንፍ አሽመደመደው! መላእኩ ለመብረር ሲሞክር ክፎቹ ከዱት፤ በቅጡ አስታውሸው ከሆነ ይህ መላእክ ሰሙ ቀውስጦስ ይባላል፤ ከተሳሳትሁ ዲያቆን ሄኖክ ያርመኛል፥

በጥንታዊ ተረካዎች ውስጥ ከማገኛቸው አንጸባራቂ የሞራል ጀግኖቼ መሀል ግንባር ቀደሙ ነው ፤
የዚህ ትረካ ደራሲ ሊነግረን የፈለገው ምንድነው ? አንኩዋን ከአለቃ ከፈጣሪ ቢመጣ የክፉ ተግባር ተባባሪ አትሁን! እምቢ በል! ክፋትን እምቢ በልና የሚመጣውን ተቀበል!

በ1968 አም ማርች ወር ፥ የአሜሪካ ወታደሮች በአንድ ማይ ላይ በተባለች የቤትናም መንደር ውስጥ ገስግሰው ደረሱ፤ ብዙም ሳይቆዩ ሰላማዊውን መንደርተኛ አሰልፈው መረሸን ጀመሩ፤ ህጻን ፥ ሴት ፥ አሮጊት ፥ ውሻ አልቀራቸውም፤ በጭካኔ የተለከፈ ፍጡር በመግደል ብቻ አይረካም፤ እንኳን ላይን ሰለጆሮ የሚቀፉ ጭካኔዎችን ሁሉ ፈጸሙ’
ባካባቢው በሂሊኮፍተር ሆኖ ቅኝት ሲያደርግ የነበረ ሌላ አሜሪካ የጦር መሪ ሲያልፍ የባሩድ ጭስ ተመልክቶ ወረደ፤ መሬት ላይ የሚካሄደውን ሲመለከት አይኑን ማመን አቃተው፤ ወገኖቹ ግድያውን ባስቸኳይ እንዲያቆሙ ጠየቀ! በደም የሰከረው የገዳይ ወታደሮች አለቃ ይህንን ጥሪ መስማት አልፈቀደም፤ ቶምሰን ጭፍሮቹን አሰልፎ “ግድያውን አቁሙ ! አለበለዝያ ወታደሮቼ በአናንተ ላይ እንዲተኩስ አዛቸዋለሁ ፤ ‘ሲል ለፈፈ ፤ በሁለት የአሜሪካ የጦር ክፍሎች መካከል ውጥረት ሰፈነ፤ ከብዙ ፍጥጫ በሁዋላ አምስት መቶ ሰላማዊ ሰዎችን የፈጀው ጭፍጨፋ ተገታ፤
የሚገርመው እነዚያ በጭፍጨፋው ላይ ከተሳተፉት ወታደሮች አንዳንዶቹ ሁኔታው ካለፈ በሁዋላ ጸጸት ረፍት ነሳቸው ፤ ጥቂቶቹ ራሳቸውን እየገደሉ ተገላገሉ፤ ገዳይም ብትሆን ከሰውነት መስፈርቶች ጥቂቶችን የምታሟላ ከሆንህ የሚወቅስ ህሊና ይኖርሀል ፤

ባገራችን ጭካኔ የባህላችን አንዱ ዘርፍ ቢሆንም ባለፉት አራት አመታት የተደረገውና የሚደረገው ስም አይገኝለትም፤ ስነምግባር የነጠፈበት አገር መሆኑ ታይቷል፤ በቡድን መግደል፥ በቡድን መድፈር የተለመደ ነው ፤ ግን ከገዳዮች መካከል አንዱ እንኳን “ ወገኖቼም ብትሆኑ እንድትገደሉ አልፈቅድላችሁም፤ ወገኖቼ ባይሆኑም እንዲሞቱ አልፈልግም “ የሚል ድምጽ ያለው ሰው መጥፋቱ አያሳዝንም? እንደ ቀውስጦስ “ከአምላክ እንኳ ቢመጣ ክፉ ትእዛዝ ክፉ ነውና አልፈጽምም “ የሚል አለመኖሩ አይገረምም? ጠመንጃ የታጠቀ ግዙፍ ሰውየ በህጻን ልጅ ላይ ሲተኩስ ሌላው ከቦ የሚጨፍርበት ክፋት ላይ የደረስነው በምን በኩል ተጉዘን ነው?

#bewketu ነው የጻፈው
@mahtot
86 viewsMokap, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 16:42:10
. dots
@mahtot
107 viewsMokap, 13:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 16:23:31 Remembering that I’ll be dead soon is the most important tool I’ve ever encountered to help me make the big choices in life. Because almost everything — all external expectations, all pride, all fear of embarrassment or failure — these things just fall away in the face of death, leaving only what is truly important. Remembering that you are going to die is the best way I know to avoid the trap of thinking you have something to lose. You are already naked. There is no reason not to follow your heart.

About a year ago I was diagnosed with cancer. I had a scan at 7:30 in the morning, and it clearly showed a tumor on my pancreas. I didn’t even know what a pancreas was. The doctors told me this was almost certainly a type of cancer that is incurable, and that I should expect to live no longer than three to six months. My doctor advised me to go home and get my affairs in order, which is doctor’s code for prepare to die. It means to try to tell your kids everything you thought you’d have the next 10 years to tell them in just a few months. It means to make sure everything is buttoned up so that it will be as easy as possible for your family. It means to say your goodbyes.

I lived with that diagnosis all day. Later that evening I had a biopsy, where they stuck an endoscope down my throat, through my stomach and into my intestines, put a needle into my pancreas and got a few cells from the tumor. I was sedated, but my wife, who was there, told me that when they viewed the cells under a microscope the doctors started crying because it turned out to be a very rare form of pancreatic cancer that is curable with surgery. I had the surgery and I’m fine now.

This was the closest I’ve been to facing death, and I hope it’s the closest I get for a few more decades. Having lived through it, I can now say this to you with a bit more certainty than when death was a useful but purely intellectual concept:

No one wants to die. Even people who want to go to heaven don’t want to die to get there. And yet death is the destination we all share. No one has ever escaped it. And that is as it should be, because Death is very likely the single best invention of Life. It is Life’s change agent. It clears out the old to make way for the new. Right now the new is you, but someday not too long from now, you will gradually become the old and be cleared away. Sorry to be so dramatic, but it is quite true.

Your time is limited, so don’t waste it living someone else’s life. Don’t be trapped by dogma — which is living with the results of other people’s thinking. Don’t let the noise of others’ opinions drown out your own inner voice. And most important, have the courage to follow your heart and intuition. They somehow already know what you truly want to become. Everything else is secondary.

When I was young, there was an amazing publication called The Whole Earth Catalog, which was one of the bibles of my generation. It was created by a fellow named Stewart Brand not far from here in Menlo Park, and he brought it to life with his poetic touch. This was in the late 1960s, before personal computers and desktop publishing, so it was all made with typewriters, scissors and Polaroid cameras. It was sort of like Google in paperback form, 35 years before Google came along: It was idealistic, and overflowing with neat tools and great notions.

Stewart and his team put out several issues of The Whole Earth Catalog, and then when it had run its course, they put out a final issue. It was the mid-1970s, and I was your age. On the back cover of their final issue was a photograph of an early morning country road, the kind you might find yourself hitchhiking on if you were so adventurous. Beneath it were the words: “Stay Hungry. Stay Foolish.” It was their farewell message as they signed off. Stay Hungry. Stay Foolish. And I have always wished that for myself. And now, as you graduate to begin anew, I wish that for you.

Stay Hungry. Stay Foolish.

Thank you all very much.
Steve jobs

@mahtot
95 viewsMokap, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 16:23:31 Again, you can’t connect the dots looking forward; you can only connect them looking backward. So you have to trust that the dots will somehow connect in your future. You have to trust in something — your gut, destiny, life, karma, whatever. This approach has never let me down, and it has made all the difference in my life.

My second story is about love and loss.

I was lucky — I found what I loved to do early in life. Woz and I started Apple in my parents’ garage when I was 20. We worked hard, and in 10 years Apple had grown from just the two of us in a garage into a $2 billion company with over 4,000 employees. We had just released our finest creation — the Macintosh — a year earlier, and I had just turned 30. And then I got fired. How can you get fired from a company you started? Well, as Apple grew we hired someone who I thought was very talented to run the company with me, and for the first year or so things went well. But then our visions of the future began to diverge and eventually we had a falling out. When we did, our Board of Directors sided with him. So at 30 I was out. And very publicly out. What had been the focus of my entire adult life was gone, and it was devastating.

I really didn’t know what to do for a few months. I felt that I had let the previous generation of entrepreneurs down — that I had dropped the baton as it was being passed to me. I met with David Packard and Bob Noyce and tried to apologize for screwing up so badly. I was a very public failure, and I even thought about running away from the valley. But something slowly began to dawn on me — I still loved what I did. The turn of events at Apple had not changed that one bit. I had been rejected, but I was still in love. And so I decided to start over.

I didn’t see it then, but it turned out that getting fired from Apple was the best thing that could have ever happened to me. The heaviness of being successful was replaced by the lightness of being a beginner again, less sure about everything. It freed me to enter one of the most creative periods of my life.

During the next five years, I started a company named NeXT, another company named Pixar, and fell in love with an amazing woman who would become my wife. Pixar went on to create the world’s first computer animated feature film, Toy Story, and is now the most successful animation studio in the world. In a remarkable turn of events, Apple bought NeXT, I returned to Apple, and the technology we developed at NeXT is at the heart of Apple’s current renaissance. And Laurene and I have a wonderful family together.

I’m pretty sure none of this would have happened if I hadn’t been fired from Apple. It was awful tasting medicine, but I guess the patient needed it. Sometimes life hits you in the head with a brick. Don’t lose faith. I’m convinced that the only thing that kept me going was that I loved what I did. You’ve got to find what you love. And that is as true for your work as it is for your lovers. Your work is going to fill a large part of your life, and the only way to be truly satisfied is to do what you believe is great work. And the only way to do great work is to love what you do. If you haven’t found it yet, keep looking. Don’t settle. As with all matters of the heart, you’ll know when you find it. And, like any great relationship, it just gets better and better as the years roll on. So keep looking until you find it. Don’t settle.

My third story is about death.

When I was 17, I read a quote that went something like: “If you live each day as if it was your last, someday you’ll most certainly be right.” It made an impression on me, and since then, for the past 33 years, I have looked in the mirror every morning and asked myself: “If today were the last day of my life, would I want to do what I am about to do today?” And whenever the answer has been “No” for too many days in a row, I know I need to change something.
65 viewsMokap, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 16:23:31 I am honored to be with you today at your commencement from one of the finest universities in the world. I never graduated from college. Truth be told, this is the closest I’ve ever gotten to a college graduation. Today I want to tell you three stories from my life. That’s it. No big deal. Just three stories.

The first story is about connecting the dots.
I dropped out of Reed College after the first 6 months, but then stayed around as a drop-in for another 18 months or so before I really quit. So why did I drop out?
It started before I was born. My biological mother was a young, unwed college graduate student, and she decided to put me up for adoption. She felt very strongly that I should be adopted by college graduates, so everything was all set for me to be adopted at birth by a lawyer and his wife. Except that when I popped out they decided at the last minute that they really wanted a girl. So my parents, who were on a waiting list, got a call in the middle of the night asking: “We have an unexpected baby boy; do you want him?” They said: “Of course.” My biological mother later found out that my mother had never graduated from college and that my father had never graduated from high school. She refused to sign the final adoption papers. She only relented a few months later when my parents promised that I would someday go to college.

And 17 years later I did go to college. But I naively chose a college that was almost as expensive as Stanford, and all of my working-class parents’ savings were being spent on my college tuition. After six months, I couldn’t see the value in it. I had no idea what I wanted to do with my life and no idea how college was going to help me figure it out. And here I was spending all of the money my parents had saved their entire life. So I decided to drop out and trust that it would all work out OK. It was pretty scary at the time, but looking back it was one of the best decisions I ever made. The minute I dropped out I could stop taking the required classes that didn’t interest me, and begin dropping in on the ones that looked interesting.

It wasn’t all romantic. I didn’t have a dorm room, so I slept on the floor in friends’ rooms, I returned Coke bottles for the 5¢ deposits to buy food with, and I would walk the 7 miles across town every Sunday night to get one good meal a week at the Hare Krishna temple. I loved it. And much of what I stumbled into by following my curiosity and intuition turned out to be priceless later on. Let me give you one example:

Reed College at that time offered perhaps the best calligraphy instruction in the country. Throughout the campus every poster, every label on every drawer, was beautifully hand calligraphed. Because I had dropped out and didn’t have to take the normal classes, I decided to take a calligraphy class to learn how to do this. I learned about serif and sans serif typefaces, about varying the amount of space between different letter combinations, about what makes great typography great. It was beautiful, historical, artistically subtle in a way that science can’t capture, and I found it fascinating.

None of this had even a hope of any practical application in my life. But 10 years later, when we were designing the first Macintosh computer, it all came back to me. And we designed it all into the Mac. It was the first computer with beautiful typography. If I had never dropped in on that single course in college, the Mac would have never had multiple typefaces or proportionally spaced fonts. And since Windows just copied the Mac, it’s likely that no personal computer would have them. If I had never dropped out, I would have never dropped in on this calligraphy class, and personal computers might not have the wonderful typography that they do. Of course it was impossible to connect the dots looking forward when I was in college. But it was very, very clear looking backward 10 years later.
70 viewsMokap, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 16:12:57 ጠላታችን ሥም ነው!

ሥም ከወላጅ የሚሰጠን ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ መጥቷል። የምናከብረው፣ ዋጋ የምንሰጠው፣ የምናስቀድመው የግለሰብ ማንነት ቀርቶ ሥምን ሆኗል። ሐብታም ለሚባልቢጤውን እናሸረግዳለን፤ የኔ ቢጤውን እናንቋሽሻለን። ለዶክተሩ ክብር ይኖረናል፤ ተራውን ዜጋ እንንቃለን። አንዱን ሰው ከሌላው፣ አንዱን ብሄር ተወላጅ ከሌላው፣ አንዱን ሐይማኖት ተከታይ ከሌላው የምንወደው፣ የምንጠላው…የምናከብረው፣ የምንንቀው…የምንቀርበው፣ የምንርቀው ማንነትን መሰረት አድርገን ሳይሆን ሥምን ተከትለን ነው። ግን ያልተገለፀልን ከሥም ሰው የመሆን ማንነት እንደሚቀድም ነው። በእኩል አይን ለመመልከት ሥም አያስፈልጋችሁም፤ ማንነት በቂ መሠረት ነው።



ሥም የለኝም፣ ሥም የለኝም በቤቴ
አንዱ እምዬዋ ሲለኝ፣ አንዱ ሲለኝ አከላቴ
ጎኔ ሽታዬዋ ሲሉኝ
በፍቅራቸው ሲጠሩኝ…(ጂጂ)


ሥም ከሌለህ ሁሉም ሥሞችህ ይሆናሉ። ይሄ ደግሞ ሰውነት ይባላል። አየህ ጠቢቧ ቀድማ ተናግራ ነበር።

በ “Game of Thrones” ተከታታይ ፊልም ላይ ከብዙዎቹ ውስጥ አንድ የምወዳት ወሳኝ ጭብጥ አለች። Jaqen H’gar የሚባለው ገፀ-ባህሪ አንዲት የመሳፍንት ዘር ያለባትን እንስት ፊት የለሽ (face less) እንድትሆን ሲያሰለጥናት ይታያል። ይሄም ፊትን በቀላሉ እየቀያየሩ ሰዎችን ለመግደል እንዲያመች ነው። አዚች ጋር ፋንጣዚ (fantacy) ነገር አለበት። እናም ፊት የለሽ ለመሆን በቅድሚ ከበፊት ሥሞችህ ጋር መፋታት ይኖርብሃል። ማንም፣ ሥም የለሽ (No one) መሆን አለብህ።

በስልጠናው ሒደት የምትሰለጥነው ጉብል Arya Stark ከበፊት ሥሟ በቀላሉ መለያየት የሚሆንላት አልሆነም። ተልኮ ቢሰጣትም የበፊት ሥሟ ተፅኖ እያደረገባት ሳትፈፅም ቀርታ አሰልጣኟ አይነ-ስውር ያደርጋታል። በዚህም በብዙ ትፈተናለች። ትራባለች፣ ትታረዛለች…። መምህሯ በመጨረሻ ይመጣና “ልጅቷ ሥሟን ከነገረችኝ ምግብ፣ መጠለያ እሰጣታለሁ፤ ብሎም የአይን ብርሃኗን እመልስላታለሁ?” እያለ ይፈትናታል። ልጅቷም “ማንም (No one) ነኝ” እያለች ትፀናለች። እንዲያ ከሆነ ይልና ጤና የሚሰጠውን (ዓይንን የሚያበራውን) ውሃ መሳይ ፈሳሽ እንድትጠጣ ይሰጣታል። በእርግጥ ፈሳሹ ሞትም አምጪ መሆኑ መታወቅ አለበት። በዚህ ወቅት ማቅማማት (እንዳትሞት ፈርታ) ሲታይባት ወሳኝ ነጥቧን ያነሳል “ልጅቷ የእውነት ማንም ከሆነች ምንም የሚያስፈራት ነገር የለም” (If a girl is truly ‘no one’, she has nothing to fear.)

ብዙሃኑ ሰው በልቡ ፍርሃት እንዲነግስበት የሚያደርገው እንደካባ ደርቦ ደራርቦ የሚዞረው ሥሙ ነው። በአብዛኛው ሰው የሚፈራው ለማንነቱ ሳይሆን ለሥሙ ነው። የሚጠነቀቀውም ለሥሙ ነው። የሚታመነውም እንደዛው። እንዳልሰደብ፣ እንዳልበለጥ፣ እንዳልወድቅ፣ መጠቋቆሚያ እንዳልሆን። መሞት የምትፈሩትም ለሥማችሁ ነው። ወልጄ ከብጄ የምትሉትም ነገር አለ። የምትወልዱትም ለሥማችሁ ነው። ተሽቀዳድማችሁ ዶክተር፣ ኢንጂነር፣ ዳኛ መሆን የምትፈልጉትም ለሥማችሁ ነው። ከሰው በላይ እንዲጠራ፤ በለጥኩኝ ለማለት ነው። አያችሁ ማንም (No one) ከሆናቹ ግን ሁሉም ሥሞች መጠሪያዎቻችሁ ይሆናሉ። ያኔ ሥሞቻቹ ማንነታችሁ አይሆንም፤ ማንነታችሁ ሥሞቻችሁ ይሆናሉ እንጂ።

ከዚህ ሐሳብ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ባይኖራትም ኤሚኒዬም የሚላትን አንድ አባባል ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። “የምታጣው ምንም ነገር ከሌለ ፣ ምታገኘው ሁሉንም ነው” (When you have nothing to lose, you have everything to gain)። የኔ ሐበሻ ጠቢቡ “የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም” እንዳለው ማለት ነው።

#ዳዊት_ወንድማገኝ
@mahtot
90 viewsMokap, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 14:55:38 ለስልጣን ጥማት ቀበሌ ገብተው እዛው ከቀበሌ እልፍ ማለት ያቃታቸው ያሳዝኑኛል።
@mahtot
78 viewsMokap, 11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 10:24:10 እውነትን እወቁ እውነትም ነጻ ታወጣችኋለች ተብሏል። ደግሞም እውነትን እውቁ እውነትም ታሳብዳችኋለች።
@mahtot
79 viewsMokap, edited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ