Get Mystery Box with random crypto!

ልጩህበት ክፍል ......1 አዘጋጅ ;- HEMA . . . . ስራዬን በጀመርኩ በ ሀያኛ | , 🖤 girls pride

ልጩህበት

ክፍል ......1

አዘጋጅ ;- HEMA
.
.
.
.

ስራዬን በጀመርኩ በ ሀያኛው ቀን ላይ እንደተለመደው እራቴን በልቼ ቡናዬን ጠጥቼ ከምሽቱ 3:15 ላይ ወደ ስራ ወጣሁ እስከ ምሽቱ አምስት ሰአት ድረስ ሲዝናኑ ካመሹት መሀል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ቤታቸው ከፊሉን ከመጠጥ ቤት አልጋ ወደያዙበት ሌላ ሆቴል ከፊሉን ከመጠጥ ቤት ወደ ሌላ መጠጥ ቤት ሳገላብጥ ቆየሁ።

ከምሽቱ አምስት ሰአት ካስር አከባቢ አንድ
ቀን ቀን ሆቴል ሆኖ ማታ ማታ ቅልጥ ወዳለ ጭፈራ ቤት ወደ ሚቀየር ሆት-ጭፈራ ቤት ከውስጥ የሚወጣ እና ትራንስፖርት መጠቀም የሚፈልግ ሰው እስኪወጣ ለመጠባበቅ ጠጋ ብዬ እንደቁምኩ አይኔ አንዲት ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሚጣል ነገር የለላት በዛው ሰአት ሰማይ ላይ እንዳለችው ጨረቃ ደስ የሚል ውበት ያላት ልጅ መግቢያ በሩ በስተቀኝ ብርዱን ለመቋቋም ከጡቶቿ በታች እጆቿን አጠላልፋ በማጣመር ቆማለች።

ሁኔታዋ ሲታይ ግራ ግብት ያላት ትመስላለች እዛው ቆማ አንዴ ቁልቁል አንዴ ሽቅብ ትገላመጣለች ።

እድሜዋ በግምት በ 19 እና በ21 መካከል ቢሆን ነው ይቺን የመሰለች ልጅ በዚህ ሳአት ሊያውም ብቻዋን እንዴት? ትልቁ የውስጤ ጥያቄ ነበር ።

አከባቢው ለኔ አዲስ ባይሆንም ልጅቷ ግን ለአከባቢው እዲስ ሳትሆን አትቀርም ከዚህ በፊት አይቻት አላውቅም ከባጃጄ ወርጄ ምነው ብቸሽን ልበላት አልበላት እያልኩ ከፍርሀቴ ጋር ስነታረክ አንዱ ስልክ ሊያናግር ከውስጥ ወደ ውጪ ወጣና ወድያው ስልኩን አናግሮ እንደጨረሰ አብረን እንግባ ብሎ ልጅቷ ላይ ሙዝዝ አለባት ከዛ በፊት እንደማይተዋወቁ ከሁኔታዋ ተረዳሁ።

ድርቅ ሲልባት ብስጭት ብላ ውዝውዝ ቅንጥስ ብጥስ እያለች ቀጥታ ወደኔ ባጃጅ መጣች ከመድረሷ በፉት ባላየ ፍቴን ወደ ፊት ለፊት አዞርኩ።

ደርሳ `` ይቅርታ ወንድም ጊቢ
ትወስደኛለህ ኮንትራት ''
አለች ዩኒቨርስቲ ማለቷ ነው ልጅቷ
የዩኒቨርስቲ ተማሪ መሆንዋን ለማወቅ
ጊዜ አላጠፋሁም ዩኒቨርስቲ ደግሞ
ከከተማ ትንሽ ወጣ ይላል


200 ብር ትከፍያለሽ አልኳት
ግማሽ ፉቷ ላይ ዘንፈል ብሎ ጋደም ያለውን ፀጉሯን በቀኝ እጃ ሁለት ጣቶች ወደ ጀርባዋ ብትን አደረገችና

"200 ብር ለተማሪ አይበዛም ወንድሜ ቤተሰብ በወር የሚልክልኝ እኮ 300 ብር ነው !" አለችኝ

መጀመሪያ አሳዘነችኝ !
ቆይቼ ደግሞ ታድያ አርፈሽ ትምህርትሽን አታጠኝም በዚህ ሰአት እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ?!ልላት ፈለኩና እሷን እንዲህ ለማለት ምንም አይነት መብት እንደሌለኝ ቶሎ በማስታወሴ ምላሴን ሰበሰብኩ።

"እ ምናልክ " አለችኝ ።
በደንብ ተመለከትኳት። ውስጤ ተላወሰ ።

እሺ ግቢ እንሂድ አልኳት
"በስንት?" አለችኝ

ደስ ያለሽን ትከፍያለሽ ዘላ ገባች :: ትንሽ
በዝምታ እየተጓዝን ድንገት ዘወር
አልኩና ....ሂሳብ አስቀንሰሽ ዝምም
ብለሽ አያዋጣኝም !

"ኦኬ እእእእእ ግን ይቅርታ በናትህ ከሚከብዱኝ ነገሮች አንዱ ጫወታ ቀድሞ መጀመር ነው" አለች እየተቁነጠነጠች

ምን አይነት ጫወታ ? አልኳት

"ያው ወሬ ነዋ ሌላ ምን አለ?"
ኧረ ብዙ አይነት ጫወታ አለ ተጫውተሽ አታውቂም እንዴ?
"እንዴ ! ክክክክክ እሱማ ብዙ አይነት ጫወታ አለ እኔ ለማለት የፈለኩት ግን ወሬውን ነው"
ሳቋ ልክ እንደ ህፃን ልጅ ሳቅ ደስ የሚል ለዛ አለው ።

ምን አይነት ጫወታ ይቀልሻል? ወይም ትወጃለሽ?

"እቃቃና እኩኩሉ ልበልህ "
ተሳሳቅን ሳቋን ወደድኩት።
ወደ ዩንቨርስቲው እየተቃረብን ነው።

እሺ እኔ ጫወታ በመጀመር ላግዝሻ?

"ከዚህ በላይ እሄው ጀመርከው እኮ! አለችኝ

እኔ ግን ጥያቄ ነበረኝ
የዩንቨርስቲ ተማሪ ሆነሽ በዚህ ሰአት ብቻሽን እዛ ጭፈራ ቤት በር ላይ ለምን ቆምሽ ወይ ገብተሽ አልተዝናናሽ

በረጁሙ ተነፈሰች ቀጠል አርጋም •••

አንድ ነገር ልንገርህ እንኳን ለኮንትራት ለምንም የሚሆን አምስት ሳንቲም ኪሴ ውስጥ የለም የፈለከውን አርገኝ!

ሲጢጢጢጢጥ ባጃጇን ከመቅፅፈት ቀጥ አድርጌ ስዞር ሽምቅቅ ብላለች•••

ይቀጥላል .....

━━━━━━━━ ✦


ክፍል 2 ይቀጥላል ........





╔═══❖• •❖═══╗
HEMA
╚═══❖• •❖═══╝