Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahebreyoredanose — ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahebreyoredanose — ማኅበረ ዮርዳኖስ የማኅበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማኅበር
የሰርጥ አድራሻ: @mahebreyoredanose
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 283
የሰርጥ መግለጫ

✝️ማህበረ ዮርዳኖስ የማህበራትና የወጣቶች አንድነት መንፈሳዊ ማህበር
👉 የማህበሩ አላማ ጥንታዊት ሐዋርያዊት ይሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመልዕልተ አድባራት በቀራንዮ መድኋኒዓለምና ቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም በወይብላ ቅድስት ማርያም ቤተክርስያን ስር ወጣቶች መንፈሳዊ ማህበር በማቋቋም ባላቸው እውቀት ጉልበት እና የገንዘብ አቅም ልክ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር ነው

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-15 07:17:43
46 views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 07:17:29 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! አሜን ።

ሐምሌ ፰ (8) ቀን


"ሰላም ለኪሮስ ዘሰዓሞ ነደ ከናፍር። ወበዛባኑ ተጽዕነ እግዚአብሔር። ወከመ ትጻእ ነፍሱ ዘንበለ ጻዕር። ዳዊት ኀለየ እንዘ ይብል በመሰንቆ ሐመዝ መዝሙር። ለጻድቅ ብእሲ ሞቱ ክቡር"። ትርጉም፦ የጻድቅ ሰው ሞት ክቡሩ ብሎ ዳዊት በመሰንቆው እያመሰገነው ነፍሱ ያላጻር የወጣች (የተለየች) እግዚአብሔርን በጀርባው ላዘለው የሚነድ መለኮት በከንፈሩ ለሳመው ለሆነ ለአባ ኪሮስ ሰላምታ ይገባል።




በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በፎስ ቡክ(facebook)
https://www.facebook.com/mahebereyordanos/
በቴሌግራም(telegram)
https://t.me/mahebreyoredanose
በዪትዪብ(YouTube)






44 views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 07:16:35
30 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 07:16:34 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! አሜን ።

ሐምሌ ፰ (8) ቀን


"ሰላም ለአባ ብሶይ ከመ ወርቅ ጽሩይ፤ ለምግባረ ጽድቅ ቅኑይ፤ በቅድስና ርሱይ"። ትርጉም፦ በቅድስና ያጌጠ፤ ለጽድቅ ሥራ የተገባ እንደ ወርቅ የጠራ የኾነ ለአባ ብሶይ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።




በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በፎስ ቡክ(facebook)
https://www.facebook.com/mahebereyordanos/
በቴሌግራም(telegram)
https://t.me/mahebreyoredanose
በዪትዪብ(YouTube)






29 views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 07:14:05
28 views04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:29:28
45 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:29:18
"ሰላም ለሚሳኤል ሶበ አዕረፈ እምተጽዕሮ። እደ ኪሮስ ድኅረ ቀበሮ። ለእለ መነንዎ ቅድመ ወኢሐወጹ ማኅደሮ። ያቅልል ለክሙ ይቤሎሙ ለጌጋይክሙ ፆሮ። እስመ በግፍዕክሙ ቦእኩ ለክርስቶስ ሀገሮ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ 8።




በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግኘት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በፎስ ቡክ(facebook)
https://www.facebook.com/mahebereyordanos/
በቴሌግራም(telegram)
https://t.me/mahebreyoredanose
በዪትዪብ(YouTube)






41 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:29:18 እኔም አባ ባውማ በዚያ ቦታ ብቻዬን ቀረሁ ተመልሼም ወደ አባ አሞን በዓት ደረስሁ። ከዚያም የሦስት ቀን መንገድ ተጉዤ ወደ አባ ስምዖን በዓት ደረስሁ። ከዚያም ሦስት ቀን ተጉዤ ወደ ቦታዬ ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረስሁ። ለመነኰሳቱም ሁሉ ያየሁትንና የሰማሁትን ሁሉ የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ስለ አባ ሲኖዳም ዕረፍት ትንቢት እንደ ተናገረ ነገርኋቸው። መነኰሳቱም ሰምተው እጅግ አደነቁ የተመሰገነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ገድሉን ጽፌ ለሚያነበውና ለሚሰማው ሁሉ መጽናኛ ይሆን
ዘንድ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉና ወደ ገዳማትም ላክሁ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ኪሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


አባ ሚሳኤል፦ ይህም አባት አባ ኪሮስ የቀበረው የንጉሥ ልጅ ድኃ የነበረ ነው። ዜናውም እንዲህ ነው። አባ ኪሮስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሳት ገዳም ሔደ። ከዚያም ደርሶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተሳለማት በዚያም አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ሥዕል አየ። ከዐይኖቹም ዕንባ እያፈሰሰ "እመቤቴ ሆይ አስቢኝ" አላት ሥዕሊቱም "ኪሮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው ከዚህም አትለፍ የአባትህን ዐፅም ትጠብቅ ዘንድ ወደ ማደሪያህ ተመለስ እንጂ" አለችው። አባ ኪሮስም ይህን ሰምቶ ከሥዕሏ ፊት ሰባት መቶ ሰግደትን ሰገደ። በዕብራይስጥም ቋንቋ "እንግዳ ነህና በቃህ በምሕረት መዝገብም ተመዝግቦልሃል" የሚለውን ቃል ሰማ።

ከዚያም በአለፈ ጊዜ መነኰሳቱ መልኩ የተዋበ ሁለመናውም ያማረ እንደሆነ ተመለከቱ። እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ "ይህ መነኵሴ ከመንግሥት ከተማ ከግብጽ አገር የመጣ ነው ሰውነቱ በጾምና በጸሎት አልጠወለገምና"። እጅግም ነቀፉት አልተቀበሉትም።ነገር ግን ወደ ሌላ ወደሚንቁት ቦታ ሰደዱት።

በዚያም መስፈርስ በሚባል ሕማም ለብዙ ጊዜ የታመመና በምድር ላይ የተጣለ ድኃ ሰውን አገኘ። በራስጌውም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በግርጌው ቅዱስ ገብርኤልን በቀኙም ቅዱስ ሩፋኤልን በግራውም ቅዱስ ሰዳካኤልን አየ። እነርሱም በክንፋቸው ጋርደውት ነበር ከሰውም ያለርሱ ያያቸው አልነበረም። "በገዳዩች ፊት ሞትን የማይፈራ ጐበዝ እንዴት ነህ" ብለው ሰላምታ ሰጡት። አባ ኪሮስም አደነቀ "በልዕልና ነዋሪዎች ሆይ ከዚህ ለምን ተቀመጣችሁ" አላቸው "ይህንን ድኃ እንድንጠብቀው ከእግዚአብሔር ታዘናል" አሉት አባ ኪሮስም "እስከ መቼ ነው" አላቸው። "ከዚህ ድካም እስከሚአሳርፈው ድረስ ነው" አሉት።

ከዚህም በኋላ ወደ ታመመው ደኃ ተመልሶ "በዚህ ቦታ ከኖርህ ምን ያህል ዘመን ነው" አለው በሽተኛውም "ሠላሳ አምስት ዓመት ነው" አለው ሁለተኛም "ከታመምክ ስንት ዓመት ነው" አለው "ሃያ ዓመት ነው" ብሎ መለሰ። "አበ ምኔቱና የገዳሙ መነኰሳት ይጐበኙሃልን" ብሎ ጠየቀው በሽተኛውም "አባቴ ሆይ የለም አይጐበኙኝም ፊታቸውን ከአየሁ ዓሥራ አምስት ዓመት ይሆናል" ብሎ መለሰ።

አባ ኪሮስም "ና ንገረኝ አባትህ ማነው እናትህስ ማናት" አለው በሽተኛውም እንዲህ ብሎ መለሰ "አባቴ የኬልቄዶን ንጉሥ እናቴም የራሕራሕ ንጉሥ ልጅ ናት። አባቴ ኪሮስ ሆይ እውነት እልሃለሁ በአባቴ ቤት ያሉ ሰዎች ወርቁንና ብሩን ቀጭኑንም ልብስ በእግሮቻቸው ይረግጡአቸዋል"። አባ ኪሮስም "ወደዚች ገዳም ማን አደረሰህ" አለው ድውዩም "እንዳንተ ያሉ ሁለት ሰዎች ወደ አባቴ ቤት መጥተው በዚያ አደሩ። እኩለ ሌሊትም ሲሆን ፊቱ ብሩህ የሆነ ሰውም ወደኔ መጣ "ሚሳኤል ብሎ ጠርቶ ሲነጋ ተነሥተህ ከእነዚህ ቅዱሳን ጋራ ሒድ" አለኝ በእንዲህ ያለ ሥራ ወጥቼ ወደዚህ ቦታ ደረስሁ ምንም በጎ ሥራ ሳልሠራም እንደ እነርሱ ሆንሁ"።

አባ ኪሮስም "እኔ አጽናናሃለሁና ወንድሜ ሆይ ስማ ስሙ በብኑዳ የሚባል አንድ እጅግ ድኃ የሆነ በበረሃ የሚኖር መነኵሴ ነበረ። የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ወደርሱ መጥቶ አሳተው እግዚአብሔርም ሥጋውን ለአንበሳና ለሰማይ ወፎች ሰጠ እርሱም በወገን የከበረ ከሮም ንገሥ በታች የሚገዛ የኬፋዝ ንጉሥ ልጅ ነበረ"። ሁለተኛም እነግርሃለሁ "የሮሜ ንጉሥ ልጅ የሆነ አንድ ድኃ ነበረ። እርሱም ከበትር ብቻ በቀር ከአባቱ ቤት ምንም ሳይዝ በቀስታ ወጣ ያንንም ሰው እኔ እጅግ አውቀዋለሁ። ከገዳም ወደ ገዳም ከተራራም ወደ ተራራ ይዞር ነበር ሞቱንም አላስተዋልኩም ሕይወቱንም አላወቅሁም"።

ዳግመኛም "አንድ የንጉሥ ልጅ ድኃ ነበረ። እርሱም በሰንበታት እነጂ በሌላ ቀን ምንም ሳይቀምስ ማቅ ለብሶ በቀንና በሌሊት ለጸሎት ይተጋ ነበር። በእንዲህ ያለ ሥራም ኑሮ አረፈ የብርሃን መላእክትም ነፍሱን ወስደው በመንግሥተ ሰማያት አኖሯት። አሁንም ወንድሜ የምነግርህን ስማ። የፈጣሪህ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አታድንቅ የወደደውን ይገሥጻልና" ያም በሽተኛ ድኃ መነኰስ "እውነት ነው ለእኔ ይገባኛል ስለ ኃጢአቴም ይህን ተቀበልሁ" ብሎ መለሰ። ይህንንም ብሎ ዝም አለ።

በዚያች ሰዓትም ያን በሽተኛ በሞት ያሰናብተው ዘንድ አባ ኪሮስ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በድንገት መጣ። እልፍ አእላፋት መላእክትም በዙሪያው ሆነው ከእርሱ ጋር ነበሩ ለጻድቃን ሞገሳቸውና ንጉሣቸው የሆነ አምላካችንን እናመስግነው ለችግረኞችም ተስፋ የሆነ አምላካችንን እናመስግነው እያሉ ይዘምሩ ነበር። በዚህ ዓለም በገድል የደከሙ በእርሱ ደስ ይላቸዋል።

አባ ኪሮስም በአየ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ "ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ወደዚህ ምን አመጣህ" አለ ጌታችንም "ስለ ጠራኸኝ መጣሁ" አለው። አባ ኪሮስም "ይህ ሰው ፃዕር በዝቶበታልና ያርፍ ዘንድ አሰናብተው" አለው። ጌታችንም "ምን ያህል እንደምወድህ የመላእክት ሠራዊት ያዩና ያውቁ ዘንድ ይቺን የገነት ተክል አበባ ከእጄ ወስደህ በዚህ በሽተኛ በፊቱ ላይ ጣል" አለው። አባ ኪሮስም ያንን የገነት ተክል አበባ ከጌታችን እጅ ተቀብሎ በበሽተኛው ፊት ላይ አኖረ ያን ጊዜም ነፍሱ ያለ ፃዕር በፍጥነት ወጣች መድኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ከእርሱም ጋር በብርሃን ሠረገላ ውስጥ አስቀመጣት አውጥቶም በሰማያዊ ክብር አኖራት።

አባ ኪሮስም እያደነቀ አለቀሰ ከዚህም በኋላ ወደ አበምኔቱ ሔዶ "እነሆ ያ ድኃ ስለ አረፈ መቃብር ቆፍረው ይቀበሩት ዘንድ ከመነኰሳቱ እዘዝ" አለው አበ ምኔቱም "ምን ግዴታ አለብኝ" አለው አባ ኪሮስም ትኩር ብሎ ተመለከተውና "ይህ የሰይጣን ሥራ እንጂ የሰው ሥራ አይደለም" አለው። ሰለ አስጨነቀውም ሰባት መነኰሳትን አዘዘለት እነርሱም ማዕጠንታቸውን ይዘው ተነሡ አባ ኪሮስም "የሚአጥኑት አሉና የረከሱ ማዕጠንቶቻችሁን አስወግዱ። በቦታቸውም ተዉአቸው ነገር ግን ቅበሩት" ብሎ አማላቸው።

ያን ጊዜም አራቱ የመላእክት አለቆች ሥጋውን በከርቤና በሚዓ አጠኑ መዓዛውም ያንን በዓት "መላው እነዚህ መነኰሳትም የሚያሸተን ምንድነው ይህመነኰስ ሥራይን ያውቅ ይሆን" ተባባሉ። ከዚህም በኋላ ሥጋውን ወስደው በዚያው ገዳም በእንግዳ መቃብር ቀበሩት ከመቃብሩም ጥሩ ውኃ ፈልቆ ለበሽተኞች ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ ሚሳኤል በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 8 ስንክሳር።
32 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:29:18 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! አሜን ።

ሐምሌ ፰ (8) ቀን


እንኳን ጌታችን በአረጀ መነኲሴ አምሳል ለተገለጸላቸ በጀርባቸው ላዘሉት የሚነድ መለኮት በከንፈራቸው ለሳሙ ለአባታችን ለአቡነ ኪሮስ ለዓመታዊ ለዕረፍታቸው በዓላቸው፣ አባ ኪሮስ ለቀበረው ለንጉሥ ልጅ ድኃ ለነበረው ለአባ ሚሳኤል ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልእግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።


አቡነ ኪሮስ፦ ይህም ቅዱስ የታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ወንድሙ ነበር በከተማ ውስጥ የሚሠራውን ዐመፅ በአየ ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ትቶ ከሀገሩ ወጣ። ጌታቸንም መርቶ ወደዚች ምዕራባዊት በረሀ አደረሰው በውስጧም ብዙ ዘመናት ብቻውን ኖረ ከሰው ማንም አላየውም በዚህ ሁሉ ዘመን የዱር አራዊትም ቢሆኑ።

በአስቄጥስም ገዳም ስሙ አባ ባውማ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ እርሱም የንጉሥ ዘይኑን ልጅ ቅድስት ኢላርያን ሥጋዋን የገነዘ ነው። እርሱም እንዲህ አለ በቤተ ክርስቲያን ወስጥ እያለሁ "አባ ባውማ ሆይ ተነሥ ወደ በረሀው ውስጥ ገብተህ ወደ ፀሐይ መግቢያ ሒድ ከቅዱሳን ሁሉ አብዝቶ ፈቃዴን የፈጸመውን የአንድ ገዳማዊ ሥጋ ትገንዝ ዘንድ የሚለኝን ቃል ከሰማይ ሰማሁ"። ያን ጊዜም ደስ ብሎኝ ተነሣሁ በበረሀውም ውስጥ ሦስት ቀን ተጉዤ ከአንድ ገዳማዊ በዓት ደርሼ ደጁን አንኳኳሁ አንድ ሽማግሌ ገዳማዊም ከፈተልኝና እርስ በርሳችን ሰላምታ ተለዋወጥን "በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን?" ብዬ ጠየቅሁት "አዎን" አለኝ። ሁለተኛም "ስምህ ማነው አባቴ ሆይ በዚችስ በረሀ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ኖርክ አልሁት" "ስሜ ስምዖን ነው በዚች በረሀ የኖርኩትም ሰባ ዓመታት ነው" አለኝ።

ከእርሱ ዘንድም ወጥቼ ሦስት ቀን ተጓዝኩ ሁለተኛም ስሙ ባሞን የሚባል ገዳማዊ አገኘሁ ሰላምታም ሰጠሁትና "በዚች በረሀ ሌላ ገዳማዊ አለን?" አልሁት "አዎን አለ" አለኝ። አራት ቀንም ተጓዝኩ ወደ አባ ኪሮስ በዓት ደረስኩ "ቅዱስ አባት ሆይ ባርከኝ" እያልኩ ደጁን አንኳኳሁ "አባ ባውማ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው" ብሎ ከውስጥ ተናገረኝ። "እግዚአብሔር ያከበረህ ሰው በሰላም በፍቅር ወደእኔ ግባ" አለኝ ያን ጊዜ ገብቼ ከእርሱ ተባረክሁ በፊቱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ክብር አየሁ የራሱ ጠጉርና ጽሕሙ እንደ በረድ የነጣ ነበር።

ከዚህም በኋላ ተቀመጥሁ በብብቻውም አቀፈኝ እንዲህም አለኝ "እነሆ ይችን ሰዓት እየጠበቅኋት በዚች በዓት ሃምሳ ሰባት ዓመት ኖርኩ" ይህንንም ሲል ጥቂት ታመመና ተኛ እየደነገጠ ያቺን ሌሊት አደረ ሲነጋም በበዓቱ ውስጥ ታላቅ ብርሃን በራ ብርሃናዊ ሰውም ገባ በእጁም የብርሃን መስቀል አለ በአባ ኪሮስ አጠገብም ተቀምጦ ሳመዉ ባረከውም አጽናናው ሰላምን ፍቅርን አንድነትን አደረገለት ከእርሱም ተሠወረ እኔም ፈራሁ "እንዲህ የሚበራ ይህን ክብር የተጐናጸፈ ይህ ማነው" አልሁት።

እርሱም "ልጄ ሆይ ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ልማዱ ስለ ሆነ ሁልጊዜ ይመጣል ያጽናናኛልም" አለኝ። "በቀዳሚት ሰንበት ዕለትም ዘጠኝ ሰዓት በሆነ ጊዜ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላቅ ጩኸትን ሰማሁ ከጩኸታቸውም ኃይል የተነሣ ምድር ተናወጸች። እኔም "ይህ የምሰማው ጩኸት ምንድነው ብዬ ጠየቅሁት እርሱም ልጄ ሆይ ይህ በሲኦል የሚኖሩ የኃጥአን ጩኸት ነው ስለ ቅድስት ትንሣኤው የእሑድ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ እግዚአብሔር ያሳርፋቸዋልና ስለዚህም እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል" አለኝ"። በዚችም ዕለት ሐምሌ ሰባት ቀን ቅዱስ አባ ኪሮስ ጩኾ አለቀሰ ዛሬ "በግብጽ አገር ታላቅ ምሰሶ ወደቀ ይኸውም የገዳማውያን አለቃ ቅዱስ አባ ሲኖዳ ነው" አለ።

ከዚህም በኋላ ከደዌው ጽናት የተነሣ እሑድ ሌሊት እጅግ ደነገጠ በበዓቱም ውስጥ እነሆ ታላቅ ብርሃን በራ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ገብቶ በአባ ኪሮስ ራስ አጠገብ ተቀመጠ። አባ ኪሮስም መድኃኒታችንን "ጌታዬ ሆይ ይህን ሰው ባርከው" አለው መድኃኒታችንም "የመረጥሁህ አባ ባውማ ሆይ ጽና አትፍራም ሰላሜ በረከቴም ከአንተ ጋራ ይኑር። አሁንም ታማኝ አገልጋዬ የሆነ የዚህን የቅዱስ ኪሮስን ያየኸውንና የሰማኸውን ወደፊትም ዳግመኛ የምታየውንና የምትሰማውን ገድሉን ጻፍ" አለኝ።

ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን አባ ኪሮስን እንዲህ አለው "እነሆ አንተ ትሞታለህና አትዘን ሞትህ ሞት አይደለም የዘላለም ሕይወት ነው እንጂ። የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን የሚሰማውንም ሁሉ በምድርም መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሽህ ዓመት በዓል ምሳ ከእኔ ጋር ይቀመጥ ዘንድ አደርገዋለሁ ከቅዱሳኖቼም ጋራ እቆጥረዋለሁ። የኃጢአቱንም መጽሐፍ ቀድጄ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ። ለመሥዋዕት የሚገባውንም ዕጣኑንና ወይኑን መብራቱንም መባ አድርጎ ለሚሰጥም በስምህም ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ለሚያደርግ ዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልቡናም ያልታሰበውን በጎ ዋጋ እኔ እጥፍ ድርብ አድርጌ እሰጠዋለሁ። በበኵር ቤተ ክርስቲያንም ሥጋዬንና ደሜን አቀብላቸዋለሁ በዚህም ዓለም ቤታቸውን እባርካለሁ። ልጆቻቸውን አሳድጋለሁ ከበጎ ነገር ሁሉ ምንም ምን አያጡም። አሁንም ከዚህ ዓለም ድካም ወደ ዕረፍት የዘላለም ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደ ብርሃን ቦታ እወስድህ ዘንድ ጊዜው ደረሰ" መድኃኒታችንም ይህን ሲናገር እነሆ ነቢዩና ዘማሪው ዳዊት መጣ መሰንቆውም ከእርሱ ጋራ ነበረች። "ይቺ ዕለት በእርሷ ፈጽሞ ሐሤት እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር የሠራት ናት" እያለ አመሰገነባት።

መድኃኒታችንም አባ ኪሮስን "እነሆ ዘማሪው ዳዊት መጥቷልና ይዘምርልህ ዘንድ የምትሻውን ንገር" አለው። ዳዊትም ቅዱስ አባ ኪሮስን "በየትኛው አውታር እንድዘምርልህ ትሻለህ ደግሞስ በየትኛው ዜማ በየትኛው ስልት በመጀመሪያው ነውን ወይስ በሁለተኛው ወይስ በሦስተኛው" አለው። ቅዱስ አባ "ኪሮስም በዐሥሩም አውታር በየስልታቸውና በየዜማቸው ልሰማ እሻለሁ" አለ። ያን ጊዜ ዳዊት መሰንቆውን አዘጋጅቶ "የጻድቅ ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው" አለ ዳግመኛም "ጐለመስሁ አረጀሁም የሚወድቅ ጻድቅን አላየሁም" አለ። ዳዊትም ድምፁን አሣምሮ ዘመረ መሰንቆውንም በስልት መታት። ያን ጊዜም የቅዱስ አባ ኪሮስ ነፍሱ ወጣች ኃኒታችንም ተቀብሎ ሳማት ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤልም ሰጣት።

እኔ አባ ባውማም የቅዱስ አባ ኪሮስን ሥጋውን ቀበርኩ ከበዓቱም በወጣሁ ጊዜ በረሀው በሰማይ ሠራዊት ተመልቶ አየሁ መድኃኒታችንም የቅዱስ አባ ኪሮስ ሥጋው ባለበት በዓት ላይ መስቀሉን አኑሮ ዘጋት። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለኔ ሰላምታ ሰጥቶኝ መላእክትና የመላእክት አለቆች በፊቱ እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ዐረገ። የቅዱስ አባ ኪሮስን ነፍስ ከመድኃኒታችን ጋራ እንደዚህ አሳረጓት። እርሷም በተሰጣት ክብር ደስ እያላት ዐረገች።
29 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:21:50
29 views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ