Get Mystery Box with random crypto!

✝ማህተቤ ክብሬ ነው✝

የቴሌግራም ቻናል አርማ maetebe_kbrenew — ✝ማህተቤ ክብሬ ነው✝
የቴሌግራም ቻናል አርማ maetebe_kbrenew — ✝ማህተቤ ክብሬ ነው✝
የሰርጥ አድራሻ: @maetebe_kbrenew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.21K
የሰርጥ መግለጫ

#ልጄ_ሆይ_እንዳትሆን_መናፍቅ ታሪክህንና ሃይማኖትህን እወቅ ። የዚህ ቻናል አላማ ትውልዱ ሐይማኖቱንና ታሪኩን ያውቅ ዘንድ እና ሙሉ ትውልድ ይሆን ዘንድ ማገዝ ነው ።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 06:28:14 #ሐምሌ7

#ቅድስትሥላሴ

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ

ምልዕተ ፀጋ ጥውም ዝማሬ






ለጥያቄዎመልስ አዲስ ስብከት




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
1.0K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 06:28:07
780 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 03:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:46:48
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ.  


እንኳን ለቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)፣ ለቅዱስ ዕዝራ ነቢይ፣ ለቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ፣ ለቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት እንዲኹም ለቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሣሌም ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ


"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!"

ዳግመኛም ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን ቅድስት ደብረ ቁስቋም፣ አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን፣ አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል፣ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ፣ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፣ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ፣ ቅድስት ሰሎሜ፣ አባ አርከ ሥሉስ፣ አባ ጽጌ ድንግል እንዲኹም ቅድስት አርሴማ ድንግል ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን አሜን!

"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33
          
  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ
መልካም ቀን  

ለመቀላቀል
1.1K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 10:59:45

861 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:07:57 የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
ታሪክ ባጭሩ

አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡

ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡

በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ፡፡

አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም

በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል።

በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡

አባታችን በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡

መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡

ለፅንሰትከ ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ።

ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ።

ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ።

የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከትታቸው አይለየን አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ

ምልዕተ ፀጋ ጥውም ዝማሬ






ለጥያቄዎመልስ አዲስ ስብከት







ስንክሳር ዘ ሐምሌ









ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
1.3K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 03:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:33:52

874 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 07:07:13
ምልዕተ ዕጋ ጥዑም ዝማሬ ሰብስክራይብ ሼር በማድረግ ናታኒም ቲዩብን ቤተሰብ ይሁኑ ውድ የተዋህዶ ልጆች።






1.0K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 07:02:10 ባለ ማህተብ ነኝ አዎ ባለ ማህተብ
ባንገቴ ያሰርኩኝ አዎ የእምነቴን ምስጢር
እንዲኖረው ትንሳኤ መቃብሬ
ለአረገ አምላክ ልመስክር ክር አስሬ
በቀጭን ሳይሆን አስሬ በወፍራሙ
እሰብካለሁ ማዳኑን ለአለሙ

በእውነት አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መላእክት ያሰማልን


ባለማዕተቦች ለባለ ማዕተቡ ሼር
ማዕተቤ ክብሬ ነው።

https://t.me/+TXNeLcC52mna201e
https://t.me/+TXNeLcC52mna201e
1.7K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 06:36:51 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ.  

እንኳን ለቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)፣ ለቅዱስ ክልስቲያኖስ ዘሮሜ ( ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት) እንዲኹም ለአባ ሉቅያስ ኤጲስ ቆጶስ ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ


"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!"

ዳግመኛም ዛሬ ሐምሌ 3 ቀን በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፣ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና፣ ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)፣ አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ እንዲኹም አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን አሜን!

"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯

  ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ
መልካም ቀን  

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ

ምልዕተ ፀጋ ጥውም ዝማሬ






ለጥያቄዎመልስ አዲስ ስብከት




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
1.5K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:18:48
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ.  


እንኳን ለቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኹ

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም!"

ዳግመኛም ዛሬ ሐምሌ 2 ቀን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት፣ ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ፣ ቅዱስ አቤል ጻድቅ፣ ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)፣ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ እንዲኹም አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ ወርኃዊ መታሰቢያቸው ነው

አምላከ ቅዱሳን በቃልኪዳናቸው ይማረን አሜን!

"የቅዱሳን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ምሳ. ፲፥፯


  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ ግሩፕ ይጋብዙ
መልካም ቀን  

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ

ምልዕተ ፀጋ ጥውም ዝማሬ






ለጥያቄዎመልስ አዲስ ስብከት




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
1.9K viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ