Get Mystery Box with random crypto!

#LWEQESH-Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ lweqesh_events — #LWEQESH-Ethiopia L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lweqesh_events — #LWEQESH-Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @lweqesh_events
ምድቦች: በጉዞ ላይ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.99K
የሰርጥ መግለጫ

ልወቅሽ የተለያዩ በሀገራችን ውስጥ ያሉ ነገርግን ያልታዩ እና ያልተዳሰሱ ታሪኮችን፣ ተፈጥሮአዊ መልክኣ ምድረዎችን እናማህበረሰቦችን አጠር በለ መልኩ የሚዳስስ ሲሆን በተጨማሪም ጉዞዎችን እንዲሁም ልዩ ዝግጅቶችን ያዘጋጃል ።"የለንን በማሳወቅ ሀገራዊ እሴትን እንገንባ !!!!!"ዕሮብ እና ቅዳሜ ፪ሰአት ይጠብቁን ለበለጠ መረጃ
@Bersihailu ፥ @fikirhailu ፥ @LWEQESH_Events

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-16 20:02:28
የኢሮ(አጱምጱም) በአል በበርታ
ይህ በአል የበርታ ማህበረሰብ በየአካባቢው ተሰብስቦ የክረምቱን ማለፍ የእህል መድረስ ጋር ተያይዞ የሚከበር ሲሆን ክብረ በአሉ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀመሮ ይከበራል።በአሉ እንደዘመን መለወጫም ይቆጠራል።
በዚህ መሰረት በአካባቢው መሪ ቤት አከባቢ ዳስ ተሰርቶ ምግብና መጠጥ ተዘጋጅቶ ህዝቡም ንፅሁ እና አዲስ ልብስ ለብሶ አምሮና ተውቦ ይሰበሰባሉ። ከዛም ከመሸ በኋላ የተለያዩ ባህላዊ መሳሪያዎችን በተለይም የዙምባራ መሳሪያን በመያዝ ሲጨፍሩ (አጱምጱም) ሲደሰቱ ያድራሉ።ወሩ ሊያልቅ አንድ ሳምንት እስኪቀረው በዚህ አይነት ሁኔታ ይቀጥላል።
የስርአቱ መጠናቀቂያ የሚሆነው በሶስተኛው ሳምንት መጨረሻ አርብ ጠዋት በመሪዎች የእሳት መወርወር የሚደረግ ሲሆን በክረምቱ የማይበሉ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች መፈቀዳቸውን ለማሳየት ነው።ከዛ ቀድሞ መብላትና አጱምጱም የተሰኘውን ጭፈራ ከበአሉ ውጪ መጨፈር በሽታ እንደሚያስከትልና የእግር ህመም እንደሚያመጣ ይታመናል።
@LWEQESH_Events
1.5K viewsሚክሎል, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:00:57 የኮሬ ብሔረሰብ ባህላዊ ዘመን መለወጫ

የኮሬ ብሔረሰብ ባህላዊ ዘመን መለወጫ በሆነው የ ''ህንግጫ ማሳላ'' የማክበረያ ቀን ዙሪያ በሰኔ 30/2014 የኮሬ ባህላዊ ንጉስ፥ቦኳዴዎች/ባህላዊ ቀበሌ/ ፥የሀይማኖት መሪዎች፥የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤት የሚሰሩ ሙሁራን እና በየደረጃ ያሉ አመራር አካላት ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ፥ የብሔረሰቡ የዘመን መለወጫ በዓል የሚከበርበት ቀን ከሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ጋር እየተገናኘ ስለመጣ በዓሉ የሚከበርበት ቀን ከጥር 27-30 እንዲሆን ተወስኗል።
@LWEQESH_Events
1.5K viewsሚክሎል, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:53:02
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልን በአሉ የሰላም፣የጤና፣የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንልን እንመኛለን።
ልወቅሽ ኢትዮጵያ https://t.me/LWEQESH_Events
1.4K viewsሚክሎል, 04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:23:34
ዘንገና ሐይቅ
በአዊ ዞን በባንጃ ወረዳ፣ በከሳ ቸውሳ ቀበሌ ከአዲስ አበባ በ430ኪ.ሜ ይገኛል የዘንገና ሐይቅ። ሐይቁ በአማካይ ከ150-169 ሜትር ጥልቀት ሲኖረው 0.54ኪ.ሜ² ስፋት ላይ ይገኛል።ይህ ውብ ተፈጥሮአዊ ሐይቅ በተለምዶ (crater lake) የሚባል ሲሆን በእሳተጎመራ መፈንዳት ምክንያት በሚፈጠር ጎድጓዳ ስፍራ ውሃ ሲያቆር የሚፈጠር።ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ በቦታው ያለ ውብ መልአምድር አቀማመጥ፣ተፈጥሮአዊ መንፈስ አዳሽ የሆኑ እፅዋቶች ህሊናን ይማርካል።
@LWEQESH_Events
1.4K viewsሚክሎል, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ