Get Mystery Box with random crypto!

ግን አንድ ነገር አለኝ ሃሳቤ ላንቺ አንጂ ለኔ መች ተቀመኝ ጠዋት አይል ማታ አንቺን እያሰብኩኝ | 💌💌💌💌MESSAGE 💌💌💌💌

ግን አንድ ነገር አለኝ

ሃሳቤ ላንቺ አንጂ ለኔ መች ተቀመኝ
ጠዋት አይል ማታ አንቺን እያሰብኩኝ
በናፍቆትሽ እሳት እረ ተይ አለኩኝ
       ግን አንድ ነገር አለኝ
አይኔ አንቺን ይላል ማረፊያዬን አምጣ
አይኖችሽን አይቶ ነገር ስላመጣ
ልቤም አንቺን ይላል ተነስቶ ሊወጣ
ደረቴን ፈንቅሎ ወዳንቺ ሊመጣ
       ግን አንድ ነገር አለኝ
       ተስፋ የሚሰጠኝ
አንገቴም አወራ እሱም አፍ አውቶ
ከነፈርሽ ሲስሙት ደስታው እላይ ወቶ
አምጣና አስገባት ይላል አፉን ሞልቶ
       ግን አንድ ነገር አለኝ
       መከታ የሆነኝ
የደረቴም ብሶ ሁኔታው ገረመኝ
የልቤን ትርታ መጥታ ታዳምጥልኝ
የለኛል ጧት ማታ እሷኑ ጥራልኝ
እጆቼም አያርፉ እጆችሽን ሲሉ
የጆችሽን ፍቅር በፍቅር ተቀበሉ
      ግን አንድ ነገር አለኝ
      እረፍቴ የሆነኝ
እግሬም ሂድ ይለኛል እሷ ካለችበት
ደከመኝ መቼ ያቃል ድካም ሆነሽበት 
     ግን አንድ ነገር አለኝ
      አለሜ የሆነኝ
ታዲያ ምን ተሻለኝ የኔ እስኪ ንገሪኝ
ስር አካላቴ በፍቅርሽ ተማርኮ ኮበለለ ጥሎኝ
    ታዲያ ግን አንድ ነገር አለኝ
    ሀሳብ ከሆነብሽ ልንገርሽ አድምጪኝ
    ፍቅር ተሸክሞ ተንገዳግዶ መቷል
    ለራሱ ሳያስብ ድካሙንም ችሏል
    ማነው እሱ ብለሽ ማወቅን ከናፈቅሽ
    የኔ ጀግና አሳቢ እረፍት ሆነኝ ልብሽ


yenaw

@yenagtm
@yenagtm
@yenagtm