Get Mystery Box with random crypto!

የሆነ ጊዜ ላይ ስለራሴ እያሰብኩ በማላውቀው መንገድ አንቺን ማሰብ ጀመርኩ ቀጠል አረኩና ለምን | Lover zone ❤❤

የሆነ ጊዜ ላይ ስለራሴ እያሰብኩ
በማላውቀው መንገድ አንቺን ማሰብ ጀመርኩ
ቀጠል አረኩና ለምን ያህል ጊዜ ሀሳቤ እንደሆንሽ ራሴኑ ጠየኩ
ብዙም አልተቸገርኩ መልሱም አልከበደኝ
ያየሁሽ ጊዜ ነው ሀሳቤ የከዳኝ
ስትስቂ ያየ ሰዓት ልቤ ላንቺ መታ
አመነሽ በጭፍን ለፍቅርሽ ተረታ
ያየሁሽ ሰዓት ነው የልቤ ጨለማ ብርሀን የተሞላው
የጨረቃም ውበት ከፀሀይ የባሰው
ያገኘሽ ሰዓት ነው አንቺን አምጣ ያለኝ ልቤ ስራ ፈቶ
አንቺ ሆንሽ ተግባሩ ደም መርጨት ረስቶ
ከዛሬ 2 አመት ከዛን ለት አንስቶ
ሀሳቤ የኔ አደለም ያንቺ ሆኗል ከቶ
አለኝ 1 መልዕክት የኔ ጣፋጭ ፍቅር
የማይቀር ነው እና ከራስ ጋር ንግግር
ካንቺው ስትዋዪ ካንቺው ስታወሪ
አደራ ይሄን መልዕክት ለልብሽ ንገሪ
አንቺ አለም ውስጥ ያለ ዘላለም ሚወደሽ
ካላንቺ የማይቆም ሁሌም የሚያፈቅርሽ
፩ ልብ እንዳለ መቼም እንዳይረሳ ንገሪው አጥብቀሽ
ደሞ የኔ ፍቅር ይሄን ስታነቢ
አፍቅሮኛል ብለሽ ፈፅሞ አታስቢ
ይህ ፍቅር አደለም ፍቅር እንዲ የለም
የፍቅር ጥግ ነው ዳር ወሰን የለውም
ይህ መውደድ አደለም መውደድ ያንስበታል
ለመግለፅ የሚሆን ቃላቶች ያጥሩታል
ከራስሽ ከልብሽ ዳግም ስታወጊ
ፍቅሬን የሚገልፀው ሌላ ቃል ፈልጊ
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አታቅልዪ
ከፍቅር በላይ ነው የሚያፈቅረኝ በዪ

SET BY @AMANDA_LAST_KING
@loverzonn