Get Mystery Box with random crypto!

#መልካምነት አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግ | 💌💌የእናት_ፍቅር💌💌

#መልካምነት

አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም፡፡ አንድ ቀን አባቱ "ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፡፡ "እንደዚያ ከሆነ የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡ ልጁም አባቱ ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ" ይለዋል ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፡፡ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው" ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ አረጋገጠ ።

#ፍርድ_ቤት_የተባለው_የሰው_ልጅ_ይችን_ዓለም_ተሰናብቶ_የሚኖርባት_የዘላለም_ቤቱ_ሲሆን

❶- #የመጀመሪያው_አልችልም_ያለው_ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ።

❷- #ሁለተኛው_ፍርድ_ቤቱ_አመጣለው እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና ልሙት አይልም።

❸- #ሶሰተኛው_እሰከ_መጨረሻው_አንተ_ጋር_ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም ሰራዎች ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ ጋር ይከተሉናል፡፡

ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና።

ፀሐፊ:ከ Fb መንደር
✦✦ ✦✦
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
Join us
@love_fikirr @ngusu_se

…...…,•’``’•,•’``’•,M
…...…’•,’ ’ ,•’
...……...’•, ,•’,•’’•,•’’•,a
,•’’•,•’`’•,....’•,’ ’ ,•’
’•,’ ’ ,•’…....’•, ,•’m
’•,