Get Mystery Box with random crypto!

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

የቴሌግራም ቻናል አርማ loret_tsegaye — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም
የቴሌግራም ቻናል አርማ loret_tsegaye — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም
የሰርጥ አድራሻ: @loret_tsegaye
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.30K
የሰርጥ መግለጫ

📓• ድርሰት ህይወት ነው ።
•|➮ የህይወት ትርጉም ያለው ማንበብ ውስጥ ነው።
•|➮ ማንበብ ውስጥ ራስን ማግኘት አለ
•|➮ ራስን ማግኘት ውስጥ ቤተሰብን ማግኘት አለ
•|➮ ቤተሰብ ውስጥ ሀገር
•|➮ ሀገር ውስጥ ፍቅርን
•|➮ ከሀገር ከቤተሰብ ከፍቅር ከፈጣሪ ከነዚህ በላይ ደሞ ምንም የለም !!
•══════════
📚•|For any promotion • Contact Admin @eyosiii

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-09-28 20:40:37 “ዋ” ብሎ

ሰው የሚማረው
አንድም በፊደል
አንድም በመከራ ነው፤
አንድ ቃል ከፊደል መዝገብ
አንድ ቃል ከመከራ መዝገብ
አንድም በሳር ‘ሀ’ ብሎ
አንድም በአሳር ‘ዋ’ ብሎ።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
15.9K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-27 20:34:27 የነገው_ነፋስ

ያንን ገለባ ልብ
ከደጅ የወደቀው፣
"አድራሻህ ወዴት ነው?"
ብለህ አትጠይቀው፣
የነገው ነፋስ ነው
መንገዱን የሚያውቀው ።

በዕውቀቱ ስዩም

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
14.8K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-07 21:27:46 አልወለድም

ላልኖር ና አትበይኝ ማማጥሽን ተይው
አቁሚ እናቴ ዓለምን አልየው
አምላክ ከሌለበት ዘመን ላይ አታምጪኝ
የምድርን ጭካኔ ፅዋ አታጠጪኝ ።

ዘር ተለግሶኝ ብሄሬን ከማየት
ዘጠኝ ወር ይለፈኝ ከሆድሽ ልሸብት
ፍቅር ሰላም የለ ከሆድሽ ብወጣ
ኖሬ ላልጨርሰው ምድር ላይ አልምጣ ።
ስሚኝ እህ ብለሽ እናቴ አድምጪኝ
ስወጣ ለማጣሽ አምጠሽ አታምጪኝ ።

ለምን ብዬ ልምጣ ዘሬን ከቆጠሩት
ወንድሜን ልገድል ጥይት ለሚያቀርቡት
ለምን ብዬ ልምጣ ምን አገኘው ብዬ
ግምት ከጠሰጠኝ እታችና ላዬ ።

ማማጥሽን ተይው እናትነትሽን አልክድም
ሰላም በሌለበት መኖር አልፈልግም
ወደ አለም አትግፊኝ እኔ አልወለድም

ከፊሊሞና

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
17.2K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-05 17:20:26 ያን ቀን

ያንን ቀን ረገምኩት ካንተ ያራቀኝን
እራሴን አስቶ ጤና የነሳኝን
ሀሙስ የቀን ቅዱስ ነበረ ያ ቀኑ
ለኔ ግን ረከሰ ሲቀማኝ አንተኑ
እማ የኔ ፍቅር እንዳላልከኝ ያኔ
ምን ሴጣን ለከፈህ ሊያርቅህ ከኔ
ምን በደልኩት ብዬ እራሴን ስወቅስ
ትራሴን አቅፌ ብቻዬን ሳለቅስ
ቀናቶች ተቆጥረው ሳምንታት አለፉ
እንዲያው ስጠብቅህ ልቤ አለመስነፉ
የውሳኔ ቀን ደርሶ ላወጣህ ከ ልቤ
አዲስ ነገር አየሁ ተረጋጋ ቀልቤ
አንተን እንዳይቀማኝ የለመንኩት ጌታ
ይኸው ተቀበለኝ ተሰማኝ እፎይታ
ይቅር ባይ አረገኝ ይቅር ባይ ነውና
አንተን ስለሰጠኝ በስሙ ልፅናና
ዳግመኛ እንዳቴድ እለምንሀለው
በፍቅር እናት ስም እማፀንሀለው
ሁሌም የኔ ሆነህ እኔም ያንተ ልሁን
እስከመጨረሻው ፈጣሪ አይለየን

Yodina
#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
15.4K views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-15 15:41:50 ቀጥረሽኝ....ፈላስፋ አደረግሽኝ


ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡

ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡

እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡

እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡

እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡

እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!

በላይ በቀለ ወያ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
17.2K views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-25 14:56:14 ለካ እሞታለው....


ለካ እሞታለሁ እሄዳለሁ እላይ
ፍርዴን ለመቀበል ከዳኛው ከበላይ
ለካ እሞታለሁ ፥ ድንኩዋን ተጥሎልኝ
በ ሜትር በ ልኬት ሳጥን ተገዝቶልኝ
ለካ እሞታለሁ! መሬት እገባለሁ
ወይ ሲኦል ገነትን ለካ አያታለሁ።
.....

ለካ እሞታለሁ ፥ ጥቁር ለብሠውልኝ
ሠው እያበሉ በ ዓመት ዘክረውኝ
ለካ እሞታለሁ ፥ጥያት ይችን ዓለም
እናት የለ አባት ፣ እህት የለ ወንድም፣
ሀገር የለ ወገን ፣ ልጅ የለ ሚስት
ያለ በዚህ ዓለም...
ሁሉን እተወዋለው ሄጄ ለዘላለም።
.....
ለካ...እሞታለሁ ያለኝን ነገር አይቼ
ወደ ሞት ስሄድ ባዶዬን ትቼ
ለካ እሞታለሁ!
የላይኛውን መንገድ ትኬት እቆርጣለሁ።
.....
መሞቴ ሆኖብኝ የማይፈታ ቅኔ
ፍቺው ጠፍቶብኝ አሁን ታዲያ እኔ
ሞትን እረሣሁት እያየሁት ባይኔ
.....
ምነው ታዲያ መሞቴን እረሳሁ
ሁሉን ትቼ እኔ ፥ እንደ አዳም ዘነጋሁ
ለካ ለካ ለካ... ለካ እሞታለሁ
ሁሉን ነገር ትቼ ካለም እርቃለሁ።


ፊሊሞና

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
18.0K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 19:11:06 ቀረሽ እንደ ዋዛ

እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ዛፍ ሐረጎች፣
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ።
ስጠብቅ ----- ስጠብቅ
“ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ፣
ሳይ ማዶ፣
የልጅነት ዓይኔ ሟሟ እንደ በረዶ።”
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር፣
ትመጫለሽ ብዬ ባዘን ሳንጎራጉር
ትመጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ስዞር
ብርድ አቆራመደኝ።
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ፣
ጨለማው ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ----- ያውቃሉ።
መስኮቶች ጨልመው፣
ቤቶች ተቆልፈው፣
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ----- ያያሉ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ---- ያውቃሉ።

ገብረ ክርስቶስ ደስታ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
18.1K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ