Get Mystery Box with random crypto!

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

የቴሌግራም ቻናል አርማ loret_tsegaye — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም
የቴሌግራም ቻናል አርማ loret_tsegaye — ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም
የሰርጥ አድራሻ: @loret_tsegaye
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.30K
የሰርጥ መግለጫ

📓• ድርሰት ህይወት ነው ።
•|➮ የህይወት ትርጉም ያለው ማንበብ ውስጥ ነው።
•|➮ ማንበብ ውስጥ ራስን ማግኘት አለ
•|➮ ራስን ማግኘት ውስጥ ቤተሰብን ማግኘት አለ
•|➮ ቤተሰብ ውስጥ ሀገር
•|➮ ሀገር ውስጥ ፍቅርን
•|➮ ከሀገር ከቤተሰብ ከፍቅር ከፈጣሪ ከነዚህ በላይ ደሞ ምንም የለም !!
•══════════
📚•|For any promotion • Contact Admin @eyosiii

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-21 21:26:41 ኪሳራ

አንዳንዱ
መድሐኒት ለመግዛት ፣ መርዝ ይቸረችራል
አንዳንዱ
መዳኒቱን ሽጦ ፣ ሲያቃስት ይኖራል::

በላይ በቀለ ወያ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
10.8K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 21:23:02 ሚስቴ ሁኝ

አፈቀርኩሽ ይላል በንባ እየራሰ
ሚስቴ ሁኝ ይለኛል ከግሬ እየደረሰ
እኔ ለራሴ፣
ከዓለም ተቃርኘ
በባንዳነት ተወስኘ
በሀዘኔ እየሳቀች
በዕንባዬ እያበበች
ላንችን ስታ ለኔ እያለች
እንድጃጅ ሳለጋ
ከመኖር ሳልጠጋ
እንድመሽ ሳይነጋልኝ
ትደክማለች እስኪወስደኝ
በዚች ንፉግ ምድር
በፍስክ እየፆምኩ
እንኳን ላንተ ልኖር
ለኔም ቁንጥር አልኖርኩ።

ገነት

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
11.0K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 19:55:22 የፍቅር ቃጠሎ

ጉንጭሽ ፅጌረዳ ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጠዋት ጨረር የበራ ማለዳ፡፡
የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ፡፡
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ ባከላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ ሆነሻል ህይወቴ፡፡
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለሁ
እስረኛ ሆኛለሁ፡፡
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ
ትኩሳት አምጥቶ፡፡
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ልቀዝቅዝ
ንከሺኝ ልደንዝዝ፡፡

ገብረክርስቶስ ደስታ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
15.4K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 21:37:54 ምናባዊቷ ሴት

ከጠቢብ ይገኛል ማስተዋልን ሲሹ
ጣዕሙን መለኪያ ከሀሳብ ቀማሹ
ምናባዊነትን የለት ቀለብ አርጋ
ሙግት የገጠመች ሀሳቧ ሳይረጋ
ተመስጦ የበዛው ውሎዋን ያስዋበ
ሀሳቧን ስትዘራው ምናቧ ያበበ
በተመልካች በኩል እብደት ቢመስለውም
የረቀቁት ምስጠት ውሉ ባይገባውም
እሷ ግድ የላትም ፈገግታ ነው መልሷ
እኔን የገረመኝ የደነቀኝ ነገር
ሀሳብ ይወለዳል ስለሷ ሲነገር
በዚ ከንቱ ዘመን ሀሳብ ከተጣላው ምናብን አፍቅሮ ሀሳብን አስምሮ
እንዴት ነው ሚኖረው
ያሳብ ልዕልና ጥቅሙ የገባት
እስጊገርመኝ ድረስ ዕፁብ ድንቅ ልጅ ናት

ዮቶር አብ

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
14.2K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-19 21:55:33
Core Computer

Join us if u need
Brand new laptops
Gaming laptops
Slightly used laptops

With 1 year warranty

Join our telegram channel
https://t.me/joinchat/byKVUnPiXhowN2U0

Call us on
0907 270775
0912 690379
Megenagna Zefmesh grand mall
12.1K views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-19 18:14:20 የአህያ ኑዛዜ

ዕፅዋት ይቀጠፍ
ዛፍ ከስሩ ይነቀል
የምድር ታሪኳ ከወዲሁ ይጠቅለል
ሀይቅና ወንዙ ከቶ ውሃ ይጣ
ኣእዋፍ አራዊት በርሃብ ይቀጣ
ደረቅ ሆኖ ይክረም የባህር ዳርቻ
እኔ ከሞትኩማ ለምን ሰርዶ ብቻ።

ዮኒ

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
11.6K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-15 20:25:46 ስንት ነው ሚገዙኝ

አይን መነፅር ሆኖ ማንነትን ማያ
ልብስ መስፈርት ሆኖ የሰው ልጅ መለኪያ
የፀጉር ስታይል ጨዋን ሰው መለያ ሆኗቸው መሳሪያ
ከሩቁ አይተውኝ ጨዋ ነው ዱርዬ ብለው ከፈረጁኝ
ስም ከለጠፋብኝ ውስጤን ሳይረዱኝ
እኔን እንደ እንስሳ በቁም ከገመቱኝ
እስኪ ጠይቋቸው ከተመቸኝ ልሸጥ
ስንት ነው ሚገዙኝ?

Teddy

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
13.1K views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 16:20:22 የሰማይ ቤት ግሮሰሪ

ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
።።።።
ከዋክብት ደግሞ ፣ አብረዋት 'ሚወጡ
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋር ሚጠጡ!!!
።።።
በጣም የሰከረው...
ራሱን ከሰማይ ፣ ፈጥፍጦ ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ፣ ማለት ነው የኛ እድል!!!

በላይ በቀለ ወያ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
14.8K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-02 09:05:32 ብቸኝነት!

ቀኑ ተሰናብቷል
ጨለማው በርትቷል
ጨረቃ የት ጠፋች?
ምን ሆኑ ኮከቦች?
ጅቦች አይፈነጩ
ውሾች አይንጫጩ፡፡
ጨለማው ፍጹም ነው
ነፋስ ጭራሽ አይነፍስ
ዛፍ አይወዛወዝ አንድ ወፍ አይላወስ
ሁሉም ፀጥ
በያለበት ለጥ፡፡
ሰው ሁሉ ምን ነካው?
ድምፁ እንዲህ የጠፋው?
እኔንስ ምን ነካኝ?
እንቅልፍ የማይወስደኝ?
እኔ ብቻዬን ነኝ በዚህ ደረቅ ውድቅት፤
ልቤ እየቃተተ ጠልቶ ብቸኝነት፡፡
ሰው አለወይ ባገር?
ማረፊያ ለፍቅር?
ፈላጊና፤ ተፈላጊ ሁሉ
ቀናው ወይ በሙሉ?
የቀረ የለም ወይ በዓለም አለኔ
በምኞት ኩነኔ?
እኔ እንደዚህ ስዋኝ ባሳብ በትካዜ
የት ይሆን ያለሽው አንቺ ይህን ግዜ
ምን ታደርጊ ይሆን?
እንገናኝ ይሆን?
መች ይሆን ዕለቱ?
መች ይሆን ሰዓቱ?
የትስ ይሆን ቦታው?
እንዴት ይሆን እውቂያው?
እጠብቅሻለሁ ልቤን እየታዘዝሁ፤
አትቅሪ፤ ፈልጊኝ፤ እፈልግሻለሁ፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
16.4K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-29 21:04:25 ድምጽ አልባ ፊደላት

ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት
ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ነገር
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጧት
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት
ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል
እናትነት ሲጎድል
ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ፊደል።

ኤፍሬም ስዩም

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye
17.0K views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ