Get Mystery Box with random crypto!

ለዉህደት_ እስኪያጨን ክልል ጎጥ ለክተዉ መትረዉ ከሰጡን ሌላ ስም ካወጡ ጠልሽቶ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

ለዉህደት_ እስኪያጨን

ክልል ጎጥ ለክተዉ
መትረዉ ከሰጡን
ሌላ ስም ካወጡ
ጠልሽቶ ስማችን
መደመር ኮስሶ
ዘረኝነት ነግሶ
ሞት ስለረከሰ
ኗሪዉ ስላነሰ
አንዱ አንዱን እንዳይገል
በቀዬ ባፈሩ
አንዱ አንዱን እንዳይል
ምንድነዉ ብሔሩ
በገዛ ቤታችን
እንዳንሆን ቤት አልባ
ጎተራችን ሞልቶ
እራብ እንዳይገባ
ፍቅርን እስኪሰጠን
ለዉህደት እስኪያጨን
እኛና ሌሎቹ
ግፍን እንዳንሰራ ግፍን እንዳይሰሩ
መትረዉ ሲያበቁ
በማይፈርስ ግድግዳ
በማይዘለል ካብ ድንበሩን ይጠሩ።

ገነት

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye