Get Mystery Box with random crypto!

'የገጣሚው እና ያናጢው ልዩነት ' እሱ (አናጢው) መሬት ተመርኩዞ መሰረት ይተክላል፣ ባለ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

"የገጣሚው እና ያናጢው ልዩነት "

እሱ (አናጢው)
መሬት ተመርኩዞ መሰረት ይተክላል፣
ባለቅኔ ዕርሱ ወይ ሴት ወይ ሀገር ነው ከዛ በምን ያልፋል።
እሱ (አናጢው)
ለሚገነባው ቤት ዲዛይን ያልማል፣
ገጣሚ ለስንኝ ቃላት ይቃርማል።
እሱ (አናጢው)
ለግድግዳው ጥርሰት መጠናከር ሚስጥር፣
ብሎኬት ምናምን ሲለቃቅም ምስማር፣
የእኔ ቢጤ ግና
ለስንኙ ማብቂያ ቤት መምቻ እያለ፣
ተመሳሳይ ፊደል ሲፈልግ ዋለለ።
(ምስኪን)
እሱ (አናጢ)
ለገነባው ማጀት ማስዋቢያ ማስጌጫ፣
ቀለምና ኮርኒስ ጊጣጌጡን ዋንጫ፣
ያመሰቃቅላል
ገጣሚው ለስንኝ ሀሳብ እያነሳ ሀሳብን ይጥላል።

ግና
በሁለቱ አለም ውስጥ መለያየት አለ ፣
አናጢው ለቤቱ አካሉን አንቅቶ ሲሽኮለኮል ዋለ።
በተግባር ዋለለ።
የኔ ባለቅኔ
ከቃላት ጦርነት ግጥሚያ እንደጀመረ፣
ስንት ሀሳብ አውርዶ :ስንቱን አባረረ፣
ከፈጣሪው ሳያንስ:ምስል እየፈጠረ።
በፈጠረው ፍጥረት ሲለው እያጋጨ፣
ሲያሰኘው በንዴት እየተነጫነጨ፣
ህመም ናፍቆት ፅፎ :ስንቱ ስንኝ ቋጨ።

አናጢው ቤት ሲያንፅ
ለራሱ ገንብቶ:ማረፊያ አዘጋጅቶ፣
ገጣሚው ግን ቤቱ፣
መኖሪያ አቀበቱ፣
በሰዎች ልብ ነው:ዝክርና እረፍቱ።

ፍሬው ተካልኝ

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye