Get Mystery Box with random crypto!

ለጤዛ ተዋድቀን! እድሜያችን ሰባ ነው፤ ቢበዛም ሰማንያ ይህም ኑሮ ሆኖ፤ ጠዋት ማታ ፍልሚያ አንዱ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን📖

ለጤዛ ተዋድቀን!

እድሜያችን ሰባ ነው፤ ቢበዛም ሰማንያ
ይህም ኑሮ ሆኖ፤ ጠዋት ማታ ፍልሚያ
አንዱ ካንዱ ጥዋ፣ ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ፣ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደ ቄጤማ፣ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ፣ ባጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ፣ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የት ገብተን እንረፍ?
በዶፍ ዝናብ አገር፣ ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን፣ ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን፣ ያከትማል አንድቀን።

- በእውቀቱ ስዩም

@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen