Get Mystery Box with random crypto!

ምን ያደርግልሻል እንዲ መጊያጋጡ ምን ያደርግልሻል እንዲ መዘነጡ ምን ያደርግልሻል እንዲ መቀባቱ እ | ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን📖

ምን ያደርግልሻል እንዲ መጊያጋጡ
ምን ያደርግልሻል እንዲ መዘነጡ
ምን ያደርግልሻል እንዲ መቀባቱ
እንደው ምን ያደርጋል ውበትሽ በሰው መታማቱ
ልብሱንም ተይው ሁሉም ያምርብሻል
ሜካፑም ይቅርብሽ እንደው ያነጣሻል
ጫማስ መቀየሩ ምን ያደርግልሻል
በሲሊፐር ሂጂ እሱ ይሻልሻል
ምንም ባታረጊ ሁሉም ያምርብሻል
ምንም ባትቀቢ እንዲም ያምርብሻል
ለስሙ ነው እንጂ ጨርቁንም መልበስሽ
ኮባ እንኳን ብትለብሺ አጀብ ነው ውበትሽ
እንዲህ ያሉኩሽ እኮ ግራ ቢገባኝ ነው
ባዶ እጄን ቀርቼ ኪሴ ሳስቶብኝ ነው
እንጂማ ምንም ባትለብሺ ምንም ባትቀቢ
ምንም ባትኳይ ጫማም ባታረጊ ምንም ባትዋቢ
መልክሽን ሳስበው ያስፈራኝ ጀመረ
ዝንጀሮን በቅጡ ታሳዪኝ ነበረ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen
@lorate_tsegaye_gebremedihen