Get Mystery Box with random crypto!

27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ: አርሰናል ከ ሊቨርፑል | ኢትዮ-ሊቨርፑል

27ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ:

አርሰናል ከ ሊቨርፑል

ዛሬ ማታ
ማታ 5:15
ኤምሬትስ ስቴድየም

በታላቁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዛሬ ከምሽቱ 5:15 ሲል ክለባችን ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ወደ ኢምሬትስ ስታድየም ተጉዞ አርሰናልን የሚገጥም ይሆናል።

ይህ ጨዋታ አለምን በጉጉት የሚጠብቀው አርሰናል ለቶፕ 4 የሚያደርገው ግስጋሴ የበለጠ የሚያሰምርበት ወይስ ሊቨርፑል ከማንቸስተር ሲቲ ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ በማጥበብ ለዋንጫ ያለው ግስጋሴ የበለጠ የሚጠጋበት ይሆናል? የሚል ጥያቄ የሚመልስ ታላቅ ጨዋታ ነው። ለሁለቱም ክለብ በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ ጨዋታም ነው።

በዚህ የውድድር አመት ከአርሰናል በተለያዩ አጋጣሚ ተገናኝተን በ3ቱም አሸንፈን በአንዱ አቻ መውጣታችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ለአራተኛ ጊዜስ ድል ይቀናን ይሆን? ብዙዎች የማሸነፍ ግምቱ ለሊቨርፑል እየሰጡ ሲሆን ነገር ግን አርሰናሎች በቅርብ ጊዚያት በጣም እየተሻሻሉ መምጣታቸው እና በተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፋቸው ሊቨርፑል ዛሬ ይፈተናል ተብሎ ይጠበቃል።

ሊቨርፑል ከዚህ ጨዋታ 3 ነጥብ ማግኘት የሚችል ከሆነ ከማንቸስተር ሲቲ ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ዝቅ በማድረግ ለዋንጫ የሚደረግ ፍክክር የበለጠ ያሳምረዋል።

|| የየርገን ክሎፕ ገገን ፕረሲንግ አጨዋወት ዛሬ አርሰናሎች እንዴት ይቋቋሙት ይሆን? አርሰናሎችስ በቅርብ እየገነቡት የመጡት ጥሩ የመከላከል መስመር ሊቨፑሎች እንዴት ሰብረው ይገቡ ይሆን? የማን ታክቲክስ ይደምቅ ይሆን? ምሽት 5:15 እንገናኝ።

ድል ለታላቁ ክለባችን ሊቨርፑል